>
5:21 pm - Saturday July 20, 0869

"ኦህዴዶች የዘር ማጥፋት ወንጀላቸዉን ሲያከብሩ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ተከበረ ብለዉ ይሳለቃሉ...!!!" (ሸንቁጥ አየለ)

“ኦህዴዶች የዘር ማጥፋት ወንጀላቸዉን ሲያከብሩ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ተከበረ ብለዉ ይሳለቃሉ…!!!”
ሸንቁጥ አየለ

*…. “በኦሮምያ ክልል በሸራተን አዲስ ሆቴል አከበርን” ሲሉህ አዲስ አበባንም መዋጥ መሰልቀጧን እግረ መንገዳቸውን አያረዱህ ነው!!!
 
ላለፉት አራት አመታት ኦህዴዶች ከሸኔ ጋር ተባብረዉ ሌሎች ነገዶችን/ህዝቦችን/ብሄረሰቦችን እየጨፈጨፉ :እያፈናቀሉ ሳያፍሩ ደግሞ የብሄር ብሄረሰብ ህዝቦች ቀን በኦሮሚያ ተከበረ ይሉሃል::
ኦህዴዶች ጋር እፍረት የለም::እነሱ ብቻ ብልጥ የሆኖ ይመስላቸዋል::ወያኔም እንዲሁ እሷ ብቻ ብልጥ የሆነች እየመሰላት ስትዋሽ እና ስታጭበረብር በህዝብ ደም ስትቀልድ ነበር::
ኦህዴዶች በአራት አመት ዉስጥ በሌሎች ነገዶች.ህዝቦች/ብሄረሰቦች ላይ ያደረሱት የዘር ማጥፋት ወንጀል በጥቂቱ የሚከተለዉ ነዉ:
1.በሚሊዮን የሚቆጠሩ የጌዲዮ ማህበረሰብን አፈናቅለዉ ጨፍጭፈዉ በትነዋቸዋል
2.በብዙ አስር ሽህዎች የሚቆጠሩ የሀመር እንዲሁም የልዩ ልዩ የደቡብ ኢትዮጵያ ነገዶችን ከሸኔ/ኦነግ ጋር ሆነዉ ጨፍጭፈዉ አፈናቅለዋል
3.ሻሸመኔ ከተማን ሌሎች ነገዶች የሚኖሩባት እና ሰርተዉ የከበሩባት ብለዉ ሸኔዎች/ኦነጎች ሲያወድሟት በተባባሪነት ቆመዉ ተመልክተዋል
4.በብዙ ሚሊዮን አማሮች ከመላዉ ኦሮሚያ በማፈናቀል:በመጨፍጨፍ እና ሀብታቸዉን በመዝረፍ የማያቋርጥ የዘር ማትፋት ወንጀል ሰርተዋል::
5.አሁንም በወለጋ በመቶ ሽህ አማሮች እና በምዕራብ ሸዋ ደግሞ በብዙ አስር ሽህ አማሮች እየጨፈጨፉ እና እያፈናቀሉ በደስታ ወደ ሰማይ ይዘላላሉ::
6.በመላዉ ኦሮሚያ የብዙ መቶ ሽህ ክርስቲያኖችን ህይወት በማፈናቀል በመግደል ምስቅልቅሉን አዉጥተዉ እና ቤተክርስቲያናትን ያወደሙ ወንጀለኞችን እንደ ጀግና እየሸለሙ በሌሎች ነገዶች ላይ ይሳለቃሉ::
—–
ኦህዴዶች የዘር ማጥፋት ወንጀላቸዉን ሲያከብሩ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ተከበረ ብለዉ ይሳለቃሉ::ኦህዴዶች ከወያኔ ልዩ የሚያደርጋቸዉ ይሄን ወንጀላቸዉን ፊት ለፊት ለሚያጋልታቸዉ ሰዉ የሚሰጡት መልስ ነው::”ምን አለበት ታዲያ ሌሎች ነገዶች ቢጨፈጨፉ?”ይላሉ::ሳያፍሩም “ሀገሩ እኮ የኛ ነዉ” ይላሉ:: “ስለዚህ ጊዜ ሲሰጥህ እንዲህ ማድረግ አግባብ ነዉ::ወያኔስ ብሆን ያደረገዉ እንዲህ አልነበረም?” ይሉሃል::አያፍሩም::እፍረት ስለሌላቸዉም ደግሞ ዞር ብለወ ወንጀላቸዉን እያከበሩ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ይሳለቃሉ::
———-
በዚህ ድራማቸዉ ቀልዳቸዉ እና መራራ ወንጀላቸዉ ተሳታፊ የሚሆኑ የሌላ ነገድ ባለስልጣናትም አላጡም::እንደ አገኘሁ ተሻገር አይነቱ የአማራን ህዝብ እወክላለሁ ባይም “እናንተ ኦህዴዶች በኦሮሚያ የአማርን ህዝብ ለመጠበቅ ምን ያህል እየተጋችሁ እንደሆነ እናቃለን” ብሎ ምስክርነት ይሰጣቸዋል:::ከዚያም ቸብ ቸብ ቸብ ቸብ….በአደባባይ::እናም ስላቁ እና የሌሎች ነገዶችን ዘር ማጥፋቱ እና ማስጠፋቱ በኦህዴዳዉያን ድራማ እና በብሄር ብሄረሰቦች ቀን ማክበር ስም በሸራተን አዲስ በዉስኪና በጮማ ይከበራል::
የምትጠጡት መጠጥ የሰዉ ደም: የምትቆርጡት ስጋም የሰዉ ስጋ መሆኑን ግን ጌታ እግዚአብሄር ይመሰክራል::
Filed in: Amharic