>

የዛሬው የእነ እስክንድር ችሎት ውሎ … በወፍ በረር !! (ዘመድኩን በቀለ)

የዛሬው የእነ እስክንድር ችሎት ውሎ … በወፍ በረር !!

ዘመድኩን በቀለ
 
*… ወንድሜ …” እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ!!
እስክንድር ነጋ
… ዐቃቤ ሕግ በእስክንድር ነጋ ላይ ከሚመሰክሩለት 22 ተከሳሾች መሃል የመጀመሪያ መስካሪውን የተባለውን ምስክር ይዞ ቀርቧል።
የመስካሪው ስም፦ ፈንታሁን አሰፋ ደበሌ
ጾታ፦ ወንድ
ብሔር፦ አልተጠቀሰም።
አድራሻ፦ ል/ክ/ከ
ወረዳ፦ 5
የቤ/ቁ፦ 538
… ምስክሩ መጽሐፍ ቅዱስ ጨብጦ፣ ምሎ፣ ተገዝቶ ምስክርነቱን መስጠት ጀመረ። በማስክ ተሸፋፍኖ ስለነበረም በእነ እስክንድር ጥያቄ በዳኞች ትእዛዝ ማስኩን አውለወቆ ለእነ እስክንድርም ለተመልካቹም ለችሎቱ ታዳሚዎች ዙሮ ታይቶ ቀጠለ።
• እስክንድር ነጋን የማውቀው በ2005 እና በ2006 ዓም ቃሊቲ ታስረን በነበርንበት ወቅት ነው።እዚያ ነው እስክንድርን የማውቀው።
• ቆይቶም ይኸው ምስክር የቀደመውን የቃሊቲ እስርቤት የትውውቅ ጊዜ ዘንግቶ ” እስክንድርን የማውቀው በ1997 ዓም ነው።” አለ።
• ቀይቶ መልሶ “እስክንድር ነጋን የማውቀው በ2005 እና በ2006 ዓም ቃሊቲ ታስረን በነበርንበት ወቅት ነው አለ።
• ከእስርቤት ከወጣን በኋላ እስክንድርን ለመጀመሪያ ጊዜ ያገኘሁት እስክንድር ፈረንሳይ ለጋስዮን ጫማውን እያስጠረገ ሳለ በድንገት ነው። ከዚያ መቼ ተፈታህ ብሎ ጠይቆኝ ተለያየን።
• ምስክሩ ዐቃቤ ሕግ እየመራው ምስክርነቱን መስጠቱን ቀጥሏል።
• ቆይቶ ደግሞ እንዲህ አለ። እኔና እስክንድርን ያስተዋወቀን አሸናፊ የሚባል ጋደኛዬ ነው። የቃሊቲውም፣ የ1997 ዓም ትውውቃቸውንም ረስቶ መሆኑ ነው። አሸናፊ የሚባል ጓደኛዬ ነው ያስተዋወቀን አለ። (አሸናፊ ማለት ከእነ እስክንድር ጋር ተከስሶ ዐቃቤ ሕግም ፎቶውም፣ አድራሻውም የለኝም ብሎ ክሱ የተቋረጠለት ሰው ነው) እናም ምስክሩ ይሄን ዐቃቤ ሕግ አላውቀውም ያለውን ሰው ነው ጓደኛዬ ነው የሚለው። እናም ከአሸናፊ ጋር ሆነን እስክንድርን አራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገኘነው። በቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ በተጋደመ የዛፍ ግንድም ላይ ለረጅም ሰዓት ተቀምጠን ከእስክንድር የጥፋት ተልእኮ ተቀበልን። የተቀበልነው ተልእኮም።
• አንደኛ ሞጣ ሄደን ወታደራዊ ሥልጠና ወስደን እንድንመጣ፣
• ሁለተኛ ታከለ ኡማን እና ሌሎች የመንግሥት ባለ ሥልጣናትን እንድንገድል፣
• ሦስተኛ አራዳ ጊዮርጊስን ጨምሮ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ጋር የሚገኘውን መስጊድ እና ሌሎች የሃይማኖት ተቋማትን እንድናቃጥል እስክንድር ራሱ ለእኔና ለአሸናፊ ተልእኮ ሰጠን። ለዚሁም 5 ሺ ብር በአሸናፊ በኩል ራሱ እስክንድር ብር ሰጠን። (ቀብድ መሆኑ ነው።)
• ሞጣም ሄደን ሳንሰለጥን ተመለስን፣ በኋላ እኔ ከአሸናፊ ጋር ተጣልቼ አሸናፊ ሽጉጥ ተኩሶ ሁላ ሳተኝ። አሸናፊን ከስሼው ከጓደኞቼ ጋር ሁሉ ቤቱ ሄደን አጣነው። እናም ይሄንና ይሄን የመሰለውን ምስክርነተቱን ሰጥቶ አጠናቀቅቋል።
… ዳኛው የመጨረሻ ጥያቄ ለምስክሩ አቀረበ። ከእነዚህ ከተከሳሾች መካከል እስክንድርን ታውቀዋለህ? ለይተህም ልታሳየን ትችላለህ? (በሳቅ…) እስክንድር ነጋን መስካሪው ሳያውቀው እንዲሸወድ መሆኑ እኮ ነው። መስካሪው ደረቱን ነፍቶ እየተንጎማለለ ሄዶ አዎ አውቀዋለሁ በማለት በእስክንድር ፊቱ ላይ ተጠግቶ አይኑን በማጉረጥረጥ ይሄ ነው አለ። የአባቱ ስም ማነው? ቀጣይ የዳኛው ጥያቄ ነው። ነጋ ነው። አስክንድር ነጋ።
… ምስክርነትህን ጨርስሃል። ሁለተኛውን ምስክርነት ከእረፍት በኋላ እንሰማለን በማለት ዳኞቹ ችሎቱን ለእረፍት አቆሙት።
… ፖሊሶቹም ምስክሩን ፎቶ እንዳይነሣ በመጋረጃ የመጠቅለል ያህል ጠቅልለው ወደ ውጭ አወጡት። በዚህን ጊዜ እስክንድር ድምጹን ከፍ አድርጎ ምስክሩን እንዲህ አለው።
ወንድሜ …
• ” እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ  !!
• ” እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ  !!
• ” እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ  !!
… እስክንድር ክርስቲያን ነው። ጥንቅቅ ያለ ክርስቲያን። ያውም የተዋሕዶ ልጅ። ባለ ማዕተብ። እናም በሀሰት መስክረው የሰቀሉት ጌታውን የሚያውቅ። በመስቀል ላይ ሳለ ጎኑን በጦር እየወጉ፣ የእሾህ አክሊል ደፍተው በግርፋት ደሙ እንደጅረት ውኃ እስኪፈስ፣ ሥጋውም ተበጣጥሶ አልቆ አጥንቱ እስኪታይ ድረስ የገረፉትን፣ በሃሰት መስክረው የሰቀሉትን አይሁድ በመስቀል ላይ ሆኖ ” አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው።” ያለ ጌታ ለገዳዮቹ ምህረት የለመነ ጌታ መድኃኔዓለም ክርስቶስን አምኖ የሚከተል በክርስቶስ ክርስቲያን ተብሎ የሚጠራ ክርስቲያን ስለሆነ የአምላኩን ቃል ዛሬ ደገመው።
ወንድሜ …
• ” እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ  !!
• ” እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ  !!
• ” እግዚአብሔር ይቅር ይበልህ  !!
