ሕወሓት በአሥመራ መንገድ ሲወጣ በቦሌ በኩል የገባው ኦነግ አልተቻለም!
ነፃነት ዘለቀ
“ጉድ ነሽ ያንኮበር ቅጠል” ብሏል አሉ አንዱ የደረሰበት ደርሶበት፡፡ ይህች ኢትዮጵያችን የማታሰማን የጉድ ዓይነት የለም፡፡ ኢትዮጵያ የትንግርት ሀገር ሆናለች፡፡ ከጆሮ አቅም በላይ ነው የሚነገረው ሁሉ፡፡
አሪስቶትል ይሁን ፕሌቶ ወይ ሌላ ፈላስፋ ተናገረው የተባለ አንድ ቁም ነገር በዚህች አጋጣሚ ባስታውስ ደስ ይለኛል፡፡ “አንድ መምህር የሚያስተምራቸው ተማሪዎች ከመምህሩ ካልበለጡ መምህሩ ደከመ እንጂ አላተረፈም፡፡” … በቀናነት ካየነውና እንደውነቱም ከሆነ ጥሩ አባባል ነው አይደል? አዎ፣ ተማሪ መምህርን ካልበለጠ ተመሳሳይ ቅጂ መፍጠር የትውልድን ዕድገትና የወደፊት ግስጋሴ እንደማቀጨጭ ይቆጠራልና አባባሉ ትክክል ነው፡፡ “ከመምህሩ ደቀ መዝሙሩ” የምንለው አገርኛ ብሂል በአጠቃቀም ወደአሉታዊነት ስለሚያደላ ለአሁኑ አነሳሴ ብዙም አይፈይድምና ሆነ ብዬ ተውኩት፡፡ እርግጥ ነው – ወያኔንና ኦህዲድን ማለትም ኦነግን በሚመለከት ግን እዚህ አሁን የጠቀስኩት የሀገርኛው ሥነ ቃል ይበልጥ ገላጭ ይመስለኛል፡፡ ተማሪ መምህርን መብለጥ ያለበት በበጎ ጎን ሲሆን እንጂ በክፋት ከሆነ ጥሩ አለመሆኑን ለመጠቆም ነው ዙሪያ ጥምጥም መጓዜ፡፡ በአወንታዊ ነገር ከጊዜ ወደጊዜና ከደረጃ ደረጃ በልጦ መገኘት ትውልድን ያንጻል፤ በአሉታዊ ነገር በልጦ መገኘት ግን ትውልድን ብቻ ሣይሆን ራስንም ያፈርሳል – ልክ እንደኛ፡፡
ኢትዮጵያን ለመበታተን አቅዶ ሕወሓትን ማን ፈጥሮ እንደላካትና ያ የጠላት ኃይል በሀገራችን ምን ጉዳት እንዳደረሰ ብዙ ጊዜ ተወስቷል፡፡ ቆየት ያለ ታሪክም ስለሆነ አሁን ወደዚያ ባንገባ ጊዜ እንቆጥባለን፡፡
ልጅ ወልዶ ማሳደግና ለወግ ለማዕረግ ማብቃት መቼም የተለመደ ነውና ሕወሓት በተራዋ ኦህዲድ የተባለ ልጅ የዛሬ 32 ዓመት ገደማ መንዝ ውስጥ ደራ በሚባል ልዩ ቦታ መጋቢት 17 ቀን 1982ዓ.ም ከደርግ ምርኮኛ የኦሮሞ ተወላጆች እነአባዱላንና ኩማ ደመቅሳን መሰል አጋሰሶችን መራርጣ በአንድ ቀን እርግዝና በቀላል ምጥ ወለደች (እነዚህ ምርኮኞች የቀድሞ ስማቸውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለቆሙለት ዓላማ ስኬት ሲሉ መለወጣቸውን ልብ ይሏል)፡፡ ከዚያ በፊት ግን አማራንና አማራውያንን ለመያዝ ብላ ኢሕዲን የሚባል እንግዴ ልጅ መገላገሏ አይዘነጋም፡፡ ያ ልጅ አሁን ጎልምሦ ብአዴን በሚል መለስ ያወጣለት ስም አማራን እያስፈጀ ነው፡፡ ይህ ሁሉ ክፍለ ዘመናዊ የትራጄዲ ትያትር እስከመቼ እንደሚቀጥል ፈጣሪ ብቻ ነው የሚያውቀው፤ ሆኖም እግዜሩም የደነደነ ልባችንን እያዬ አሣራችንን አበዛው፡፡
