>

አንዳርጋቸዉ ጽጌ:- ግራ በተጋባ በራሱ ማንነት ላይ ሶስት ጊዜ ክህደት ለመፈጽም ሶስት መጽሃፍ የጻፈ  (ሸንቁጥ አየለ

አንዳርጋቸዉ ጽጌ:- ግራ በተጋባ በራሱ ማንነት ላይ ሶስት ጊዜ ክህደት ለመፈጽም ሶስት መጽሃፍ የጻፈ 

ንቁጥ አየለ

1.አማራ ከዬት ወዴት የሚለዉ መጽሃፍ የተጻፈዉ እኔም አማራ ነኝ::አማራን ወክዬ ስልጣን እይዛለሁ የሚል ትልምን ተንተርሶ ነዉ::ይሄ ሀሳብ አይከፋም ነበር::ክፋቱ ግን አማራ ያልሆኑ የከተማ ሰዎችን ሁሉ አማርኛ ስለሚናገሩ ብቻ አማራ ይሁኑ::ኢትዮጵያም ትፍረስ::ኢትዮጵያ ስትፈርስ የአማራ ብሄረተኝነት ይቀጣጠላ የሚለዉ ሸዉራራ ሀገር አፍራሽ ህሳቤ ነበር::የዚህ ሸዉራራ ህሳቤ መነሻዉም ከአማራ በላይ አማራ ሆኖ ለመገኘት የታቀደ መሰረት የሌለዉ ስሁት ስነልቦናዊ ቀመር ነበር::
ይሄን መጽሃፉን ሳያነቡ አንዳንድ የአማራ ብሄረተኞች አንዳርጋቸዉ ስለ አማራ ህዝብ መጽሃፍ ጽፏል የሚል ተረት ተረት ያሰራጫሉ::አንዳርጋቸዉ ይሄን የአማራ ህዝብ ከዬት ወዴት የሚለዉን መጽሃፉን የጻፈዉ ግን በህዉሃታዊ/ኢህ አዴጋዊ የፖለቲካ ፍልስፍና ተቃኝቶ ሲሆን መጽሃፉም የተጻፈዉ ህዉሃት አንዳርጋቸዉን ከአዲስ አበባ ከቲባ ጸሃፊነት ካባረረችዉ ማግስት ነዉ::
2. በሁለተኛዉ መጽሃፉ ደግሞ ኦሮሞነቱን እና አማራነቱን ለማሳዬት ከሁለቱ ነገዶች መወለዱን ለማጣቀስ የተገደደበት ሁኔታ ነበር::ይሄዉም ቅንጅት ህብረ ብሄራዊነትን እያገነነዉ ስለመጣ ነበር::በዚህ ህብረ ብሄራዊነት ምህዳር ዉስጥ በሁለቱ ትልልቅ ነገዶች ተወክሎ መሪነቱን ለመጨበት እና ከኔ በላይ ወካይ የለም የሚል ታሳቢን ያነገበ ነዉ::
3. አሁን ነገሮች ሲገለባበጡ እና የኦሮሞ ብሄረተኝነት ጉልበት ሲያገኝ ደግሞ ሌላ የስልጣን ጎዳና ስልጥ መቀዬስ አስፈላጊ ሆነ::እኔ ኦሮሞ ነኝ::አማራ የሚባል ነገድ የለም ብሎ ቁጭ::ይሄንንም በማለት አሁንም በስልጣን ወንበር ስር የማድፈጥ ስትራቴጅ ስልት እንጅ የኦሮሞን ህዝብ በተለዬ የመዉደድ ባህሪ ኖሮት አይደለም::የስልታን መንገዱ እጅግ ዘወርዋራ እና ብዙ መሆኑን አልሞ የተነሳዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ ሁሉንም ስልቶች እየቀያዬር  እየሞከራቸዉ ይመስላል:: ሁሉም የከተማ ሰዎች እና የአማራ ክልል ህዝብ አማራ ይሁን ሲል አማራ ከዬት ወዴት በሚለዉ መጽሃፉ ያወጀዉ አንዳርጋቸዉ ጽጌ አሁን ደግሞ አማራ የሚባል ህዝብ የለም ብሎ እርፍ::
—————
 ምክር ለአንዳርጋቸዉ ጽጌ
—————–
ከሁሉም  የሚበልጠዉን ኢትዮጵያዊ  ማንነት በምልዓት ብትለብሰዉ እንዲህ የስነልቦና ቀዉስ ዉስጥ አትገባም ነበር::የኢትዮጵያም ስልጣን እግዚአብሄር ከፈቀደልህ ያንተ ይሆን ነበር::ስልጣን ከእግዚአብሄር እንጂ ከዘርህ ወይም ከፓርቲህ አይመነጭም::ሃሃሃሃ…ለኮሚኒስቶች የሚያስቅ የካህን-ንጉስ ፍልስፍና ነገርኩህ አይደለም?
ለማንኛዉም ኢትዮጵያዊነት ከሁሉም ማንነቶች በላይ መሆኑን ብታዉቅ: አንተም ከሁለቱ ነገዶችም ተወልደህ ቢሆን: ወይም ከኦሮሞ ብሄር ብቻ ተወልደህ ቢሆን: ወይም ቀድሞ አማራ ነኝ እንዳልከዉ ከአማራ ብሄርም ተወልደህ ቢሆን ከንኡስ ማንነትህ የሚበልጠዉ አምንነት ኢትዮጵያዊ ማንነት ነዉ ነዉ::ከአማራነትም: ከኦሮሞነትም የሚበልጠዉን ኢትዮጵያዊ ማንነት በእምነት ብትለብሰዉ ከሁሉም በላይ ትከብር ነበር::
