>
5:13 pm - Monday April 19, 0151

ሀገሬ...! ወዴት ነሽ !? (ዘምሳሌ)

ሀገሬ…!ወዴት ነሽ !?

 ዘምሳሌ


ሀገሬ አለሽ ወይ ኢትዮጵያ ወዴት ነሽ
ጠፋሽኝ ተስፋ አጣሁ የት ነው የማገኝሽ
እስኪ አለሁ በይኝ  ካለሽበት ሆነሽ
አካልሽ ተከፍሎ በስም ብቻ ቀርተሽ

አለሽ ሆይ ኢትዮጵያ  በህብር  ቁመና
መልካም በነበረ ው  የአንድነቱ ፋና
ስምሽ ብቻ  ቀርቶ ወጥቶ   ከጎዳና
አፍቃሪ  ልጆችሽን አሳጥቶ መና

ኢትዮጵያ  ያንቺ  ዕጣ  የማይሆነው  በጎ
ለበዪ የዳረገሽ  ህዝብ ለእልቂት ዳርጎ
ጓዳ እርቃንሽን እንድትቀሪ አድርጎ
የከረመ  አጋችሽ  በእብሪቱ  ባልጎ

ኢትዮጵያ  መች ይሆን የሰላም ዘመንሽ
አንዱ አንዱን ማይገለው ህግ ሚሰፍንብሽ
ልጆችሽ በሰላም ወጥተው ሚገቡብሽ
በፍቅር በምርጫ  መሪ ሚመርጡልሽ

ደጉ ጊዜ ሲርቅ ተስፋው የህዝብሽም
ርሀብ እርዛቱ ስደት ሆኖ የትም
አንዱ በሌላኛው ወንድሙ ሲቃወም
የእልቂቱ ጊዚያት ማያባራው ዘላለም

ኢትዮጵያ መች ይሆን የሰላምሽ ቀኑ
ህዝብሽ ሚነጋለት ሚያቆም መባከኑ
ልቡ ሚመለስበት  ሚቀር ማባነኑ
ሀብት ልማትሽን ማቃጠል ማትነኑ

ደገኛው አመትሽ ከተፍ የሚልበት
ብርሀን የሚሆነው የሚጠፋው ፅልመት
እንዴት ይናፍቃል ለሚወድሽ በእውነት
ሀገሬ ለሚያይሽ አሁን ባለሽበት

ሀገሬ አለሽ ወይ ወዴት ነው ያልሽው
ባጥፊ ገዳዮችሽ ቅርቃር የገባሽው
ህዝብሽን ተሰዳጅ አሳዳጅ ያረግሽው
ወደጥንቱ አቋምሽ የማትመለሽው
ወጥተሽ  የወረድሽው ኖረሽ የሌለሽው
ወጥተን እንፈልግሽ  ወዴት ነው ያልሽው?

Filed in: Amharic