ልጅ ከተወለደ አይቀር ቁርጥ አባቱን ሲሆን ደስ ይላል፤ ያኔ ታዲያ ወላጅንም ያኮራል፡፡ እናም የወያኔ ልጆች ቁርጥ አባታቸውን ስለመሆናቸው በተለይ ለጉድ የጎለተን አንጋፋ ዜጎች የማተባችንን እንመሰክራለን፡፡ አንዳንድ ልጅ እንዲያውም ምስስሉ እስከአያትና ከዚያም ሊያልፍ እንደሚችል በጀብሃ/ሻዕቢያ እና በኦህዲድ/ኦነግ መካከል ያለውን ጥብቅ ዝምድና በማየት መገንዘብ ይቻላል – በተለይ አማራና ኢትዮጵያ ላይ ባላቸው ጥላቻ፡፡
ለማንኛውም ወደመነሻየ ልመለስ፡፡ ሕወሓት በአሥመራ መንገድ ወደ መቀሌ ስታስነካው ኦነግ ደግሞ በወቅቱ በተፈጠረለት ምቹ ሁኔታ በልጁ በአቢይ አህመድ አማካይነት በቦሌ አየር መንገድ በኩል ሰተት ብሎ ገብቶ አየር መንገዱን ራሱን ጭምር በመቆጣጠር በጥቅሉ በኢትዮጵያ በተለይ ደግሞ በአየር መንገዳችን አሁን ምን እየሠራ እንዳለ የአደባባይ ምሥጢር የሆነውን ጉድ ለመግለጽ ነው ዋና አነሳሴ፡፡
ልጅ ተወልዶ አባቱን ካልበለጠ “ምኑን ተወለደው?” የሚል ነገር አልነበር ከመነሻየ የጠቆምኩት? አዎና፤ ያኔ ዱሮ ወያኔን ይሉኝታ ቢስ ያልኩበትን ምላሴን አሁን አፈርኩበት፡፡ አሁን ላይ ሆኜ ሳስበው ወያኔዎች መጠነኛ ይሉኝታ ነበራቸው – እንደገቡ ሰሞን ያሳዩት የነበረውን ጠባይ ነው የምልህ ታዲያ፤ በተለይ ከ2010ሩ ለውጥ ተብዬው ወዲህ በአጠቃላይ ደግሞ ከ1997 ወዲህ ያሉትን ወያኔዎች አላልኩም፡፡ “ሚስት ካልሞተች ወይ ካልተፈታች ጣሟ አይታወቅም” ይባላልም አይደል? እነዚህ ኦነጋውያን እኮ ከሕወሓቶች ነባሩ ነውረኝነት (የአሁኑማ ለወሬም አይመችም!) ብዙም ባልተናነሰ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሣንሆን የሰው ዘርን በሙሉ በሀፍረት አንገት የሚያስደፋ ነገር ነው እያደረጉ የሚገኙት፡፡ ይሉኝታና የሞራል ዕሤት ብሎ ነገር ሲያልፉ አይነኳቸውም፡፡ መደዴነታቸው ደግሞ ከአነጋገር ብልግናቸው ላይ በግልጽ ይታያል፡፡ ጨዋነት ምን ማለት እንደሆነ በጭራሽ አያውቁም፡፡ ሰውን ሲያመናጭቁ አይጣል ነው፡፡ አንተ በተረጋጋ መንገድ ስታናግራቸው እነሱ እሳት እንደበዛበት የድሃ ሽሮ ከላይ ከላይ ነው የሚንተከተኩት፡፡ ምክንያቱም ባንኩም ታንኩም በነሱ ቁጥጥር ሥር ነዋ! ዘረኝነት በዕብሪትና ጥጋብ አቅልን የሚያስትና ያንተ ያልሆነን ጎሣና ነገድ ሁሉ ያንተ አሽከር እንደሆነ በመቁጠር በጌትነት የስሜት ስካር የሚያነበርር መጥፎ በሽታ መሆን አለበት፡፡ በእውነቱ ይህን መሳይ ሥነ ልቦናዊ ልክፍት እንኳንስ ለወዳጅ ለጠላትም አይስጥ፡፡
አሁን እኮ ከሦስቱ ስሞችህ በአጋጣሚና ዕድልህ ተጣሞ የትግርኛ ከሆነ ጉድህ ነው – የትም ቦታ በተለይ ደግሞ ቦሌ አየር ማረፊያ፡፡ አንዱ ጓደኛየ “ጥሎበት” የአባቱ ስም – የትግሬ ስም ብሎ ነገር መኖር አለበት ብዬ ባላምንበትም – የትግሬ ነው፤ (ለምሣሌ እኔ ዛሬውኑ ስሜን ለውጬ “ፍትዊ” ወይም “ሰርቤሣ” አሊያም “ዘበርጋ” ሆኛለሁ ብል የሚከለክለኝ ህግ ወይንም ቤርቤረሰብ አለ እንዴ?)