አቻምየለህ ታምሩ
ሕወሓት የሚባለው የወንጀል ድርጅት እንደ ፋሽስት ድርጅት የተፈጠረው በአማራ መቃብር ላይ ታላቋን የትግሬ ሪፑብሊክ ለመመስረት ነው። ይህ የቅሚያ፣ የግድያ፣ የዘረፋና የወረራ ድርጅት ዛሬ በአማራ ሕዝብ ላይ እየፈጸመ የሚገኘውን የጅምላ ፍጅት፣ ውድመትና የዘር ማጥፋት የጸነሰው፣ ለመፈጸመ ፕሮግራም ቀርጾ ወደ ጫካ የወረደውና ዛሬ በአማራ ላይ የጅምላ ፍጅት እያካሄዱ የሚገኙ ተከታዮቹን “ገድሊ ማለት አምሓራይ ምቅታል ማለት እዩ” ወይም «ትግል ማለት አማራን መግደል ነው» እያለ ያሰለጠነው ዐቢይ አሕመድ ከመወለዱ በፊት ነው።
ዐቢይ አሕመድ ከመወለዱ በፊት አማራን እንደ ሕዝብ ማጥፋትን እንደ ትግል አላማና ግብ ይዘው ጫካ የወረዱትን ወሮበሎችና በመንግሥትነት ተሰይመው በኖሩባቸው ዘመናትም አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ያልፈጽሙት የወንጀል አይነት በመብራት ተፈልጎ የማይገኝላቸውን አለማቀፍ ወንጀለኞች ባለፉት ጥቂት ወራት በግፍ በወረሯቸው የወሎና የጎንደር አካባቢዎች የሚያካሂዱትን በፕሮግራም የታገዘ የቤት ለቤት የጅምላ ፍጅት፣ የዘር ማጥፋት፣ ዘረፋና ውድመት ዐቢይ አሕመድን ከሥልጣን ለማውረድ በሚፈልጉ ፋሽስት ወያኔዎችና እንዳይወርድ በሚከላከሉት አማራዎች መካከል የተፈጸመ አድርጎ ማቅረብ ተራ የፋሽስ ወያኔን talking point ማስተጋባት ብቻ ሳይሆን ከወራሪው የፋሽስት ወያኔ አንበጣ ሠራዊት ጎን በመቆም ይህ ግፈኛ የፋሽስት ወያኔ ወራሪና ዘራፊ ሠራዊት በግፍ በወረራቸው የወሎ፣ የጎንደርና የአፋር አካባቢዎች እያካሄደ ያለውን እልቂት፣ ፍጅትና ውድመት መደገፍም ጭምር ነው።
In all, Meaza’s bizarre and robotic repetition of TPLF’s talking point on the criminal enterprise’s invasion of Gondar, Wollo, and Afar and its devastating and genocidal war is tantamount to justifying the industry-scale vandalization, destruction, and genocide committed by fascist TPLF against civilian Amharas and Afars in the north.