በአእምሮ ህሙማን የሚመራው የአቢይ ግራኝ አህመድ መንግሥት
ዳግማዊ ጉዱ ካሣ
ሰላም ወገኖቼ፡፡ አለሁ ለማለት ያህል ብቅ አልኩ እንጂ የምናገረው አዲስ ነገር ኖሮኝ እንዳልሆነ በትኅትና መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡ በድረ ገፆች የሚመላለስ ሰው ሲጠፋ ቅር የሚለው ሰው አይጠፋም – አንድም ሰው ቢሆን፡፡ ስሜቱን የሚገልጽበት መንገድ የተለያዬና አንዳንዴም መረሳት ያለና የነበረም መሆኑ ግን የታወቀ ነው፡፡ ለምሣሌ እነይገረም ዓለሙና አሁንገና ዓለማየሁን የመሰሉ ጸሐፍት አሁን አሁን (አ)ሸምቀዋል፡፡ ጊዜው የአርምሞ ይመስላል፡፡ “ጮህን ጮህን እንዳልጮህን ሆን” የሚለው የ“ነባይነ ነባይነ ከእምዘባይነ ኮነ” የግዕዝ ብሂል መገለጫ ትክክለኛ ወቅት ላይ ደርሰናል፡፡ አዎ፣ ዘመኑ የመናገሪያ ሳይሆን የተነገረውን የማስተንተኛና የትንቢቶች ፍጻሜ መታያ ነው፤ የአዝመራ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ ለዐርባና ሃምሣ ዓመታት የዘራነውን ልናጭድ የመጨረሻ የመኸር ወቅት ላይ ነን፡፡ ዐውድማው በሚገባ ተለቅልቋል፤ ገበሬዎች እና አበራይ በሬዎች ተዘጋጅተዋል፤ ንግርቱ አበቅቴውን እየጠበቀ እንጂ ፊሽካውም ከተነፋ ቆይቷል፤ … ምርትና ግርዱ በቅርቡ ይለያል፡፡ ከዚያን በኋላ ኦሮሙማ የለ፤ ኦህዲድና ኦነግ የለ፤ ተላላኪ ብአዴንና ጋንኤል ሕወሓት የለ፤ በአቅጣጫ ስም መጠራት የለ፣ የደቡብና ምሥራቅ ሕዝቦችና ቤርቤረሰቦች የለ፣ የአጋንንት ባንዲራ የለ፤ በየወሩ የሚፈለፈል ክልል የለ፤ በዘርና በቋንቋ መካለል የለ …. መጪው ዘመን ዘመነ ትንሣኤ ነው፡፡ እንኳን ለዋዜማው አደረሰን፡፡ እርግጥ ነው – ከትንሣኤው አስቀድሞ ብዙ ፍስፍስ መኖሩን በተለይ አሁን ጡት ያልጣለ ሕጻንም ያውቃል፡፡
ያልተያያዘ እዚያና እዚህ የሚረግጥ አንዳንድ ነገር ልናገርና ልሰናበት፡፡
አፄ ኃይለ ሥላሤ – (ግማሽ እግዜር – ግማሽ ሰይጣን) – የወሎ ሕዝብ ተርቦ በብዛት ወደሸዋ እየተፈናቀለ በነበረበትና ለገሠ በዙ የተባለ የወቅቱ አስተዳዳሪ “ወሎ መሰደድ ዱሮውንም ብርቁ አይደለም” ብሎ ባላገጠበት ወቅት አፄው ልደታቸውን ለማክብር ከእንግሊዝ ኬክ በማስመጣት ላይ ነበሩ፤ ኬኩ በምንገድ ተሰነጠቀና ለጥገና ተመለሰ፡፡ የኢትዮጵያ መሪዎች ጥጋብና ዕብደት በዚህ ይበልጥ ተገለጠና በዓለም ታወቀ፡፡ ወሎ ጦሰኛ ነው፡፡ በአንድ ወይ በሌላ መንገድ ካኮረፈና በገዢዎች ላይ ከተቀየመ እርግማኑ መቀመቅ ይከታል፡፡ ሰውዬውም 67ን አላለፉም፡፡ የመሪዎች አእምሮ ግን ምን ያህል በሥልጣን ሱስ ሊያብድና የቆመለትን ዓላማ ጭራሽ ሊስት እንደሚችል ይህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ተረግመዋል መሰለኝ፡፡
የደርጉ መንግሥት ወሎ ተርቦ መከራ ፍዳውን እየበላ ከዚችው ከእንግሊዝ የብር 500 ሽህ ዊስኪና ልዩ ልዩ መጠጦችን አስመጥቶ የኢሕድሪን ምሥረታ በፌሽታና በፈንጠዝያ አከበረ፡፡ ብዙም አልቆዬ፤ የኢትዮጵያን መንግሥታት ድንቁርና ለዓለምና ለራሱ ሕዝብ በይፋ አሳይቶ በባራባሶ ተጫሚዎች፣ በሰባራ ክላሽ ታጣቂዎች፣ በአሻጥርና በዓለም አቀፍ ሤራ እንዲሁም በሕዝብ ኩርፊያና ጥላቻ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ታንኩንና መትረየሱን ለወያኔ በማስረከብ እግር አውጭኝ አለ፤ እኛንም ሀገራችንንም አዋረደ፡፡ ለተከታታይ የቀን ጅቦችም አጋልጦን ከሰመ፡፡ ለአፍሪካ የሚያስፈራ ኃይል ቀን ከዳውና በቀላሉ ተፈረካከሰ፡፡ ይህ ታሪካዊና መለኮታዊ ቅጣት ጥጋበኛና ዕብሪተኛ ለሆነ ሁሉ የሚቀር አይደለምና በዚህ ዓመትም አቢይና ጭፍሮቹ ላይም ሲደገም እናያለን፡፡ እኔና አንተ ባናይ ቀሪ ያየዋል፡፡ በርግጠኝነት!!