፡፡ … ለማንኛውም ጓደኛየ ወደ አንድ ሀገር ለመሄድ በቦሌ አየር መንገድ በኩል ማለፍ ነበረበት፡፡ የርሱ ተራ ደርሶ ፓስፖርቱ ሲታይ የአባቱ ስም “ሐጎስ” ይላል፡፡ ያኔ የአየር መንገዱ የመንገደኞች ቁጥጥር ኃላፊ ኦቦ ደቻሣ ሊለቀው ነው? ልክ ከጠፈር እንደመጣ ልዩ ፍጡር ቆጥሮት ዐይኖቹን ጎልጉሎ አፈጠጠበታ! ከሌሎች ተሣፋሪዎች ለይቶ ወደኋላ የሚያስቀረው ከስሙ በስተቀር ሌላ ምንም ምክንያት የለም፡፡ እንደተፋጠጡ አየሩ ሊነሣ ሆነ፡፡ ጓደኛየ ግን በውል ባልተረዳው ምክንያት ቢሮ ውስጥ እንደተገተረ ነው፡፡ ደቻሣም የተለዬ ወንጀለኛ የያዘ መሆኑን በሚያሳብቅ ከፍተኛ ጀብድ ተጀቡኖ በስልክ ከበላዮች ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል – በኦሮምኛ፡፡ (የአየር መንገዱ በዐዋጅ ያልተነገረ ግን በጉልበት እየተተገበረ የሚገኝ ኦፊሴላዊ ቋንቋ ኦሮምኛ መሆኑን ለመጠቆም እንጂ የቋንቋውን በዚያ ቦታ መነገር በመቃወም እንዳልሆነ ይታወቅልኝ ታዲያ)፡፡ በዚያ መሀል ኦቦ ደቼ የቀበሌ መታወቂያውን እንዲያሳይ ጓደኛየን ይጠይቀዋል፡፡ አሳየው፡፡ የፈረደበት ብሔር ሲታይ “ኦሮሞ” ይላል፡፡ ደቻሣ ቀጠለ፡- “ያባትህ ስም ትግሬ ሆኖ እንዴት ኦሮሞ ብሔር ልትሆን ትችላለህ?” – ጓደኛየ ቀጠለ – “ኦሮሞ መሆን ወንጀል ነው እንዴ?” – ባልጠበቀው መንገድ ነው የሄደበት፡፡ ከፊል ኦሮሞው ጓደኛየ የደቻሣ አመጣጥ ገብቶታል፡፡ ደቼ ቀጠለ – ምንም ድንግጥ ሳይልና በማስፈራራት ጭምር (ባጊዜነት ግን ደስ ሲል!)፡- “እንደሱ ያለህ የለም … እኔ ያልኩህ….” የጓደኛየን ነገር በዚህ ልቋጨው፤ ችግሩ ዕልባት አግኝቶ ሄዷልና በሄደበት ይቅናው፡፡ አየር መንገዱ ግን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሀብት ንብረትና መገልገያ ሳይሆን በአሁኑ ሰዓት የአንድ ነገድ ብቸኛ አንጡራ ሀብት ሆኗል፡፡ እዚህ ላይ መታወቅ ያለበት ትልቁ ጉዳይ ይህ አየር መንገድ 86ቱም ነገዶች ላባቸውን ጠብ አድርገው የመሠረቱትና ያሳደጉት እንጂ የአንዱ ጎሣ ብቻ ጥሪት አይደለም፡፡
አሁን በግልጽ እንደሚስተዋለው ቦሌ አየር መንገድ ሥራውንና የመስተንግዶ ሙያን ፍጹም በማያውቁ መደዴ አክራሪ ኦሮሞዎች ተሞልቷል፡፡ ኦሮሞነታቸው ችግር ሊሆን አይችልም፡፡ ግና ኦሮሞ ብቻ ያን ቦታ መያዝ አለበት ቢባልም እንኳን ለኦሮሙማው መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ማሳሰብ የምፈልገው “ሰው ሰው የሚሸቱ ኦሮሞዎችን እየፈለጋችሁ ቅጠሩ፤ ሰገጤ ኦሮሞዎችን ከየገጠሩ እያመጣችሁ በመሰግሰግ አታዋርዱን” የሚል ነው፡፡ አየር መንገድና ንግድ ባንክ በአንጻራዊነት በወያኔ ብዙ ሳይበለሻሹ እስካሁን ለዘር ያህል ቀርተውልን ነበር – አሁን እነሱንም ኦነግ/ኦህዲዶች አግማሟቸው፡፡ ኤዲያ! የሚያስጠላ ዘመን፡፡
