>

"አርበኛ ዘመነም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም 'ሃገር ለማዳን ነው ጦር ሜዳ የወረዱት የእኩል ሚዛን ሊኖረን ይገባል...!!!" መስከረም አበራ

“አርበኛ ዘመነም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይም ‘ሃገር ለማዳን ነው ጦር ሜዳ የወረዱት የእኩል ሚዛን ሊኖረን ይገባል…!!!”
መስከረም አበራ

*… “የመንጋው ጋጋታ እና የጅምላ ፍረጃ የትም አያደርስም!!!”
ኢትዮጵያ ቱ ዴይ
“አሁን ዋና ትኩረታችን መሆን ያለበት ሃገራችን ከውስጥም ከውጭም የተቃጣባትን ሁለንተናዊ የህልውና አደጋ መቀልበሱ ላይ ነው፤ ሌላው ሃገራችን መትረፏን ካረጋገጥን በኋላ ይደርሳል” የሚለው ተገቢ አቅጣጫ የእኔ ቢጤውን ተራ ሰውም ጉልበታሙን መንግስትም እኩል ሊገዛ ይገባዋል።
 ስለዚህ ባለ ብዙ ጠበቃው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ‘ሃገር ለማዳን የጦር ሜዳ ስለወረዱ በጥያቄ ብዛት አታድክሟቸው’ የሚለው ጥብቅና ሃገር ለማዳን ጦር ሜዳ ለወረዱት እነ ዘመነ ካሴም ሊሰራ ይገባል።ጅንስ እና ሱፉን አውልቆ መለዮ ለብሶ የሚንጎራደደው ዲያስፖራም ሆነ ፖለቲከኛ ፣ጋዜጠኛም ሆነ ካድሬ  ይህን ሊናገር ይገባል! ካልሆነ መለዮ ያስለበሳቸው የመንግስት አዝማሪነት እንጅ ሌላ እንዳልሆነ ገሃድ ይወጣል።  ይሄው ነው!
“የመንጋው ጋጋታ እና የጅምላ ፍረጃ የትም አያደርስም!!!”
ኢትዮጵያ ቱ ዴይ
 አብይን ወይም በእሱ የሚመራወን መንግስት የተቸ ሁሉ በመንጋው ቤት ጁንታ ወይም ሌላ ስም ያሰጠዋል። ሀገሪቱን እየጎዳ ያለው ይሄው አንድ አይነት አስተሳሰብ ወይም እኔ ብቻ አውቅልሃለሁ የሚለው አመለካከት ነው። ሀገሪቱን ማን ይምራ ምን በህዝብ ዘንድ በየአቅጣጫው የሚሰነዘሩ ትችትም ሆነ ገንቢ ሀሳቦችን ተቀብሎ ተግባራዊ የማያደርግ መንግስት እድሜ የለውም፣ ህዶ ህዶ መጨረሻውም አያምርም።
መምህርት እና አክትቪስት መስከረም አበራ በሀሳብ ልእልና የምታምን፣ ህሊናዋ የነገራትን ፊት ለፊት ሳትደብቅ የምትናገር፣ ለጥቅም ወይም ልመወደድ ብላ የማታወራ፣ ለተበደለ ወይም ፍትህ ላጣ ህዝብ የምትቆም ጀግና ሴት ነች።
መስከረም ሁሉ ሰው ለውጥ ለውጥ እያለ ከመንጋው ጋር እየነጎደ ባለበት ወቅት በመተከል፣ በወለጋ ሆነ በሰሜን ሽዋ ያለምንም ጥፋታቸው ለተጨፈጨፉ አማራወች ቀድማ የተናገረች፣ የመንግስት ቸለልተኝነትን የተቸች  ጀግና ነች።
የመተከል ኮማንድ ፖስት ከጨፍጫፊወች ጋር ወግኖ አካባቢውን የደም አሜኬላ ሲያደርገው፤ በሰሜን ሽዋ አጣዬ አካባቢ በወረዳ እና በዞን ባሉ ባለስልጣናት ድጋፍ ጨፍጫፊ እና ገዳዩ ኦነግ ሸኔ አንድ ከተማ ሙሉ ሲያወድም፣ በመቶዎች ሲገድል፣ በመቶ ሺወች ሲፈያናቅል አንዳንድ እንደመስከረም አበራ ያሉ ለህሊናቸው ያደሩ በቀር የአብይን መንግስት የተቸ የለም።
“መስከረም አበራ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይም ፤ ታጋይ ዘመነ ካሴም ወደ ጦር ሜዳ የወረዱት ሃገር ለማዳን ነው” ባለችው ፁህፏ ውርጂብኝ እየደረሰባት ነው። አመዛዝኖ ለሚያስብ ወይም ደግሞ ትችትን እና ገንቢ ሀሳብን ለሚወድ ሰው ሆነ መንግስት ግን ፅሁፉ እንከን የሌለው ነው።
Filed in: Amharic