>

የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ ተሰረዘ...!!! (ኢ ፕ ድ)

የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ ተሰረዘ…!!!
ኢ ፕ ድ

*…… አገር ለማፍረስ በድብቅ ሲወያዩ የነበሩትን የእነ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሀቅ፣  ኢሌኒ ገብረመድህ፣ አሸባሪው ብርሀነ ገብረክርስቶስ እና አጋሮቻቸውን ውይይት ያዘጋጀው የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ ተሰረዘ
ሰሞኑን አገር ለማፍረስ በድብቅ ሲወያዩ የነበሩትን የእነ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሀቅ፣  ኢሌኒገብረመድህ፣ አሸባሪው ብርሀነ ገብረክርስቶስ እና አጋሮቻቸውን ውይይት ያዘጋጀው የሰላም ልማት ማዕከል ፈቃድ ተሰረዘ።
ይህ ማዕከል ሰሞኑን በፕሮፌሰር ኤፍሬም አወያይነት የቀድሞ የአሜሪከ አምባሳደሮችና የአሸባሪው ህወሓት አባላትና የጥቅም ተጋሪዎች የተካሄደውንና ኢትዮጵያን የማፍረስ ውይይት አዘጋጅቷል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 9 መሰረት፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ የሀገርን ህልውናና ሉዓላዊነት እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፤  በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ የሚጠረጠር የሲቪል ማህበር ድርጅትን ፈቃድ እንዲሰረዝ ያዛል በሚለው መሰረት   የሰላም ልማት
 ማዕከሉ ፈቃድ ተሰርዟል።
የሲቪል ማህበረሰቦች ባለስልጣን ለኢፕድ ባደረሰው መረጃ መሰረት
የማዕከሉ ፈቃድ ከዛሬ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ. ም ጀምሮ  ተሰርዟል።
Filed in: Amharic