… እስክንድር ማለት ይሄ ነው። ሐዋርያ፣ ሰማዕት፣ የነፃነት ታጋይ፣ ይቅር ባይ፣ በሕግ በሥርዓት የሚያምን፣ ለሌሎች ምቾት እሱ ተጎሳቅሎ የሚኖር፣ ጥርት ያለ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች፣ ምን ያደርጋል ታዲያ እስክንድር ዐማራና ኦርቶዶክስ መሆኑ ጎዳው። ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን መውደዱም ዋጋ እያስከፈለው ነው። የሌላው በደልና ግፍ ሳይቆጠር የዐቢይ አሕመድን መንግሥት በእስክንድር ነጋ ላይ እየፈጸመ ያለው ግፍ እመቀዕመቃት ያወርደዋል።
• ኃይል የእግዚአብሔር ነው  !!
• ድል ለዲሞክራሲ  !!
… የሌሎቹም ምስክርነት እንዲሁ እየተዘገበ ይቀጥላል። መስካሪው ፈንታሁን አሰፋ ደበሌ ግን ማነው?
“እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።”  ማቴ 5፥45
ክፉ የሚለውን ቃል ለመፍታት መዝገበ ቃላት ማገላበጥ አይጠበቅብንም ብዬ አምናለሁ ምን የሚሰራ ሰው ክፉ እንደሚባል እናውቃለን ክፉ ተደገርጎብን ያውቃል፤ በተለይ ያደረገብን ሰው በእኛም ላይ በሌላም ሰው ላይ ሁሌ የሚያደርግ ከሆነ ክፉ ነው እከሌ ልንለው እንችላለን በምድራችን ላይ ክፉ የምንላቸው ብዙ ሰዎች አሉ ቅንነት የሚባል የሌላቸው፣ ዘር አብቅሎ እንደማያውቅ ድንጋያማ መሬት ደግነት የሚባል የማያውቁ አሉ እግዚአብሔር ግን ለእነዚህ ሰዎች ፀሐይ አይገባቸውም ብሎ አልከለከላቸውም የተጠቀምንበትን የውሀ ሂሳብ ካልከፈልን ውሀው ይቆረጣል ክፉዎች ክፉ ሆነው ባይታዘዙትም ፀሐይን ግን አልከለከላቸውም ማለዳ ፀሐይዋን የሚያወጣት ለክፉዎችም ለበጎዎችም ነው ለሰው ልጅ ፀሐይ አስፈላጊ ናት አስፈላጊዋን ፀሐይ ለክፉውም በየቀኑ ይቸረዋል ፈጣሪ ቸር ነውና ሰው ምንም ክፉ ቢሆን እግዚአብሔር ግን ቸርነት ማድረጉን አይተውም ለክፉ ሰው እንኳ ሳይቀር ቸርነቱን ያደረጋል ለክፉው እንኳ ፀሐይን የሚያወጣለት አምላክ ስሙን ለምንጠራ ለእኛማ እንዴት ቸር ነው!!! በየዕለቱ ፀሐይ ትወጣለች ስለ ለመድናት እንዲሁ የምትወጣ ሳትሆን የሚያወጣት እግዚአብሔር ነው በየዕለቱ ለክፉዎችም እንደ በጎዎቹ ሁሉ ፀሐይን ያወጣታል እግዚአብሔር ክፉ ለሰሩበት መቅጣት ብቻ ሳይሆን ቸርነቱንም እንደሚያደርግ ያሳየናል የእግዚአብሔር ቸርነት በኛ በልጆቹ ላይ ደግሞ እንዴት ተትረፍርፎ እንዳለ ማየት ይቻላል ስለዚህ በድካማችንም ሰዓት ተስፋ አንቆርጥም፤ ከኛ በጎነት ቢታጣ በምሕረቱና በቸርነቱ ተስፋ እናደርጋለን በሆነ ምክንያት የምንበላውን ማሰናዳት ባንችል ወዳጀጆቻችን ወደ ሆኑት ጎረቤቶቻችን በመሄድ የምንዋሰው እንጀራ ላናጣ …!
Filed in: Amharic