ኦነግና ኦነጋውያን የማያሰሙን ጉድ የለም፡፡ ሌላ ጉድ ልንገርህ ከፈለግህ፡፡ ባንኮችና በርካታ መሥሪያ ቤቶች ደግሞ የቅጥር መሥፈርታቸውን አሻሽለው አንድ ዜጋ ለመቀጠር ዕድሜው ከ25 ዓመት በታች መሆን አለበት ተብሏል – ካሻህም ኦሮሞነትንም ልትጨምርበት ትችላለህ – ውኃ የሚያነሣ እውነት ነውና፡፡ ይህም ህግ ታዲያ በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርደስ ይመዝገብልን፡፡ እነዚህን ልበ ሥውራን የፍላጎቶቻቸውን በርና መስኮት አንድዬ ይዘጋጋልን እንጂ የማያደርጉን ነገር ላይኖራቸው ነው – አይፈልጉ እንጂ ስማችንን እንድንለውጥ ቢፈልጉስ? አይፈልጉ እንጂ በአንድ አዳር ቋንቋችንን እነሱ ወደሚፈልጉት እንድንቀይር ቢፈልጉስ? አይጣል አትልም!! …. እናስ ታዲያ ከ25 ዓመት በላይ ሥራ አይቀጠርም ማለት የጤና ነው? ኦነግ ከእንግዲህ ስድስት የአገዛዝ ዓመታትን አግኝቶ ሥልጣን ላይ በድምሩ ለ10 ዓመት ቢቆይ ኢትዮጵያ ምን ልትመስል እንደምትችል በምናባችሁ ቃኟት፡፡ ደግነቱ ….የነሱም የጌቶቻቸውም ቀን ከሞላ ጎደል እኩል መምሸቱ፡፡
የመንግሥት ሥራ ለማመልከት በብዙ ቦታዎች የኦሮምኛ ቋንቋ መቻል እንደግዴታ ያህል እንደሚጠየቅም ሰምቻለሁ፡፡ በአዋሽ ባንክ፣ በኦሮሚያ ባንክ፣ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክና በመሳሰሉትማ ዱሮውንም ካለኦሮሞ አይቀጥሩም – ትልቅ የአላዋቂነትና የግብዝነት ምልክት ነው ይህ ዓይነቱ ውሻን ይመስል ደም ማነፍነፍ፡፡ በሌላ በኩል ግን ነፈዙ የአማራ ክልል መሥሪያ ቤቶቹን ተዋቸውና የክልሉን ፕሬዝደንትም ሳይቀር ኦሮሞ ሊያደርግ ይችላል፡፡ በበኩሌ አይሁን አልልም፡፡ ግን ግን አንዱ ብልጥ ሆኖ ሌላው ሞኝ ሲሆን ከነፈዝነትም በላይ ነው፡፡ የሚገርመው በኦሮምያ አካባቢ ኦሮምኛ ብትችልም አክራሪው ኦሮሞ አይቀበልህም፡፡ ኢትዮጵያውያን ከነገድ ማዕቀፍ ወጥተን ሰው የምንሆንበት ወርቃማ ጊዜ ናፈቀኝ፡፡
ይህ የዘረኝነት የቋያ እሳት ከሀገራችን ካልተወገደ ኢትዮጵያ አፈሯን አራግፋ ከሙታን መንደር አትነሳም፡፡ በስምና በቋንቋ እንዲህ እየተናፈርን የትም አንደርስም፡፡ ስም ደግሞ የሁሉም ነው፡፡ ደራርቱ ባሸነፈች ወቅት ልጁን ደራርቱ ብሎ የጠራ እጅግ ብዙ ኦሮሞ ያልሆነ ዜጋ ነበረ፡፡ የአብዲሣ አጋን ታሪክ ያነበበ ብዙ ዜጋ የልጁን ስም አብዲሣ ብሎ ሰይሟል፡፡ የኃይሌንና የቀነኒሣን ክብርና ዝና የሚያውቅ ብዙ ሰው ልጆቹን በነሱ ስም ጠርቷል፡፡ እና ስምህ ስንሻው ስለሆነ ሥራ አትቀጠርም ወይም ስምህ ግደይ ስለሆነ በዚህ መንገድ አታልፍም ይባላል? ጉሙዞችና በርታዎች ልጆቻቸውን ጆንሰንና ዊሊያም ብለው ይሰይማሉ፡፡ የእንግሊዛዊው የሪቻርድ ፓንክረስት ልጅ ዶክተር አሉላ ፓንክረስት መባሉንም እናስታውስ፡፡ ስም እኮ ተራ ነገር ነው፤ ቋንቋም ጭምር፡፡ ስትሞት ጥለኸው የምትሄደው ማንኛውም ምድራዊ ነገር ሁሉ የሞትህ መንስኤ ሊሆን የማይገባው እጅግ በጣም ተራና ትንሽ ነገር ነው፡፡ ድንቁርና ቤቱን ሠራብንና ክፉኛ ተበጠበጥን፡፡ ደርግና ወያኔ እግዜር ይይላቸው፡፡ የግብረ ገብ ትምህርት መቼ ነበር የቀረው
