>
5:33 pm - Thursday December 5, 9895

ለታላቁ የትዝታ ንጉስ ለአርቲስት መሃሙድ አህመድ  የክብርና የዕዉቅና ስነ-ስርዓት ዛሬ በዋሽንግተን ይካሄዳል...!!!

ለታላቁ የትዝታ ንጉስ ለአርቲስት መሃሙድ አህመድ  የክብርና የዕዉቅና ስነ-ስርዓት ዛሬ በዋሽንግተን ይካሄዳል…!!!
ሳይበርዜና ሲቲዝን

 

*….  የምን ጊዜም የበላይ ” ሆኖ ዛሬን ደርሷል። ጋሽ መሃሙድ በሰራዎቹ ሰርቶ ፣  ለፍቶ ሙዚቃን ከብሮ ጥበብን አስከብሯታልም። በተፈጥሮ በተለገሰዉ ሆድ የሚያባባና ፣ትናንትን በምልሰት በሚከስት አይረሴ የትዝታ ቅላፄዉ ድንገት የጀመረዉ የሙዚቃ ህይወቱ ከሃገሩ እስከ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መድረኮች  ” አንቱ ” አሰኝተዉታል.   ….!!!
 
   ኢትዮጵያዊዉ የትዝታ  ሙዚቃ ንጉስ  ድምፃዊ መሃሙድ አህመድ በኢትዮጵያዉያን የኪነ ጥበብ ምኩራብ ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በዘለቀ ትጋቱ በተለይም በትዝታ ስልት ” የምን ጊዜም የበላይ ” ሆኖ ዛሬን ደርሷል። ጋሽ መሃሙድ በሰራዎቹ ሰርቶ ፣  ለፍቶ ሙዚቃን ከብሮ ጥበብን አስከብሯታልም።
  በተፈጥሮ በተለገሰዉ ሆድ የሚያባባና ፣ትናንትን በምልሰት በሚከስት አይረሴ የትዝታ ቅላፄዉ ድንገት የጀመረዉ የሙዚቃ ህይወቱ ከሃገሩ እስከ ዓለም አቀፍ የሙዚቃ መድረኮች  ” አንቱ ” አሰኝተዉታል።
  ተግባቢዉ ፣ሳቂታዉና፣ ብርቱ የስራ ተምሳሌቱ ጋሽ መሃሙድ ተቀጥሮ ይሰራበት ከነበረዉ አንድ ሆቴል የተጠነሰሰዉ የጥበብ ህይወቱ ከክቡር ዘበኛ እስከ ቤተ መንግስት  ፣ ከቤተ መንግስት እስከ ቀዳማዊ ሃይለስላሴ ቲአትር፤  ከትዝታ እስከ አይረሴ የጉራጊኛ ስልትና ዉዝዋዜ አንግሶታል ። አርቲስቱ በትጋቱ ድንበር ተሻግሮም የኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘዉግን ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ወስዶ  አስከብሮታል።
  እናም በኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ ከስልሳ ዓመታት በላይ፤ የሀበሻ የሙዚቃ ህብረ ቀለም የሆነዉን አንጋፋ የትዝታ ሊቅ ታላቁን አርቲስት መሃሙድ አህመድን ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ፣ ወዳጆቹና ፣ የጥበብ አፍቃሪዎቹ ዛሬ በዋሸንግተን ዲሲ ሂልተን ለጥበብ አስተዋፅዎዉ ያከብሩታል፣ ያመሰግኑታል  ፣ ያነግሱታልም። የምስጋናና የእውቅና ስነ ስርዓቱን ተከታትለን እናደርሳችሃለን።
Filed in: Amharic