>

ደምሳሽም፣ ተደምሳሽም እኛው ነን፤ ለሰላም እድል እንስጥ..  !!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ደምሳሽም፣ ተደምሳሽም እኛው ነን፤ ለሰላም እድል እንስጥ..  !!!
ያሬድ ሀይለማርያም

ለሰላም እድል መስጠት አይከፉም። ደምሳሽም፣ ተደምሳሽም እኛው ነን። የእርስ በርስ ጦርነት ክፉቱ፤ ሀዘኑ ከቤት አይወጣም። “… ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ” እንደሚባለው ነው ዛሬ ኢትዮጵያ የገጠማት ፈተና።
ስለ ሰላም ሲወራ ደሙ የሚንተከተክ ብዙ ሰው እንዳለ አውቃለሁ። አንዳንዶችም የሰላሙ ነገር ህውሃትን ለማዳን የተመረጠ መንገድ አድርገው ያስቡታል። ይሄ ጦርነት በህውሃት መደምሰስ ብቻ ይጠናቀቃል ከሚል እሳቤ የመነጨ ይመስለኛል። በእኔ እይታ ጦርነቱ በድምሰሳ ይጠናቀቃል ብዮ አላምንም። ያ ጊዜ ያለፈ ይመስለኛል። ህውሃት ከአቧራነት ተመልሳ ትግራይን እንድትቆጣጠር ከተደረገ ወዲህ ነገሮች ተገለባብጠዋል። ህውሃት የትግራይ ወጣቶች እና እጻናት ቢያልቁ ግድ እንደማይሰጠው አሳይቷል።
ጦርነቱ ለተራዘመ ጊዜ መቀጠሉ ደግሞ  እስካሁን ካለቀው በላይ በአሥር ሺዎች የሚቆጠር የሰው ህይወት እናጣለን። በአገሩቱ ኢኮኖሚም ላይ እስካሁን ከደረሰው ጉዳት እጅግ የከፋ ጉዳት ይደርሳል። ቢዘገይም አሁንም ለሰላም እድል መስጠት እና የአገር ሉዐላዊነትን በማይነካ እና ተጠያቂነትንም ባረጋገጠ መልኩ ለውይይት እድል መስጠት ያሸናፊነት ምልክት ነው ብዮ አስባለሁ።
ዞሮ ዞሮ በግራም፣ በቀኝም ሟችም ገዳይም፣ ደምሳሽም ተደምሳሽም እኛው ነን።
Filed in: Amharic