>

ህወሓት እድል ቀንቶት አዲስ አበባ መግባት ቢችል ምን ያደርጋል? (ሳምሶን ገረመው)

ህወሓት እድል ቀንቶት አዲስ አበባ መግባት ቢችል ምን ያደርጋል?

ሳምሶን ገረመው

– የመጀመሪያው ስራ አገርን በማረጋጋት ስም የክልል መዋቅሮችን ዳግም መቆጣጠር ይሆናል::
– ለይስሙላ የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታውን ኦሮሞ እንዲይዘው ያደርጋል::
– ትግራይ ክልል ከቤንሻንጉል እና ከጋምቤላ ክልሎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲኖራቸው በማድረግ ልዮ የሆነ ክልላዊ ህብረት ( እንደ ኮንፌደሬት) እንዲመሰረቱ ያደርጋል:: በሁለቱ ክልሎች አጥተውት የነበረውን ንብረት እና ይዞታ መልሰው እንዲወስዱ ይደረጋል:: ሌሎች በርካታ ትግሬዎች በክልሎቹ እንዲሰፍሩም ይደረጋል::
– አማራ ክልል በበርካታ ክልሎች እንዲሰነጣጠቅ ይደረጋል:: ቅማንት: ዋግ ህምራ: አገው: ራሳቸውን የቻሉ ክልሎች ይሆናሉ:: የኦሮሚያን ገዥዎች ልብ ይበልጥ ለማማለል: የደቡብ ወሎ ከሚሴ እና አካባቢው በኦሮሚያ ክልል ስር ሆኖ እንዲተዳደር ያደርጋል::
– በደቡብ: በቅድሚያ ወላይታ ክልል እንዲሆን ያደርጋል:: ለሌሎችም እንደዚያው::
– ሶማሌ ክልል ከሁሉ ቀድሞ አንቀፅ 39ኝን ተጠቅሞ እጅግ ተጠናክሮ ለመገንጠል እንዲችል ያዘጋጀዋል:: በዚህ ሚክንያት ከኢትዮጲያ ጋር የመኖር ፍላጎት እንዳይኖረው ይደረጋል:: በማእከላዊው መንግስት ተሳትፎ እንዳይኖረው ይደረጋል::
– በመጨረሻም: ከሁሉ አስቀድመው: ትግራይ ክልል (ወልቅይት ጠገዴና ጠለምትን: ራያ ከአለውሃ ድረስ ዘልቆ ያለውን ቦታ ሁሉ አካትቶ) ለመገንጠል ህዝበ ውሳኔ እንዲያደርግ ይሰራል:: በውጤቱ ትግራይ ትገነጠላለች:: ልክ ህወሓት ለኤርትራ እንዳደረገው ሁሉ: በህወሓት ቁጥጥር ስር ያለው የኦሮሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኢትዮጵያን ወክሎ የትግራይን መገንጠል እና አገር መሆን እውቅና እንዲሰጥ ይደረጋል::
– የትግራይን መገንጠል ተከትሎ: በአጭር ጊዜ ውስጥ: በህወሓት ወታደራዊ እና የደህንነት መዋቅር ፍፁም ቁጥጥር ውስጥ ያሉት ቤንሻንጉል እና ጋምቤላ ህዝበ ውሳኔ አድርገው እንዲገነጠሉ ይደረጋል::
– የታላቋን ትግራይ ህልም እውን ለማድረግ: ጋምቤላ እና ቤኒሻንጉል የቅማንት ክልልን ጨምረው ከትግራይ ጋር የኮንፌደሬት ህብረት አድርገው አንድ ካርታ ውስጥ ይጠቃለላሉ:: አማራ አገር አልባ ይሆናል:: ኦሮሚያ የሚባል አገር ለመመስረት በሚደረገው ጥረት የኦሮሞ ህዝብ እርስ በርሱ ይባላል:: ከሶማሌ ጋር ማለቂያ የሌለው ፀብ ውስጥ ይገባል…
– አፋር ክልልንም አልረሳሁም:: አፋር ልክ እንደ ቤንሻንጉል እና ጋምቤላ ሁሉ በመጨረሻ በትግራይ ስር ይጠቃለላል:: የትግራይን የባህር በር ባለቤትነት ለማረጋገጥ አፋር የግድ አስፈላጊ ነውና::
– ደቡብ ያለው ህዝባችን: እንደ ወላጅ አልባ ህፃን ልጅ የትም ተበትኖ ይቀራል::
– በመጨረሻም ትልቁን ኪሳራ ተከናንቦ የሚቀረው ግን ኦሮሚያ የሚል ህልም ይዞ ባዶውን የሚቀረው የኦሮሞ ፓለቲከኛ ይሆናል:: ትልቁ ስኬቱ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተጫወተው ጉልህ ሚና እንደሆነ ተደርጎ ይነገርለታል::
Filed in: Amharic