>

" ሱዳን የግብጽን ፍላጎት ለማስፈጸም በኢትዮጵያ ላይ የጸብ አጫሪነት ትንኮሳ እያካሄደች ነው"  (ሱዳናዊ ጋዜጠኛ  ካሊድ አል-ሰናቢ)

” ሱዳን የግብጽን ፍላጎት ለማስፈጸም በኢትዮጵያ ላይ የጸብ አጫሪነት ትንኮሳ እያካሄደች ነው”  –ሱዳናዊ ጋዜጠኛ  ካሊድ አል-ሰናቢ
 
በመሀመድ ሁሴን

በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል ግጭት በማስነሳት የግብጽን ስውር አጀንዳ ለማስፈጸም እየተሰራ ነው። ይህ የውክልና ጦርነት ሱዳንና ሕዝቦቿን የሚጎዳ  ከመሆኑም በላይ የሱዳንን ባለስልጣናት ተላላኪነት የሚያጋልጥ መሆኑን ሱዳናዊ ጋዜጠኛ ካሊድ አል-ሰናቢ በሱዳኑ ዓል ራኮባ ጋዜጣ ላይ ጽፏል።
በአል-ቡርሃን ጦር  አማካኝነት በኢትዮጵያ ድንበር ላይ የተካሄደው ጦርነት አስገርሞኛል፤ የግብጽን የውክልና ጦርነት  ሱዳን ስለምን ተላላኪና አስፈጻሚ ሆነች በማለት የሱዳኑ ዓል ራኮባ ጋዜጣ ፀሐፊ ካሊድ አል-ሰናቢ ይገልጻል።
የኢትዮጵያ ጦር የሱዳን ጦር ላይ ጥቃት ሰነዘረ በሚል የሀሰት ውንጀላ የውክልና ጦርነቱን እየጀመሩ ነው ያለው ካሊድ፤  ሁላችንም የምናውቀው የአኢትዮጵያ መንግስትና መከላከያ ሰራዊቱ አሸባሪው የህወሓት  ቡድን በአማራና በአፋር ክልሎች የሰነዘረበትን ጥቃት ለመመከት ከየአካባቢው የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን በመዋጋት ላይ መሆኑን ነው ብሏል።
በሱዳን ላይ ምንም አይነት ጦርነት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አለመጀመሩን አስረድቷል።
ዶ/ር አብይ አህመድ ወደ ጦር ግምባር በአካል ገብተው በማዋጋት እነዚህ የጥፍት ቡድኖች ወደ አዲስ አበባ ለመግባት  ያሰቡትን የጥፍት  ተልእኮ ለማክሸፍና  የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በተቃጣበት የሕልውና ጦርነት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፡ የኢትዮጵያ መንግስት ጦርነት ከፈተብን ብሎ ማውራት ፈጽሞ ከእውነት የራቀ መሆኑን ጸሐፊው አመላክቷል።
ጸሐፊው እንደገለጸው በኢትዮጵያ የተከሰተውን ጦርነት እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም የግብፅን ስውር ፍላጎት ለማስፈጸም በግብጽ የመረጃ ሰዎችና የግብጽ መንግስት አሻንጉሊቱን አል-ቡርሀንን በመጠቀም በሱዳን ካሉ የሰራዊቱ ክፍሎች ጋር ተደራጅተው በኢትዮጵያ ላይ የከፈቱት የውሸት ጦርነት መሆኑን አስረድቷል።
የግብፅ መንግስት በአል-ቡርሃን ተላላኪነት የፈለጉትን ዕኩይ ተግባር በኢትዮጵያ ላይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም የሚያደርጉት ጥረት ለህዝቡ ያለውን ጠላትነትና  ምንም አይነት የሀገር ፍቅር ስሜት አለመኖሩን መረዳት ይገባል ይላል ፀሐፊው።
ከግብጽ መንግስት በኩል በሚገባለት የውሸት ቃል ኪዳኖች ተነሳስቶ በሱዳን ና በኢትዮጵያ ያለውን መሠረተ ልማት ለማውደም እና የሁለቱን ሀገራት የልማት ፕሮጀክቶች ለማደናቀፍ የግብፅ የውክልና ጦርነት በኢትዮጵያ ላይ እንዲከፍት  እያደረገ ያለው የሱዳን መንግስት ነው።
የሱዳን መንግስት በሱዳን ወጣቶችና በሕዝቡ እየተነሳበት ያለውን ተቃውሞ ለማርገብ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ማፈኑን የገለጸው ጸሐፊው የራሱን ዜጎች ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ  ወጣቱን አዋርዶ አብዮቱን ለመቀልበስ እየጣረ ነውም ብሏል።
የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ በቅርቡ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የሱዳን መንግስት ወታደሮቼ ተገደሉብኝ በሚል ያወጣው መረጃ ሀሰት መሆኑን ጠቅሰዋል። መንግስት የአሸባሪው ህወሓት ታጣቂዎች የሆኑና ብሱዳን ስልጠና ወስደው እና ታጥቀው ሊገቡ የሞከሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የማይካድራ ጨፍጫፊዎችን መደምሰሱን መግለጹም የሚታወስ ነው።
Filed in: Amharic