>

ከጨፌ ኦሮሚያ  እስከ ሚኒልክ ቤተመንግስት ÷ የሚርመሰመሰዉ  የህዉሃት ደህንነት  በወፍ በረር ሲዳሰስ....?!? (ሸንቁጥ አየለ)

ከጨፌ ኦሮሚያ  እስከ ሚኒልክ ቤተመንግስት ÷ የሚርመሰመሰዉ  የህዉሃት ደህንነት  በወፍ በረር ሲዳሰስ….?!?
ሸንቁጥ አየለ

*  …. ከኦህዴድ መከላከያ ጋር ያልተነካካ የጦር ሀይል ብቻ ህዉሃትን መደምሰስ ይችላል። የኦህዴድ መከላከያ ዉስጥ የተሰገሰጉ አመራሮች “ለአማራ መሬት አንዋጋም” የሚሉት አባባል ጥልቅ የሆነ  ጸረ አማራ ስነልቦና ስለተቆራኛቸዉ ብቻ ሳይሆን ከጨፌ ኦሮሚያ እስከ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት ህዉሃት የዘረጋችዉ የደህንነት መረብ ዉስጥ የወደቁ በመሆናቸዉም ነዉ። 
  የስነልቦናዉኢ ቀዉሱን ብቻዉን እንኳን ብናዬዉ አቢይ አህመድ ሰሞኑን የተናገረዉን ንግግር መመርመር በቂ ነዉ።ለራሱ መንግስት የሚዋጉለትን ታጣቂዎች ጠቅላይ ሚኒስቴር ሰሞኑን ምን ብሎ እንደወንጀላቸዉ ማስተዋል ብቻ በቂ ነዉ። ህዉሃት አንዴ የአማራን ክልል ከተቆጣጠረ ኦህዴድን ከቤተ መንግስት ለማባረር ሁለት ሰዓት በቂዉ ነዉ።
ይሄን መላዉ የኦህዴድ ሀይል ያዉቃል::
ኦህዴዳዉያን ግን አማራ ክልል ላይ ህዉሃት ከሚሸነፍ ይልቅ የተቆጣጠሩትን መንግስትነት ቢያጡት ይመርጣሉ ::ይሄ ጉዳይ ትልቅ የስነልቦና ህመም ነዉ። ጠቅላይ ሚኒስቴሩ የተናገረዉን እንዲሁም በግንባር ያሉ የኦህዴድ የጦር አዛዦች
  “ለአማራ መሬት አንዋጋም” የሚሉት አባባል  የስነልቦናን ጥልቅ በሽታ ያሳያል። ኢትዮጵያን ወርሰዉ እና እግዚአብሄር መንግስት አድርጓቸዉ ሳለ የራሳቸዉን የመንግስት መሰረት ለመናድ የሚሄዱበት ርቀት አስገራሚ ነዉ።
ልክ ህዉሃት ኦህዴድ ከብአዴን ጋር ተባብሮ ከቤተ መንግስት አባሯት ሳለ “ብአዼን ብቻዉን ነዉ ያባረረኝ ” ብላ ሚሊዮን ጊዜ የጥላቻ መርዟን በአማራ ህዝብ ላይ  እየረጨች አማራን እበቀላለሁ እያለች እንደምታጓራዉ አይነት የስነ ልቦና በሽታ አይነት ኦህዴዶችም ዉስጥ እንደ ካንሰር ተሰራጭቶባቸዋል።
ለጨበጡትን ስነ መንግስት  ግንባር እና መሰረት ሆኖ የሚዋጋላቸዉን የአማራ ገዥ መሬት “ለአማራ መሬት ብዬ አልዋጋም” ብሎ ትጥቅና ስንቅን እንዲሁም ገዥዉን መሬት ለወያኔ እያስረከቡ ከመፈርጠጥ የከፋ ታላቅ በሽታ ከቶም የለም።
አቢይ አህመድም መከላከያዉን ቀድሞ የህዉሃት አባል ለነበረዉ ሰዉዬ አስረክቦ ከህዉሃታዉያን ጋር ድርድር እያደረገ ስልጣኑ የማይቀማ እስኪመስለዉ እንቅልፍ ዉስጥ የገባዉ ዝም ብሎ አይደለም። መራራ የስነልቦና ችግር ነው።