ዘረኛው የመለስ መንግሥት አማራን ከኢትዮጵያ ጨርሶ ለማጥፋት ዐውጆ ከውስጥና ከውጭ ተባባሪዎቹ ጋር ብዙ ዓመታትን ደከመ፡፡ ኢትዮጵያና አማራ አዘኑበት፤ አለቀሱበት፡፡ በመጨረሻም በአፍላ የአምባገነንት ዕድሜው አይሆኑ ሆኖ ተቀጨ – ፈራርሶ፡፡ አማራና ኢትዮጵያ የረገሙት መቅኖ የለውም፡፡ እነስብሃት ነጋንና ሌሎች የሞቱና የታሰሩ እንዲሁም በዱር በገደል የሚንከራተቱ ፀረ ኢትዮጵያ ወገኖችን ማየት ይቻላል፡፡ አሁን አራት ኪሎ ላይ የሚንጎማለሉትን የአቢይ ውሾች ተዋቸው፤ነገ መግቢያ ሲያጡ ታያላችሁ፡፡ የኢትዮጵያን አምላክ አይቀጣጠቡትም፤ ኢትዮጵያ ሦርያ ወይንም የመንና ሰሜን ኮርያ አይደለችም፡፡ አሁን በአማራ ሬሣ ላይ እየሸና ያለው አማራን አቅፎ የሚያድረውና ከአማራ የተዋለደው አቢይ ወይም ወንደሙ ሽመልስ ወይንም ታዬ ልበደንዳና መጨረሻቸውን ለማየት ትንሽ መታገስ ነው – ትንሽ፡፡ የነዚህ ውድቀት ከነዚያኞቹ የከፋ ነው፤ ሲፈርድባቸው ዙሩን እጅግ አክረሩት፡፡ ለበጎ ነው፡፡
ይህ ጉግማንጉግ ልጅ በሥልጣንና በዝና ፍቅር ራሱ ታውሮ ሌሎችንና ደህና ናቸው የሚባሉትን ጭምር እያሳወረ ይገኛል፡፡ የሥነ ልቦና ህመሞች ጎተራ የሆነው ይሄ ብላቴና እንደከብት በዐይን ጥቅሻ ሊያዛቸውና ሊነዳቸው የሚችሉ ንፍጣቸው ያልደረቀ ውርጋጦችንና ሣዱላዎችን ከየሥርቻው እየሰበሰበ በሚስትነትና – ማነው – በሚኒስትርነትና በትላልቅ ሹመኝነት መመደቡን ተያይዞታል፡፡ የሥልጣን ጥም አቅሉን ያሳተው አቢይ ግራኝ አህመድ የሥልጣን አሰጣጥ መሥፈርቱን ሃይማኖት፣ ዘርና ፆታ አድርጎ ችሎታንና ብቃትን ገደል ሰዷቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ጤናማ አሠራርና አግባብነት ያለው የአስተዳደር ዘይቤ እንጦርጦስ ወርደው ሀገር የማይማንና የልበ ሥውራን መጫወቻ ሆናለች፡፡ ለበጎ ነው እንበል፡፡
የሰሞኑ ደግሞ ለየት ይላል፡፡ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በኦሮሙማ የፖለቲካ ሤራና ሻጥር ምክንያት በተለይ አማራው በአጠቃላይ ደግሞ ትግሬውና አማራው በጦርነትና በርሀብ እያለቁ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ከመኖሪያው ተፈናቅሎ በየመጠለያ ጣቢያው ውስጥ እንደከብት ታጉሮ በርሀብና በበሽታ እየረገፈ፣ በወለጋ አማራዎች በኦነግሸኔና በሽመልስ አብዲሣ ጦር እየተመተሩ፣ በመሀል አገር ሕዝቡ በኑሮ ውድነትና በግልጽ እግር አውጥቶ በሚሄድ የሙስና ሰንሰለት ቁም ስቅሉን እያዬ… ይህ ማፈሪያ የዲያቢሎስ ወኪል ለቀናት በሚዘልቅ የሥርዓተ-ሺሞት ድግስ ከቢጤዎቹ ጋር ዳንኪራ ይረግጣል፤ በዚህ ሰው አገዛዝ ሥር መውደቅ በውነት መረገም ነው፡፡ የሚሰቀጥጥ ሀገራዊ ነባራዊ እውነት፡፡ በዚህ ሰውዬ ድርጊት አሁን የማያፍር መቼም አያፍርምና ከአቢይ ተለይቶ ሊታይ አይገባም፡፡ ከፍ ሲል የተጠቀሱት የሀገራችን መሪዎች ካደረጉት ይህኛው በእጅጉ የሚለዬው የአሁኑ ዘረኝነት ላይ የተመሠረተ መሆኑና የቅጣቱ ዓይነትና የአመጣጡ አቅጣጫ በጣም ብዙ በመሆኑ ነው፡፡ አቢይ ሰይጣን መሆኑን ብዙዎች አያውቁም፡፡ እንዲያውም በተንኮልና በሸር ሰይጣንን የሚያስከነዳና እርሱ ራሱን ሊያሰለጥን የሚችል ነው፡፡
ህመምተኛው አቢይ የሚሾማቸውን ሰዎች ዓይነትና ስብጥር ስናይ ደግሞ ልጁ በርግጥም ያልታደለና እኛ እርግማናችን ያልተነሳልን መሆናችንን እንረዳለን፡፡ ነገረ ሥራው ሁሉ “ማን ምን አባቱ ያመጣል!” የሚል ይመስላል፡፡ በሽተኛ ሰው መያዝ የማይገባውን ሥልጣን ሲይዝ ምን ሊያደርግ እንደሚችል አቢይን በማየት መረዳት ይቻላል፤ ለይቶለት አፄ ቦካሣንና ኢዲያሚን ዳዳን ሆኖት አረፈው፡፡ የሚገርም ሀገራዊ ሥዕል እያየሁ እኔማ ተገርሜና ተሳቅቄ ልሞት ነው፡፡ አዲስ አበቤንና ኢትዮጵያን በጥቅሉ የጠላ ብቻ ሳይሆን እንዳይሸጡ እንዳይለወጡ አድርጎ የተሳደበ ፓርላማ ይገባል – በኩራት፤ እሱም ብቻ ሳይሆን ይህ ሰው ቦሌ ላይ አቀባበል ሲደረግለት ለሚመለከት “አዲስ አበቤ ነኝ ባይን የፊንፊኔ ወራሪ ሁላ እንኳን በስድብ ሞለጭክልን” የሚል መልእክት እንዳለው መገንዘብ አያቅተውም፡፡ ይህም አቢይ ያጸደቀው ስድብ ለመሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡
በጫካ አማራን ሲፈጅና ሲያስፈጅ የነበረ የሸኔ መሪ ፕሬዝደንታዊ አቀባበል ተደርጎለት በቦሌ ሲገባ ለሰላም የታገለ ንጹሕ ዜጋ ግን ወደ ከርቸሌ ይወርዳል፡፡ አናቷ ላይ የኦህዲድን ጨርቅ ጠምጥማ፣ የዝንጀሮ ይሁን የሰው መሆኑ የማይታወቅ ሞተከዳ ፀጉር ከእርግብግቢቷ እስከ መቀመጫዋ የፀጉር ዘባተሎ ከምራ (መጌጡ ነው እኮ! ኡኡቴ!)፣ የትምህርት ሚኒስትርነቱን ቦታ ለኔ ስጡ የምትለዋ “ዶክተር” ጉዳይ ደግሞ እዚህ ላይ ሳይጠቀስ መታለፍ የለበትም፡፡ አቢይ በምን ዓይነት ሰዎች መከበብ እንደሚፈልግ ጠቋሚ ነውና የዚህች ሴት ልጅ ነገር በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ ጉድ ነው ዘንድሮ መቼም! ይህን ሁሉ የአቢይ ዕብደት የሚመለከቱ የርሱ አምላኪዎች አሁን ምን እንደሚሰማቸው አላውቅም፡፡ ግን መርዙ የሚለቃቸው አይመስልም፤ አለመለከፍ ነው ወንድም እህቶቼ፡፡ መርዙ ደግሞ ካልገደለ አይለቅም መሰለኝ፡፡
