>

“የምንፈልገው እኛ ሞተን የምትቆይ ኢትዮጵያን ማየት ነው...!!!" (ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ)

“የምንፈልገው እኛ ሞተን የምትቆይ ኢትዮጵያን ማየት ነው…!!!”
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ሰራዊት በአፋር ግንባር የሚገኙትን ጭፍራ እና ቡርቃን በዛሬው ዕለት እንደሚይዝ ተናገሩ። ሰራዊቱ በዚያው ግንባር የሚገኘውን የካሳጊታን አካባቢ መቆጣጠሩን አስታውቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት፤ በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ዛሬ አርብ ከሰዓት በሰበር ዜና በቀረበ መልዕክታቸው ነው። የወታደራዊ የደንብ ልብስ ለብሰው በቴሌቪዥን የታዩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ አብረዋቸው የሚገኙት የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት “ከፍተኛ ድል” ማስመዝገባቸውን ተናግረዋል።
“የምንፈልገው እኛ ሞተን የምትቆይ ኢትዮጵያን ማየት ነው። የምንፈልገው ወይም ኢትዮጵያዊ መሆን ነው፤ ወይም ኢትዮጵያ መሆን ነው። ይሄን ደግሞ በድል እንደምናሳካ እርግጠኛ [ነን]” ያሉት አብይ፤ ለዚህም ህዝቡ ከጎናቸው መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።
ሰበር ዜና‼
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ግንባር ሆነው ያበሰሩት ድልና ያስተላለፉት መልዕክት…‼
. ከእኔ ጀርባ የምታዩት ጠላት እስከትናንትና ድረስ ሙሉ በሙሉ የያዘው ተራራ ነው፤ ዛሬ አስለቅቅናል፤
. ካሳጊታን ይዘናል ዛሬ ጭፍራንና ቡርቃን እንይዛለን፤
. የሰራዊቱ ሞራል እጅግ ደስ ይላል፤ ጦርነቱ በከፍተኛ ድል  ነው እየተከናወነ ያለው፤
. የኢትዮጵያ ነጻነት እስኪረጋገጥ ወደኋለ አንልም፤
. የምንፈልገው እኛ ሞተን የምትቆም ኢትዮጵያን ማየት ነው
. የምንፈልገው ኢትዮጵያዊ መሆን አሊያም ኢትዮጵያ መሆን ነው፤
. ሁሉንም በድል እንደምናሳካ በጣም እርግጠኛ ነኝ፤
. ህዝብችን ከጎናችን ነው፤
. በውጭ ያሉ ወገኖቻችን ባላቸው አቅም እየጮሁ ነው፤ የእኔ ስራ ደግሞ በግንባር ሆኖ ጦርነቱን መምራት ነው፤
. በጣም ትላልቅ ድሎች አሉ፤ ይቀጥላል፤
. ጠላት ከእኛ ጋር ሊስተካከል የሚችል ቁመና የለውም እናሸንፋለን፤
. ነጻ የበለጸገች ኢትዮጵያን ለልጆቻችን እናሸጋግራለን፤ ውጤቱ በጣም ጥሩ ነው በርቱ
የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፤ ወደ ጦር ሜዳ ለመሄድ መወሰናቸውን ያስታወቁት ባለፈው ሰኞ ህዳር 13፤ 2014 ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ጦር ግንባር መሄዳቸው ከተነገረ በኋላ በቴሌቪዥን ሲታዩ የዛሬው የመጀመሪያቸው ነው።
Filed in: Amharic