>

የትግራይ ሰራዊት ዋና አዛዥ ታጋይ ታደሰ ወረደ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለሰራዊቱ ያስተላለፉት መልእክት - ትግራይ ሚድያ

የትግራይ ሰራዊት ዋና አዛዥ ታጋይ ታደሰ ወረደ ለኢትዮጵያ ህዝብ እና ለሰራዊቱ ያስተላለፉት መልእክት
ትግራይ ሚድያ
ለኢትዮጵያ ህዝብ ያስተላለፋት መልእክት፦
” ይህ ጦርነት መቆም አይችልም።ሊያስቆመው የሚችል ኃይልም የለም። እንጨርሰዋለን! በዚህ በምንጨርሰው ደማዊ ጦርነት አሁንም ልጆችህን ልታሳትፋቸው አይገባም!  በየአካባቢው እነዚያ በየሚዲያው ብቅ እያሉ የሚፎክሩ፤ እየዋሹ በማይመለከትህ ጦርነት የሚያነሳሱህ፤ ብዙዎቹ ነገ ከአንተ ጋር አይቆሙም! ጥለውህ ነው የሚሸሹት::
ስለዚህ ለማንም ብለህ ልጆችህን ሆነ እራስህን በዚህ በማይመለከትህ ጦርነት እንዳታቃጥል፤ ጥንቃቄ ማድረግ አለብህ!  እስከ አሁን ባለፉት ዓመታትና ወራት በቂ ትምህርት ተገኝቷል! ከአሁን በኋላ ተጨማሪ ደም ማፍሰስ የለብህም! እስከአሁን የከፈልከው ደም ይበቃል!
በዚህ ሰሞኑን በተካሄደው የመልሶ ማጥቃት ጦርነት፤ በታሪካችን አይተነው የማናውቅ ዕልቂት አሳይቶናል:: ቁጥር ስፍር የሌለው ልትቆጥረው የሚታክት የኢትዮጵያ ሰራዊት ሞቷል:: በካሜራ የቀረፅነው ቢሆንም፤ በሚዲያ ለማስተላለፍ ለህሊና የሚከብድ፤ ሰብአዊ ኪሳራ ነው የደረሰው::
በረዥሙ ዕድሜ የጦርነት ልምዴና ታሪኬ፤ አይቼውም ሆነ ሰምቼው የማላውቅ፤ ሊያጋጥም ይችላል ብየ የማልገምተው ዓይነት፤ ሰብአዊ ኪሳራ ነው ጠላት የከፈለው::
ይህ ዕልቂት የእኛ ሰራዊት በጦርነት የገደለው ብቻም ሳይሆን፤ የጠላት ሰራዊት ሲፈርስና ሲበተን፤ አዛዦቹ ከኋላ ባዘጋጁት ሓይል የጨፈጨፉት ሜዳ ሙሉ ሬሳ ነው:: እነዚህ በከንቱ የረገፉት ልጆችህ ናቸው! ተጨማሪ ኪሳራ አትክፈል!”
ለኢትዮጵያ ሰራዊት ያስተላለፉት መልእክት፦
“ይበቃሃል! ይህንን ጦርነት ማስቆም አትችልም! አብቅቶለታል! አንተም ሆንክ ማንም ሊያስቆመው አይችልም!
ከአሁን በኋላ የምትከፍለው የህይወት ኪሳራ፤ ማንም የማይዘክረውና የማያስታውሰው፤ እንደ ደርግ ሰራዊት በየአካባቢው ‘ነበረ’ ነው የምትባለው!  ስለዚህ ለማንም ብለህ ተጨማሪ ሞት አያስፈልግህም! ይህንን መልእክት ልብ ብለህ ስማ!! አመሰግናለሁ!”
የትግራይ ኮሙኒኬሽን ቢሮ
07   ጥቅምት 2014 ዓ/ም
መቐለ
Filed in: Amharic