>

የቪኦኤ ነውረኛ ስራና ሴራ ሲጋለጥ...‼! (ETHIO12 NEWS)

የቪኦኤ ነውረኛ ስራና ሴራ ሲጋለጥ…‼!

ETHIO12 NEWS

ቪኦኤ ትህነግ ድርድር ቢጠይቅም በግንባር ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን አስታወቀ፤ ወዴት አቅጣጫ እየገሰገሰ እንደሆን አልገለጸም‼
የአሜሪካ መንግስት የሚመራው የቪኦኤ አማርኛ ክፍለ ጊዜ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ለሃምሳ አምስት የተለያዩ አገራትና ተቋማት ለድርድር እንዲያስቀምጡት ደብዳቤ ማሰራጨቱን ሲያስታውቅ ” በአማራና አፋር ክልሎች የሚያደርጉትን የድል ግስጋሴ” መቀጠሉን በማስታወቅ ሲሆን ” የድል ግስጋሴው” በይተኛው አቅጣጫ እንደሆነ አላብራራም። ትህነግ ከአማራና አፋር ክልል አብዛኛ አካባቢዎች እንዲለቅ መደረጉን አልጠቆመም።
የዝግጅት ክፉል የመቀለ ዘጋቢ ተጠቅሶ በጽዮን ግርማ የተነበበው “የትህነግ የድርድር ጥሪ” ዓላማው በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ላይ ጫና እንዲደረግ የሚጠይቅ እንደሆነ አመልክቷል። “ኃይሎቹ በአማራና አፋር ክልሎች የሚያደርጉትን የድል ግስጋሴ መቀጠላቸውን የጠቀሰው ይሄው አካል ዘላቂ መፍትሄ የሚመጣው ግን በድርድር ላይ በተመሰረተ ተኩስ አቁም መሆኑን አመልክቷል” በሚል የተነበብው ዜና ግስጋሴው ከቀድሞው በሰፋ መልኩ ወደየት እንደሆነ አላብራራም። ወይም እንዲብራራለት ስለመሞከሩ አይጠቅስም።
በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ ሚኒስትር ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ ትህነግ ለሃምሳ አምስት አገራትና ተቋማት የ”አደራድሩኝ” ሰነድ ማዘጋጀቱን አመልክተው ነበር። ሰነዱ መሰራጨቱ ይፋ ከመሆኑ ሳምንት በፊት አቶ ቢቂላ ” ካሁን በሁዋላ ህወሓት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የፖለቲካና ወታደራዊ ኃይል ሆኖ መቀጠል እንዳይችል ተደርጎ እንዲደመሰስ አቋም ተይዟል” ሲሉ አስታወቀዋል።
ህወሃት ድርድርን የሚጠቀመው “ትንፋሽ አግኝቶ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብን ለማሳሳት፤ ጊዜ አግኝቶ ኃይል ለማከማቸት እና ሴራውን ለማስቀጠል እንጅ ቁጭ ብሎ ተደራድሮ የትግራይ ሕዝብ ከዚህ በላይ ሰቆቃ አይገባውም በሚል አስቦ አይደለም”
ቪኦኤ ትህነግ በግንባር ” የድል ግስጋሴው” መቀጠሉን ጠቁሞ የዘገበውን የድርድር ዘገባ ” ወታደራዊ የበላይነቱ ከቀጠለ ለምን የቀድሞው ስምንት ቅድመ ሁኔታ ተነሳ? ስለምንስ ለ55 አገራት ደብዳቤ መሳፍ አስፈለገ? የትህነግ ሰራዊት ከወረራቸው ስፋራዎች በገሃድ እንዲለቅ ከተደረገና እየተደረገ መሆኑ ለቀረበው የድርድር ጥያቄ ” የድል ግስጋሴው እንደቀጠለ ቢሆንም” የሚለው ማጣቀሻ አግባብ ነው ወይ? በሚል መሰረታዊ ጥያቄዎች ያልታሸ መሆኑንን ዜናውን ሰምተው ለኢትዮ 12 ሃሳብ የሰጡት አቶ ኮስትሬ ሃይለ ማሪያም ገልጸዋል።
ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ እንደሆነ አመልክተው ” ቪኦኤ የማንን ምኞትና ሃሳብ እንደሚያራምድ ቢታወቅም፣ ሊጥ፣ ዱቄት፣ ዶሮ፣ ሽሮ፣ በርበሬ … ሳይቀር ተዘረፍን። ቤታችን ቆርቆሮው ተነቅሎ ተጋዘ፣ ከብቶቻችንን በሉ፣ ገደሉ፣ ነዱ… ባሌን ገደሉብኝ፣ እናቴን ዷ አደረጋት፣ ወዘተ የሚሉ ምስክርነቶች ነጻ ከወጡት አካባቢዎች መሰማቱ እያታወቀ የድል ግስጋሴው እንደቀጠለ ቢሆንም ብሎ መዘገብ ታሪክ የሚመዘግበው ቅጥፈትና ክህደት ነው” ብለዋል።
ትህነግ የድል ግስጋሴው የቀጠለ መሆኑንን ቢጠቅስም በምድር ላይ ያለውን ሃቅ ማመጣጠን አግባብ እንደሆነ ያመለክቱት አስተያየት ሰጪ፣መንግስትና አገር ተለይተው መታየት እንዳለባቸው አመልክተዋል። አሁን ጉዳዩ የህዝብ እንጂ የመንግስት አይደለምና ጥንቃቄ ካልተደረገ ጸቡ ከህዝብና ከአገር ጋር ሊሆን እንደሚችል ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እሰከዳር ተንቀሳቅሶ፣ መከላከያም ልዩ ሃይሎችን፣ ሚሊሻና ወጣቱ ደሙን ከፍሎ የተወረረበትን አካባቢ እያጸዳ መሆኑንን በማስረጃ እያዩ ያሉት የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ይህንን ገድል ማራከስ እንደማይችሉና እንደማይፈቀድላቸው አክለው ገልጸዋል።
የትግራይ ዘጋቢ የድርድሩን ደብዳቤ ይዘት ቢያሰራጭም ሃሳቡን መመርመር የኤዲተሮች ሃላፊነት መሆኑንን በማመልከት ሁሉም ተመሳሳይነት እንዳላቸው አክለው ገልጸዋል።
ትህነግ በወረራ ከያዛቸው አብዛናው የአማራና የአፋር ክልል መባረሩን የሚመከታቸው አካላት ማስታወቃቸው፣ መከላከያ አስር ሺህ በላይ የትህነግ ሃይሎች መሞታቸውን፣ በሺህ መማረካቸውንና መቁሰላቸውን ማስታወቁ፣ መከላከያ የጸረ ማጥቃት እርምጃውን አጠናክሮ እንዲቀጥል መታዘዙና ወደፊት እየገፋ መሆኑንን የቪኦኤ የድርድር ሪፖርት ከመሰራቸቱ በፊት መገለጹ ይታወሳል።
ድርድሩን አስመልክቶ አስቀድሞ መረጃ እንዳለ ጠቅሰው አየመንግስትን አቋም ያስታወቁት ዶከተ በቀለ፣ ትህነግ ሲቸግረው ለማምታት፣ ለማገገምና ዳግም የመደራጃ ጊዜ ለማግኘት ድርድር መጠየቅ ባህሪዎ መሆኑንን አመልክተው ይህ እንደማይፈቀድለት በግልጽ ተናግረዋል። አያይዘውም ” ጉዳዩ ከዳር እስከዳር አንድ አቋም ይዞ የተነሳው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነና፣ ህዝቡም ተመሳሳይ አቋም አለው” ሲሉ ጉዳዩን ዘግተዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ክህደት በመፈጸም የተጀመረው ጦርነት አስረኛ ወሩን በያዘበት በአሁኑ ሰዓት በርካታ ወገኖች የሰላም ያለህ ቢሉም በመከላከያ ላይ ክህደት እንዲፈጸም ያዘዙና የፈጸሙ ከፍተኛ የትህነግ ባለስልጣናት በህግ ሊጠየቁ እንደሚገባ በሁሉም ዘንድ ስምምነት አለ። via፦
Filed in: Amharic