>

በፕ/ሮ ኤፍሬም መሪነት በተካሄደው ድብቅ ስብሳባ ላይ በተሳተፉ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እንዲጀመር ተጠየቀ‼ (አወድ መሀመድ)

በፕ/ሮ ኤፍሬም መሪነት በተካሄደው ድብቅ ስብሳባ ላይ በተሳተፉ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እንዲጀመር ለኤፍ ቢ አይ እና ለአቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰረትባቸው ተጠየቀ‼
አወድ መሀመድ

በአሜሪካ የሚገኙ አራት የኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበራት በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የኢትዮጵያ መንግሥት በኃይል ለመቀየር በማሰብ በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ አጋፋሪነት እነ ኢሌኒ ገብረመድህን፣ አሸባሪው ብርሃነ ገ/ክርስቶስን ጨምሮ የቀድሞ የአሜሪካ አምባሳደሮችና ሌሎች በሴራው ላይ የተሳተፉ ግለሰቦች በሕግ እንዲጠየቁ ለፍትህ መምሪያ፣ ለኒዮርክ አቃቤ ህግ ቢሮ እና ለፌዴራል የወንጀል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡
 
ደብዳቤውን የጻፉት ተቋማትም ፦
 
➣ግሎባል ኢትዮጵያን አሜሪካን አድቮኬሲ ኔክሰስ፣
➣ወርልድ ዋይድ ኢትዮጵያን አክሺን ፈንድ፣
➣ዩኒቲ ፎር ሂውማን ራይት ኤንድ ዴሞክራሲ እና ➣ኢትዮ-አሜሪካን ዴቨሎፕመንት ካውንስል ናቸው፡፡ 
 
ተቋማቱ በጻፉት ደብዳቤ የግለሰቦቹ  ተግባር ከ118 ዓመት በላይ የዘለቀውን የኢትዮጵያ እና አሜሪካ ወዳጅነት በእጅጉ የሚጎዳ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
ከሳምንት በፊት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጨምሮ የአውሮፓና አሜሪካ ዲፕሎማቶች በድብቅ ያደረጉት የሽግግር መንግሥት የመመስረት የበይነ መረብ ውይይት አሜሪካ በሌላ አገር የውስጥ ጉዳይ እንደማትገባና የሌላ አገር መንግስትን ለመስወገድ አትሰራም የሚለውን ሕግ የሚጥስ በመሆኑ የአሜሪካ የፌደራል ምርምራ ቢሮ (FBI) እና የኒውዮርክ አቃቤ ሕግ ቢሮ በእነዚህ ግለሰቦች ላይ ምርመራ እንዲያካሂዱ ጠይቀዋል፡፡
ከሁሉም ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ጋር ተባብረን  የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እናስጠብቃለን፤ እንዲሁ ያሉ ተግባራትን እናወግዛለን ብለዋል ተቋማቱ በጻፉት ደብዳቤ። በኢትዮጵያ የተጀመረውን የዲሞክራሲ ለውጥ ለማደናቀፍ የሚሞክሩ ሃይሎችን ከአሁን በኋላ ይቁም እንላለን።
ዝርዝር መረጃውን ሊንኩን ተጭነው ያገኙታል።
Filed in: Amharic