ልጂቱ ዱክትርናውን በእንትን እንዳገኘችው ቋንቋ አጠቃቀሟ ራሱ ምስክር ነው – ለነገሩ መምህሮቿ ራሳቸው ከርሷ እምብዝም የሚሻሉ ሊሆኑ አይችሉም፤ መለስና ገነት ዘውዴ አፈር ከድሜ ያበሉት የትምህርት ሥርዓት ስሙን በእንግሊዝኛ የማይጽፍ ዶክተርና ፕሮፌሰር ቢያመርት አይፈረድበትም፡፡ በዚያ ላይ ይሄ የፈረደበት የሴቶች እንትንና ዘረኝነት እንዲሁም ሃይማኖት ምናልባትም ገንዘብና ሌላ ሌላ ነገር ተጨምሮበት ያው ቦሃ ላይ ቆረቆር እንዲሉ ነው፡፡ እርሷ የተሳሳተችውን የሰዋስው ስህተት እኔ የርሷን የመሰለ ትልቅ የትምህርት ቤት ደጃፍ ያልረገጥኩት ደንቆሮ አልሠራውም፡፡ በዚያ ችሎታዋ ደግሞ እንኳንስ የትምህርት ሚኒስትርነትን ቦታ በየትኛውም ትምህርት ቤት የአስማሪነት ሥራ ልታገኝ አይገባም፡፡ የነጠላና የቁጥር ስህተት ከታች ክፍሎች በቀላሉ መስተካከል ያለበት ስህተት እንጂ እስከዶክትሬት ሊዘልቅ አይገባውም፡፡ ምን አለች – We are educator. ምን መባል ነበረበት – We are educators. ስለዚህ ነገ ጧት በተማሪዎች ፊት “He are my husbands you is mine dads.” ላለማለቷ ምንም ዋስትና የለንም – ትንሽ የሚመስል ነገር ደግሞ የትልቅ ነገር ምልክት ነው፤ ይህ ስህተት ብዙ ነገር ይጠቁማል፡፡ ሹመቱ ለርሷ እንደሚገባ ስትናገር ደግሞ በከፍተኛ የራስ መተማመን ነበር የምታስረዳው – ሊያውም አሁን ድረስ የምታመልክባትን አገር አጥፊ ዮዲት ጉዲትን(ገነትን) እየጠቀሰች፡፡
ጠቅለል ባለ አገላለጽ አቢይ የያዛት ኢትዮጵያና ሕጻን ልጅ የያዘው ዕንቁላል አንድ ናቸው፡፡ ሁለቱም የመትረፍ ዕድላቸው በእግዚአብሔርና በዕድል መካከል ብቻ ተንጠልጥሎ ይገኛል፡፡ ዕንቁላሉ የራሱ ጉዳይ፤ ኢትዮያን ግን እግዚአብሔር ይናት፤ ደግሞም ይደርስላታልና ብዙም አንስጋ፡፡ ግን እንጸልይ፡፡ የቀረን ትልቁ የመዳኛ መሣሪያ ጸሎት ነው፡፡ ሰውንማ እስኪበቃን አየነው፡፡ አላየነውም? እርግጥ ነው – እግዚአብሔርም ቢሆን ራሱ መጥቶ ጦርነትን አይዋጋም፤ ሰዎችን መላክን ግን ያውቅበታልና ለራሳቸው ሳይሆን ለወገንና ለሀገር የሚጨነቁ የሚጠበቡ ቅንና በጎ አሳቢ ዜጎችን ይላክልን፡፡
የምተርፍ ከሆነ ከነጻነት በፊት ወደዚህ መድረክ ላለመምጣት ፈጣሪ ይሁነኝ፡፡ መልካም ክራሞት፡፡ ግን ግን አቢይ ያከረፋብንን/ያበላሸብንን ለክፉ ቀን ይሆኑናል ያልናቸውን ሰዎች እንዴት መልሰን እንደምናገኛቸው ይጨንቀኛል፡፡ ሥልጣንና ሀብት መጥፎ ነው፡፡ ዝናና ዕውቅና የሰውን ኅሊና ይቀይራል፡፡ አቢይ አሉን የምንላቸውን ሰዎች ሁሉ እንደአጋዘን እያደነ ተራ በተራ ሁሉንም ሊያበክትብን ነው፡፡ ብዙ ሰዎችን እንዳልተፈለፈለ ዕንቁላል አገማብን፡፡
እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክ፤ አሜን፡፡