 ለእሱ ስልጣን እየተዋደቀለት ካለዉ ሀይል ይልቅ ከህዉሃታዉያን ጋር የተሰናሰነ ስነ ልቦናዊ ቁርኝት ነዉ። ለማንኛዉም ህዉሃትን ከኦህዴዳዉያን ጋር ተሰልፌ እደመስሣታለሁ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነዉ።
ህዉሃትን ሊደመስሳት የሚችል አንድ ሀይል ብቻ ነዉ። ይሄዉም እራሱን ከኦህዴዳዉያንም ሆነ ከህዉሃታዉያን አተላ ተሸካሚዎች ነጻ ያደረገ ሀይል ብቻ ይደመሣታል። ጦርነት ከጦር መሳሪያ በላይ የጦርነቱን ሚስጥር መጠበቅ ትልቁ የማሸነፊያ ቁልፉ ነዉ።
 አሁን ባለዉ ሁኔታ ግን ከኦህዴዳዉያን ጸረ አማራ የስነ ልቦና በሽታ በተጨማሪ የኦህዴድ እና ኦነግ የተጨመላለቀ አንድነት በጣም ትልቁ አስጠቂ ነገር ነዉ። ኦህዴድ እና ኦነግ በአደባባይ የተጣሉ ቢመስሉም በአንድ መርህ ላይ ግን ሳይነጋገሩ ይግባባሉ። ይሄዉም በጸረ አማራ አቋማቸዉ። ሆኖም ኦህዴድ እና ኦነግ በስልጣን ደግሞ መርህ አልባ በሆነ መልክ ተጣልተዋል። መርህ አልባ የሚያስብለዉም ጦርነት በመንግስት ላይ ያወጁት ኦነጋዉያን ዉሏቸዉም አዳራቸዉም ከቤተመንግስት እስከ ጨፌ ኦሮሚያ ነዉ።
ይሄም ማለት ህዉሃት ከጨፌ ኦሮሚያ እስከ እስከ ቤተ መንግስት ያሰለፈቻቸዉ የደህንነት ሀይሎች አሏት ማለት ነዉ።ይሄዉ የተወሳሰበ አሰላለፍ ጥልቅ ከሆነዉ የጸረ አማራነት ስነልቦና ጋር ሲጋመድ ኦህዴድ ዉስጥ ሚስጢር ሊጠብቅ የሚችል አመራር ይገኛል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነዉ።
በአጭሩ ከኦህዴድ ጋር ሆኖ መዋጋት ሚስጢር የባቄላ ወፍጮ ነዉ።ይሄዉ ጉዳይ አዲስ ከተሾመዉ የቀድሞ የህዉሃት ሰዉ መከላከይ ሚኒስቴር ሆኖ መሰዬም ጋር ተዳብሮ ሲታይ እዉነታዉን መራር ያደርገዋል። ስለሆነም ከጨፌ ኦሮሚያ እስከ ቤተ መንግስት ከዚያም ሲዘል መከላከያ ዉስጥ እስከተሰገሰገዉ የህዉሃት ደህንነት ሚስጢር ጥበቃዉን ፈጽሞ አዳጋች ያደርገዋል። ይሄን ሁሉ ፈተና አልፎ ሚስጢር ተጠበቀ ቢባል እንኳን በስነልቦናዊ ህመም የራስን መንግስት ለማጣት የሚያስችል  እርምጃ ይወሰዳል።
ስለሆነም ማንም ህዉሃትን እደመስሣለሁ ብሎ ካሰበ እጅግ ጥብቅ በሆነ መልክ ሚስጢሩን መጠበቅ የሚችል ሀይል ሊኖረዉ ግድ ነዉ። ሚስጢሩን መጠበቅ የሚችል ሀይል ህዉሃትን በግማሽ ሰዓታት ከተከዜ ማዶ አሻግሮ ማባረር ይችላል። በሶስት ወራት ዉስጥ ደግሞ ህዉሃትን ከመላዉ ትግራይ መደምሰስ ይችላል። በጥቂት አመታት ዉስጥም ህዉሃት. ከትግራይ ህዝብ ልብ ዉስጥ ፍቆ በማዉጣት ለኢትዮጵያ አንድነት እና ሰላም የሚሆን መደላድል መፍጠር ይችላል።
Filed in: Amharic