>

“በምሥራቅ እና በምዕራብ የተገኘው ድል በመሐል ሀገር ይደገማል”( ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ)


በምሥራቅ እና በምዕራብ የተገኘው ድል በመሐል ሀገር ይደገማል”፦
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

በምሥራቅ እና በምዕራብ የተገኘው ድል በመሐል ሀገር እንደሚደገም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የተናገሩት በሦስተኛው ቁልፍ ግንባር ተገኝተው ከሠራዊቱ ጋር በመከሩበት ወቅት ነው።
ከሰሞኑ በሚሠሩ ኦፕሬሽኖች በወራሪው አሸባሪ የተያዙ ተጨማሪ ከተሞች ነጻ እንደሚወጡ ገልጸው፣ ለወረራ የገባው አሸባሪ ምንም ነገር ይዞ እንዳይወጣ ሕዝቡ ተደራጅቶ ማስቀረት እንዳለበት ጥሪ አቅርዋል።
“ጠላት ፈርሷል፤ ተበትኗል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ “አሁን ጠላት ያለው አማራጭ የሰረቀውን አስረክቦ እጁን መስጠት ነው” ብለዋል።
“የሰረቀውን አስረክቦ እጁን ከሰጠ ምርኮኞችን ተንከባክቦ መያዝ የጀግና ባህላችን ነው” ብለዋል።
ከአሸባሪው ሕወሓት ነፃ በወጡ አካባቢዎች በአስቸኳይ መስተዳድሩን በቶሎ መልሶ ማቋቋም እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሳስበዋል።
“ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነዋል፤ ወታደሩ በከፍተኛ ሞራል ላይ ነው” ሲሉም የወገን ኃይል ያለበትን ደረጃ አመላክተዋል።
ሕዝቡ እስካሁን ላደረገው ተሳትፎ ምስጋና አቅርበው፣ “አንድነታችን የተጠበቀ ይሁን፤ የአሉባልታ ወሬ ወጀብ አይውሰደን፤ አንድ ሆነን የማትደፈር ሀገር ለልጆቻችን እናስረክብ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መልእክት አስተላልፈዋል።
Filed in: Amharic