>

ጭና ዳግማዊ ማይካድራ...!!! (ሙሉአለም ገ/መድህን) 

ጭና ዳግማዊ ማይካድራ…!!!

ሙሉአለም ገ/መድህን 

በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ በወገኖቻችን ላይ ከተፈፀሙ ግፎች በጥቂቱ፦
➦  ምንም የማያውቁ አርሶ አደሮችን ሰብስበው  በጅምላ ጨፍጭፈዋቸዋል። (ሟቾቹ በተለያየ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ናቸው)፤
➦ በአንዳንድ አርሶ አደሮች ቤት በመግባት የቤታቸውን  ወለል በመቆፈር የጠላት አስከሬን ደራርበው ቀብረውባቸው ሸሽተዋል፤
 (ጠላት ይህን ያደረገው፣ አርሶ አደሮቹ መኖሪያ ቤታቸውን ተጸይፈው እንዲለቁ፣  በቀሪው የህይወት ዘመናቸው የመኖሪያ ቤታቸው ‘መቃብር ቤት’ ሁኖ እንዲሰማቸው ለማድረግ የተፈጸመ ድርጊት ነው)
➦ እዛው ጭና ቀበሌ ውስጥ ከአንድ ቤተሰብ እስከ 6  አባላትን በግፍ ጨፍጭፈው ገድለዋል፤
(የቅርብ ጓደኛዬ፣ ሚስቱ አራት ቤተሰቦቿ ተገድለውባታል። አንደኛው የ72 ዓመት ቄስ ናቸው። ሁለቱ ታዳጊ ወጣቶች ሲሆኑ፤ አንደኛዋ ሟች የአንድ ልጅ እናት ነበረች)
 ➦ ከ40 እስከ 50 የሚጠጋ የንጹሃን አስከሬን በየቦታው  ተገኝቷል፤ (ይህ የጅምላ መቃብሩን አህዛዊ መረጃ አይጨምርም)
➦ ጭና ቀበሌ ተክለኃይማኖት ቤተክርስቲያን በቤተ-መቅደስ ውስጥ ካህናትን አስረው ገርፈዋል፤ አዘፍነዋቸዋል፤ ረሽነዋል፤ (ልብ አድርጉ ቤተመቅደስ ውስጥ ነው በግዳጅ ያዘፈኗቸው)
➦ የጠላት ክፋት ባልጠፋ ቦታ ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ፣ ይባስ ብለው ወደ ቤተ-መቅደስ ድረስ ዘልቀው በመግባት ማብሰያ ምድጃ ሰርተው፤ የአርሶ አደሮችን በግ በማረድ በምጣድ ጠብሰው ቤተ-መቅደሱ ውስጥ  ተመግበውበታል፤
➦ በጭና አሁንም ድረስ ምናቸውም ያልተገኘና ደብዛቸው የጠፉ ወገኖች በርካታ ናቸው፤ ቤተሰቦቻቸው እነሱን ፍለጋ በየጥሻው በመንከራተት ላይ ይገኛሉ፤
➦ የአርሶ አደሮችን በሬ ሳያርዱ፣ በሬው በቁሙ እየተራመደ አንደኛውን ጭን በመቁረጥ ሌላውን በመተው ጠብሰው በልተዋል፤
 (አረመኔነታቸው በሰው ልጅም በእንሰሳት ላይም ስለመሆኑ ደጋግመው በተግባር አሳይተውናል። የአማራ የሆነ ነገር ሁሉ ጠላታቸው ነው።  ሰማይም ቢሆን!)
➦ የቄስ ሚስትን ለ3 ለ4 ደፍረዋል፤ ባልና ሚስትን ድስትና ጭራሮ አሸክመው ወጥ ሲያሰሩ ቆይተዋል፤ ባል እያየ ሚስቱን እንደፈለጉ በመቀያየር ደፍረዋታል፤
(ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ ከሞት የከፋ በደል ነው የተፈጸመው)
➦ የወገን ጦር ማጥቃት ሲያበዛ ጭና ቀበሌን ሲለቁ የተወሰኑ ታዳጊ ወጣቶችን ጓዝ (ስንቅ፣ ጥይት፣…ወዘተ) አሸክመው እንዲሸኟቸው ካስገደዱ በኋላ መንገድ ላይ ሲደክማቸው ረሽነዋቸው ሂደዋል፤
➦ በአጠቃላይ የትግራይ ወራሪና ጨፍጫፊ መንጋ በአማራ ላይ የፈፀመው ህልቆ መሳፍርት ግፍ በምን አይነት ሂሳብ ቢወራረድ እንደሚመለስ አላውቅም።
• አንድ የዋልድባ አባት እንዳሉት፦
“እነዚህ ሰዎች ኃይማኖት የላቸውም። ኃይማኖታቸው ወያኔ የተባለው ድርጅት ነው። ፈጣሪያቸውም መለስ ዜናዊ ነው”
መፍሔው ጊዜ ሳይሰጡ ከፈጣሪያቸው ጋር መቀላቀል ነው።
ከላይ የቀረቡት ጥሬ መረጃዎች የ Thomas Jejaw Molla ናቸው። ሌሎች ቦታው ድረስ የተገኙ የቅርብ ሰዎች መረጃ እንደተጨማሪ ግብዓት ተካተዋል።
Filed in: Amharic