>

" ሰብአዊ መብትን የሚያከብሩበት የሥልጣን ዘመን ይሁንልዎ....!!!" (ያሬድ ሀይለማርያም)

” ሰብአዊ መብትን የሚያከብሩበት የሥልጣን ዘመን ይሁንልዎ….!!!”

ያሬድ ሀይለማርያም

መልካም የሥራ ዘመን ይሁንልዎ! ከክፉ አገዛዝ ብንመጣም በእርሶ ምሪት ያሳለፍናቸው ሦሰት ዓመታት በጭላንጭል ተስፋዎች የታጀቡ እጅግ በርካታ፣ ሰቅጣጭና ፈታኝ የሆኑ ነገሮችን ያስተናገድንበት ነው። ብዙ ዜጎቻችንን በአሰቃቂ ሁኔታ አጥተናል። አስነዋሪና የክፋት ስራዎች የእለት ዜና ሆነው አይምሯችንን አደንዝዞታል። ይህ የሰቆቃ ዘመን እንዲያበቃ እና የተረጋጋ ሀገር እንዲመሩ ከልቤ እመኝልዎታለሁ። ስህተቶችዎን የሚያርሙበት፣ ፍትህ የሚያሰፍኑበት፣ የጎደለውን የሚያቀኑበት፣ ሰላም የሚያመጡበት፣ የሕግ የበላይነትን የሚያረጋግጡበት፣ ዲሞክራሲን የሚያንጹበት፣ ተፈናቅለው በየጥሻው የወደቁ ዜጎችን የሚታደጉበት፣ ሙስናን የሚዋጉበት፣ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጡበትና ሰብአዊ መብትን የሚያከብሩበት የሥልጣን ዘመን ይሁንልዎ። ቃል የእምነት እዳ ነው። የአገር መሪ ሲኮን ግን የሕግና የሕዝብም እዳ ነው። በቃልዎት እንዲኖሩና እንዲመላለሱ እግዚያብሔር ይርዳዎት።

Filed in: Amharic