>

መከላከያ ሰራዊት የአምባሰል ገዥ መሬቶችን አስረከበ...!!! (ወንደሰን ተክሉ)

መከላከያ ሰራዊት የአምባሰል ገዥ መሬቶችን አስረከበ…!!!

ወንደሰን ተክሉ

በህወሃት አሸባሪ ታጣቂዎች ትንኮሳ ለአንድ ሳምንት የዘለቀው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዛሬ ትላንት እና ዛሬ አዳሩን ደቡብ ወሎ አምባሰልን ውጫሌን ለመያዝ በመከላከያ ሰራዊት እና በህወሃት ከባድ ፍልሚያ ተደርጓል፡፡
 ትላንት እስከ ምሽት በተደረገው ውጊያ የአምባሰል ወረዳ ወጣቶች እና አመራሮች ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በመሆን ሲፋለሙ ውለዋል፡፡
ይሁን እና ወደ ስፍራው ያቀናው የመከላከያ ሰራዊት አፈግፍጎ የህወሃት ታጣቂዎች የአምባሰልን ሰንሰለታማ ተራሮች ተቆጣጥረዋል፡፡
መከላከያ ሰራዊትን ሊያግዝ ወደ ስፍራው የወጣው ወጣት ትላንት ማታ እስከ 4 ሰዓት ድረስ በየጫካው ተበትኖ ነበር፡፡
ከውጫሌ ከተማ ከፍ ብሎ በሚገኘው አበት አቦ ትምህርት ቤት፣ ወሊ፣ ቢዘን፣ ኳሻት ኢየሱስ፣  የውርጌሳ እና የአምባሰል ተራራማ ቦታዎችን ማለትም ገምሻት፣ ጎሎ፣ ጋቲራ፣ አዲስ አምባ ፣ ቋሆ እና ብርኩማ አምባየህወሃት ወታደሮች መሽገውበታል፡፡ የመከላከያ ሰራዊት ከተማዋን ለቆ እየወጣ ነው፡፡ ውጫሌ እስከ አሁን አልተያዘችም!!!
ጃንጥላው
Filed in: Amharic