>

"መረጃ ቲቪ በማን ለምንና እንዴት ከሳተላይት ወረደ....!!!"  (ዘመድኩን በቀለ)

“መረጃ ቲቪ በማን ለምንና እንዴት ከሳተላይት ወረደ….!!!”
ዘመድኩን በቀለ

“…የሆነው እንዲህ ነው…
“…የዐቢይ አሕመድ (ዶር) መንግሥት የፈረንሳይ መንግሥትን ጠየቀ። ወተወተ። ተማጸነ። በፈረንሳይ መንግሥት ድርጅቶች ስር በተቋቋመው የሳታላይት ጣቢያ ላይ የአየር ሰዓት ገዝተው የሚጠቀሙትን እነዚህንና እነዚያን ድርጅቶች በሙሉ አስወርዱልኝም ብሎ አመለከተ።
ከሚወርዱት ጣቢያዎች መካከልም የመረጃ
ቴቪ አንደኛው ሆኖ ተገኘ። …የሳታላይት ጣቢያው ባለ ሥልጣናትም ደነገጡ። አዘኑም። በአውሮጳ
ያልተለመደ የሚድያ ነፃነትን የሚጋፋ ድርጊት መሆኑን ቢያምኑም ጉዳዩ ከፈረንሳዩ የማርኮን መንግሥት ዘንድ በቀጥታ ትእዛዝ የመጣ ስለሆነ ትእዛዙን
ከመፈጸም በቀር ሌላ አማራጭ አልነበራቸውም። ለሚያከብሩት ለመረጃ ቴሌቭዥን ዋና ሥራ አስኪያጅ ለአንጋፋው ጋዜጠኛ ለአቶ ኤልያስ ክፍሌ
ደወሉለት። የተፈጠረውንም ነገር ሁሉ እያዘኑ ነገሩት። አስረዱት።
• መቼ ነው የምታወርዱት አላቸው?
… አሁን አሉት
• እንደሱማ አይሆንም። አሁን እኔ ከምኖርበት ከተማ ለሥራ ጉዳይ ወጥቼ ነው ያለሁት። ሥራዬን አቋርጬ ልመለስና ለተመልካቾቻችን የተፈጠረውን ሁኔታ
እንድናስረዳ ፍቀዱልን፣ ታገሱን በማለት ጠየቃቸው።
… እሺ ይሁን፣ እስከነገ ምሳ ሰዓት ድረስ ጊዜ እንሰጣችኋለን፣ እንጠብቃችኋለንም ብለው ቃላቸውን ሰጡት።
…ወዲያው ኤልያስ ካለበት ሆኖ ሌሊት ደወለልኝ። ሁኔታውንም ነገረኝ። እናም መረጃ ቴሌቭዥን ከመዘጋቱ በፊት ኤልያስ እንቅልፉን እኔም ድካም ሳይለቀኝ በጠዋት የመጨረሻ ያልነውን መልእክት አስተላልፈን በክብር ከአየር ወርደናል።
የሳታላይት ድርጅቱን ኃላፊዎችም ምስጋና ይድረሳቸው ብለናል።
…እኔማ ኮቴ መናና፣ እግረ ደረቅ የሆንኩ ሁላ እየመሰለኝ መጥቷል። በገባሁበት ሁሉ አውሬው ይቆጣል። ዘንዶው ይጮሃል። ዘንዶ ዩቲዩብ አባሮኛል። ድራሽ አባቴን ነው ያጠፋኝ። አጅሬ ፌስቡክም አባሮኛል። እሱም ድራሽ አባቴን ነው
ያጠፋኝ። መረጃ ቴሌቭዥን ነበር የቀረው እሱንም በፕሬዘዳንት ማርኮን የፈረንሳይ መንግሥት ቀጥተኛ ትእዛዝ ይኸው ዛሬ ከአየር አስወርደውኛል። ድራሽ
አባቴን ነው ያጠፉት። የቀረኝ የራሺያው ፑቲን የቴሌግራም ቻናሌ ብቻ ነው።
እሱን ተቀላቀሉና በዚያ እናወጋለን። በድምጽም በጽሑፍም እንወያያለን።
…አንዱ የመልእክቶቼ መለጠፊያ። አንዱ ደግሞ የመወያያ መድረክ። ሁለቱንም ተቀላቀሏቸው።
…በእኔ በኩል እጅ መስጠት ብሎ ነገር የለም። እኔ የማውቀው ዘወትር አሸናፊ መሆኔን ብቻ ነው። ከማሸነፍ በቀር ሌላ ሁለተኛም፣ አንደኛም ዕድል የሌለኝ፣ አማራጭ የሌለኝ ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጅ ነኝ። እኔ የማውቀው ድል ማድረጌን ብቻ ነው። እኔ የማውቀው ሐሰት ዲያብሎስን መቀጥቀጤን ነው።
እውነት እግዚአብሔርን ማስከበሬን ነው። እኔ የማውቀው ደሀ መበደሉን ፍርድ መጓደሉን ማወጄን ነው። እኔ የማውቀው ዘር ቀለም ሳልለይ ለተጨቆኑ ሁሉ ድምጽ መሆኔን ነው። እኔ የማውቀው ለተገፉ፣ ለታረዱ፣ በግፍ ለታሰሩ ድምጽ መሆኔን ነው። ሃገሬንም ቤተ ክርስቲያኔንም በምችለው አቅም ለመጥቀም፣ ለማገልገል ዊኒጥ ዊኒጥ ማለቴን ነው። እኔ የማውቀው፣ የማምነውም እንደ ዜጋ
ለሃገሬ፣ እንደ አማኝ ለሃይማኖቴ የበኩሌን አስተዋጽኦ የአቅሚቲ ማድረጌን ነው።
በደረኩት ሁሉ ቅንጣት ታህል የሚጸጽተኝ ነገር የለም። ባደረግኩት ነገር የተከፋ፣ የሚከፋም የለም ማለቴም አይደለም። ይኖራል። የትየለሌም ነው። ይሄ ደግሞ ተፈጥሮአዊ ነው። መኖርም አለበት። እኔ አይሞቀኝ፣ አይበርደኝ። ኬሬዳሽ!!!
Filed in: Amharic