>

‹‹የጋሸና በወገን ጦር መያዝ ቀሪ አካባቢዎችንም ለመያዝና ውጊያውን በበላይነት ለማጠናቀቅ ያግዛል››  -ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ 

‹‹የጋሸና በወገን ጦር መያዝ ቀሪ አካባቢዎችንም ለመያዝና ውጊያውን በበላይነት ለማጠናቀቅ ያግዛል›› 
-ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ 
***********************
(ኢ ፕ ድ)

ጋሸና ወታደራዊ እስትራቴጂ ቦታ እንደመሆኑ  በወገን ጦር መያዙ ቀሪ አካባቢዎችንም ለመያዝና ውጊያውን በበላይነት ለማጠናቀቅ እንደሚያግዝ ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ንጋቱ ገለጹ፡፡
ብርጋዴል ጀነራል ዋሲሁን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በውጊያ ጊዜ ለግዳጅ መሳካት ጠቃሚ የሆነ ቦታ መያዝ የግድ ያስፈልጋል፡፡ ጠላት ጋሸናን ለመያዝ የፈለገበት ዋና ምክንያትም ወታደራዊ መሬት በመሆኑ ነው፡፡
ወታደራዊ እስትራቴጂ ቦታ እንደመሆኑ ያንን ቦታ ማስለቀቁ ለወገን ጦር በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ አካባቢው ከተያዘ በኃላ ደግሞ በትክክለኛ መረጃ ለማጥቃት ያግዛል፡፡
ሞራል የሚሰጥ በመሆኑም ጋሸና መያዝ ለወገን ጦር ጥቅሙ ከፍ ያለ ነው፡፡ ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለልዩ ሃይሎችና ለሚሊሻዎች የመዋጋት ሞራልን ይሰጣል፣ ቀሪ አካባቢዎችንም ለመያዝና ውጊያውን በበላይነት ለማጠናቀቅ ያግዛል፡፡ የድል ልዕልናን ያጎናጽፋል፡፡
ለሽፍታው፣ ለአመጸኛውና ለወንበዴው የህወኃት ቡድን ጋሸናን መልቀቁ ከፍተኛ ጉዳት ነው ብለዋል፡፡
በጋሸና ግንባር  ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ሀይል ሚሊሻና ፋኖ በጥምረት ባደረጉት ተጋድሎ የአርቢትን፣ የአቀትን፣ የዳቦና የጋሸና ከተሞችን ነጻ ማውጣቱ ዛሬ መገለጹ ይታወቃል።
በዚህ ግምባር  ጠላት ለበርካታ ወራት የዘረፈውን ሀብት  በመጠቀም በወረራ የያዘውን አካባቢ ህዝብ በማስገደድ ያሰራውን ባለብዙ እርከን ኮንክሪት ምሽግ በተቀናጀ እቅድ፣ አመራርና ቴክኖሎጂ በመታገዝ በአነስተኛ መስዋዕትነት ምሽጉ መሰበሩንና ጦሩ በላሊባለ፣ ወልዲያና ወገል ጤና አቅጣጫ በአሁኑ ሰአት ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን የመንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ዛሬ ማብሰራቸውም አይዘነጋም።
በዘለላም ግዛው
Filed in: Amharic