“ኢትዮጵያ በሁለት እሳቶች መሀል ገብታ እየነደደች ትገኛለች፡፡” በሚለው ሃሳብ ጅምሬን ላጠናቅ፡፡ አንደኛው በሕወሓት ቅሪቶች በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚፈጸመው ሊሰሙት የሚዘገንን ከሰይጣንም የከፋ ሰይጣናዊነት ሲሆን ሌላኛው በተረኞቹ እየተከናወነ የሚገኘው የዘረኝነት ዕኩይ ተግባር ነው፡፡ ደረጃቸው ይለያይ እንጂ ሁለቱም ነዲድ እሳቶች ናቸው፡፡ ሁለቱም መከሰቻቸው ሞትና የንብረት ውድመት እንዲሁም በማያባራ የኑሮ ውድነት ሕዝብን በርሀብ አለንጋ መግረፍ ናቸው፡፡ ቸሩ ፈጣሪ ከሁለቱም ይገላግለን፡፡
በመጨረሻም – እነሽመልስ አብዲሣ ሆይ – በምታምኑት ይሁንባችሁ – እነዚህን ጅላጅል የቦሌ አየር መንገድና የሌላም ቦታ ሠራተኞች በተሻሉ – ሥራውን በሚችሉና ለሰው ክብር በሚሰጡ – ኦሮሞዎች ለውጡልን!! ኦሮሞን አታሰድቡ እንጂ፡፡ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ በእናንተ ጦስ ይሰደብ? ሀ/ጊዮርጊስ ዲነግዴ (አባመላ) በነዚህ ነፍጫሎች ሳቢያ ይወቀስ? አፄ ኃይለ ሥላሤ፣ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ፣ ጄኔራል ካሣየ ጨመዳ፣ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያም፣ ሎሬት ፀጋየ ገ/መድኅን፣ አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ፣ ዶር. መስከረም ለቺሣ፣ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሣ …. በነዚህ ጅላንፎዎች ምክንያት ስማቸው በክፉ ይነሳ? አይ – ግዴላችሁም – ጤነኛ ነን የምትሉ ኦሮሞዎች – በአካልም ይሁን በኅሊና፣ በጥቅምም ይን በዓላማ ያልታሰራችሁና ከተረኞቹ ጋር ያልተሳሰራችሁ ማለቴ ነው – ሰብሰብ በሉና ነገሮች ከዚህም በባሰ ሳይበላሹ መላ ፈልጉ፡፡ ጥሩ ነገር እየታየኝ አይደለም፡፡ ይህንንም ስል ነገን ሳላውቀው ቀርቼ እንዳይመስልብኝ ታዲያ፡፡ ነገ ከትናንት ጀምሮ ግልጽ እንደነበር ሁለመናየ ያውቅ ነበርና ችግሬ አሁን እንጂ ነገ ሊሆን እንደማይችል ማሳሰብ እፈልጋለሁ፡፡ ነገማ ቆንጆ ነው!! ቆንጆነቱ ግን ከአሁኑ ቢጀምር ደስ ይለኛል – ማንንም እንዳላጣ….
ሰላምና ፍቅር ለኢትዮጵያችን ይሁን፡፡ “ኢትዮጵያ” የሚለው ስም ሲጠራ ለሚያስደነግጣቸውና እውነተኛው ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ አዶከብሬያቸው ለሚነሳባቸው ወንድሞቼና እህቶቼ መጽናናትንና የፈጣሪ ምሕረትን ተመኘሁ፡፡