እንዲህ አንዴ አንዱ የነገድ ማንነትህ ትዝ ሲልህ ሌላ ጊዜ እንደሌለ ሲጠፋብህ: ሌላ ጊዜ ከሁለት መወለድህ ሲታሰብህ ባትተህ እና ዋትተህ መመላለስህ ያሳዝናል::እንደ ኢትዮጵያዊ ወንድሜ ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ የአዳም ልጅ ወንድሜ የማንነትህ ነገር እንዲህ እስከ አንጥንትህ ድረስ ለምን እንደ በላህ ሳስበዉ አሳዘንከኝ::
ለማኛዉም ኢትዮጵያዊነትን መቶ አመት ነዉ እድሜዉ ብለህ በቅኝ ግዛት የተፈጠረ ሀገር ነዉ ብለህ ብትክደዉም መጽሃፍ ቅዱስ ግን የሚተርክልን ኢትዮጵያዊ ማንነት ከማንኛዉም የነገድ ማንነት በላይ መሆኑን ነዉ::በመጽሃፍ ቅዱስ እግዚአብሄር እራሱ ኢትዮጵያዊ ልጄ ነዉ ብሎ መስክሯል እና::
ኢትዮጵያዊነትን ለኢትዮጵያዊ ሁሉ የሰጠዉ እራሱ እግዚአብሄር ነዉና::የሚቀበለዉ ኢትዮጵያዊ መልካም አደረግ::የማይቀበለዉም ኢትዮጵያዊ መብቱ ነዉ:: ከእዉነቱ ስትቆረጥ ይዘህዉ የምትመጣዉ ትንታኔ ሁሉ ሀስት እና እርስ በርሱ የሚምታት ነዉ::አንዴ አማራ ነኝ: አንዴ አማራ እና ኦሮሞ ነኝ: አንዴ አማራ የሚባል ህዝብ የለም እያልክ መከራህን ታያለህ::አንዴ በስልታን ጥም: አንዴ በበቀል: አንዴም በግል ተራ ፍልስፍና ስትዋልል ትዉላለህ::
ኢትዮጵያዊነት ተፈልጎም የማይገኝ ማንነት ነዉ::ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለዉ ህዝብ እንኳን ቢጥለዉ ሌላ ወገን ያነሳዋል::ጥቁሩ አለም የነጻነት: የእኩልነት: በእግዚአብሄር መንፈስ መወደድን እና በ እግዚአብሄር አይን የታወቀ ህዝብ መሆኑን ማረጋገጫ ቢፈልግ የሚያገኘዉ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ነዉ::
ስለዚህ ዛሬ ኢትዮጵያ የተባለዉ ህዝብ ኢትዮጵያዊነትን አዉልቆ ቢጥለዉ ሌላዉ ወገን አንስቶ ይልብሰዋል::
ኢትዮጵያ ጥሎባት እናንተ ከወያኔ ጋር ሆናችሁ በቀየሳችሁት የነገድ ፖለቲካ ስር ገብታለች እና ገና ብዙ በርካታ ዉጥንቅጦች እና የማምንነት ቀዉሶችን የተሸከሙ ዜጎች ታስተናግዳለች:: አንዴ ይሄኛዉን ነኝ::ሌላ ጊዜ ያኛዉን ነኝ የሚሉ የማንነት ቀዉስ ዉስጥ የሚዳክሩ በርካታ ዜጎች የሚተራመሱባት ሀገር::
በነገራችን ላይ ኢሳያስ አፈወርቂ በአንድ ወገን ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ጥሎ ነዉ ኤርትራዉያንን ከወንድሞቻቸዉ ኢትዮጵያዉያንን የነጣጠላቸዉ::መለስ ዜናዊም በአንድ ወገን ኤርትራዊ ማንነቱን ክዶ ነዉ ኢትዮጵያዉያንን ከወንድሞቻቸዉ ኤርትራዉያንን የነጣጠሏቸዉ::ይሄም ሁሉ የክፋት እና ስልጣን መያዝን እንደ ግብ የመዉሰድ የተሳሳተ ፍልስፍና ነዉ::
የሆነ ሆኖ እግዚአብሄር የታመነ ነዉና  ህዝቤ ያለዉን እና የተወደደ ኢትዮጵያዊነት የተላበሰዉን ህዝቡን ያድናል::
ስለዚህ ከኢትዮጵያዊ ማንነት የበለጠ ማንነት ፍለጋ ሶስት ጊዜ እራስህን ክደህ ለማስተዋወቅ ሶስት መጽሃፍ መጻፍ አያስፈልግህም ነበር::ህዝብም ዝም ብሎ አንተ የምታመጣዉን ተረት ተረት የሚቀበል እንዳይመስልህ::ማበጠሪያዉ ወንፊት እህዝብ ዉስጥ አለና::
Filed in: Amharic