>

ዉሻ ወደ ትፋቱ ...???  (ሸንቁጥ አየለ)

ዉሻ ወደ ትፋቱ …??? 

ሸንቁጥ አየለ

ያሬድ ጥበቡ ድሮም ቢሆን የህዉሃት ጆከር እንደነበረ ብዙ ጽፈናል። እንዴዉም አንዳንድ እንኩቶ የአማራ ብሄረተኛ ነን ባዮች  ከያሬድ ጥበቡ ጋር አዲስ ፓርቲ ሊያቋቁም ሰነድ መስራት ጀምረዉ ያሬድ ጥበቡንም በአስራት ሚዲያ ሳቀር ሲያጯጩሁት ነበር።   በወቅቱ ከያሬድ ጥበቡ እንዲርቁ የሞገትናቸዉ ሰዎች ታዲያ ዛሬ ያሬድ ጥበቡ ከወያኔ ወገነ ብለዉ አልቃሽ ሆነዋል። ዋሸሁ እንዴ? ይላል ነገረኛ ተራቢ።
2. ታምራት ላይኔ የህሊናዉ ፍርድ ትክክለኝነት አጠራጣሪ ነዉ።አማራን አሁን በለዉ ግደለዉ ብሎ በአደባባይ የተናገረ ሰዉ የባህሪና የህሊና ለዉጥ ያመጣል ብሎ መጠበቅ ትልቅ ጅልነት ነዉ።
 3ኛ. ልደቱ አያሌዉ ሶስተኛ አማራጭ በሚል ፍልስፍናዉ ከጀዋርም ከህዉሃትም ቁጭ ብዬ ስለለፈለፍኩ እደመጣለሁ ብሎ የሚያስብ  ብልጣብልጥ ፖለቲከኛ ነዉ።  ልደቱ ለመለስ ዜናዊ የፓርላማ ድምቀት ጥሩ አጫፋሪ እንደነበረዉ አሁንም በተደራዳሪነት ይሄንኑ ሚና ለመጫወት መወሰኑ ዉሻ ወደ ትፋቱ ያስብላል።
 ወያኔዎች እንደሆኑ ድርድር ቅብጥርስ የሚባለዉ ነገር አይሰሙህም። ድርድር ቅብጥርስ ለነሱ በነሱ ህግ እስከተጫወትህ ብቻ ነዉ። ልክ ኦነጋዉያንን እንደሚያደርጉት ሁሉ ፈረስም ጋሪም ሁን ሲሉህ የወያኔን ትዛዝ እየተቀበልክ መሬት ከላስክ ከነሱ ጋር ስለ ድርድር መነጋገር ትችላለህ።
 የኢትዮጵያ ህዝብ በተለዬም የአማራ ህዝብ በዚህ ጦርነት ጠላቶቹን ሁሉ ደምሦ አሸናፊ ሆኖ ካልወጣ በቀጣይ እልል ያል የሽምቅ ዉጊያ ዉስጥ ገብቶ በማንኛዉም መንገድ ጸረ አማራ ትርክቶች ሁሉ ከኢትዮጵያ ምድር ተነቅለዉ ሲጣሉ ብቻ እንደ ሰዉ ልጅ መቆም ይችላል።ኢትዮጵያን ማዳን የሚቻለዉ የታመነ እና ከሁሉም ጠላት ጋር ገጥሞ ጠላት አፈር የሚያግጥ ጉልበት ሲኖር ብቻ ነዉ።
 በኣጭሩ አሁን ልደቱ፡ ያሬድ ታምራት ላይኔ  እያደረጉት ያለዉ.  ከወያኔ ጋር የወገነ ስራ  ዉሻ ወደትፋቱ የሚባል አካሂያድ ነዉ።
Filed in: Amharic