>
5:13 pm - Tuesday April 20, 5717

"አሜሪካ የኢትዮጵያ ጦርነት ካልኩሌሽን ላይ ልክ እንደ አፍጋኒስታን ስህተት ፈፃማለች!!" (የቀድሞ የአሜሪካ ጄኔራል)

“አሜሪካ የኢትዮጵያ ጦርነት ካልኩሌሽን ላይ ልክ እንደ አፍጋኒስታን ስህተት ፈፃማለች!!”
የቀድሞ የአሜሪካ ጄኔራል

 

*…. አሜሪካ ሕወሓት አ.አ በቀናት ውስጥ ሊገባ ስለሆነ ከኢትዮጵያ ለቃችህ ውጡ በሚል የራሷን እና ወዳጅ ሀገራትን ዜጎቿን አጣድፋ ማስወጣቷ ሌላው ትልቅ የተሳሳተ ስሌት ነበር! የሕወሓት ግስጋሴ ተቀልብሶ ነገሮች በተቃራኒው ሆነዋል!!
     –
ትውልደ ሊባኖሳዊ አረብ የሆነውና በአሜሪካ ሰራዊት ስመጥር በመሆን ሲያገለግል ቆይቶ ከ8 አመት በፊት ጡረታ የወጣው General Juhun Abi Zayd እንዳለው፤ አሜሪካ በተለያዩ ሀገራት በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጦርነት ካልኩሌሽን ችግር እየሠራች ነው በሚል የኢራቅን አፍጋኒስታን እና የኢትዮጵያን ጦርነት በምሳሌነት ጠቅሷል። ሰፊ እቅድ ይዞ አፍጋኒስታን የገባው የአሜሪካ ጦር አፍጋኒስታን ላይ ተሸንፎ ወጣ።  ኢራቅና ሶርያ ላይም ተመሣሣይ እጣ እየገጠመው ይገኛል ብሏል።
የአሜሪካ ሰራዊት ከአፍጋኒስታን ሲወጣ ታሊባን ካቡልን ለመቆጣጠር ከአመት በላይ የሆነ ጊዜ ይወስድበታል የሚል ስሌት የአሜሪካ ጄኔራሎች ሰርተው ለፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አቅርበው ነገር ግን ታሊባን ካቡል የገባው በ 5 ቀን ፈጣን ውጊያ እንደነበር ያስታውሳል።በዚህም የተነሣ አላስፈላጊ ጥፋቶች ደርሰዋል። አብዛኛው የአሜሪካ ሠራዊት መሣርያ በታሊባን ተማርኳል።
ሌሎች ተመሣሣይ ምሳሌዎችን ያነሣና ከ 3 ሳምንት በፊት አሜሪካ ሕወሓት አአ በቀናት ውስጥ ሊገባ ስለሆነ ከኢትዮጵያ ለቃችህ ውጡ በሚል የራሷን እና ወዳጅ ሀገራትን ዜጎቿን አጣድፋ ማስወጣቷ ሌላው ትልቅ የተሳሳተ ስሌት ነበር ይላል። አሜሪካ ይህን ካለችበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ግን ሕወሓት የለቀቀው እንጂ ያስለቀቀው ስትራቴጂካዊ ቦታ እንደሌለ ጠቅሶ የጦርነቱን የወደፊት ገፅታ በሚወስን መልኩ በአፋር ግንባር ከባድ ሰብአዊና የማቴሪያል ኪሳራ ገጥሞታል። በምእራብ ግንባርም ተመሣሣይ ክስተት ገጥሞታል። የኢትዮጵያ ሠራዊት የመሬትም የአየርም የበላይነት ይዞ ወደ መቀሌ የሚያመሩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ጀምሯል ብሏል።
ስለሆነም የሕወሓት ግስጋሴ ተቀልብሶ ነገሮች በተቃራኒ ሆነዋል። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ጨዋታ ቀያሪዎች ድሮኖች(በተለይ የቱርክ) እና የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ንቅናቄ ናቸው። የአሜሪካ ጦር ባለሙያዎች ካልኩሌሽን ግን እነዚህ ሁለት ጉዳዮችን ያላከተተ ስለነበር ጄኔራሎቹ ተሳስተው መንግስቱንም አሳሳቱት ይላል። የአሜሪካ ጦርነት ቀማሪያን እና ባለሙያ ነን የሚሉ አካላት ለወደፊት ነገሮችን በአግባቡ ያላገናዘበ ካልኩሌሽን ከመስራት ቢታቀቡ የተሻለ ነው ሲል መክሯል።
ምንጭ_ Vice world news
Filed in: Amharic