>

ከኤርትራ ማሰታወቅያ ሚኒስትር የተሰጠ መግለጫ... !!!

ከኤርትራ ማሰታወቅያ ሚኒስትር የተሰጠ መግለጫ… !!!
ኣሜሪካና ሸሪኮቿ፡ ኤርትራን ከዓለም ማህበረ-ሰብ ነጥለው በሁለንተናዋ ለማዳከም፡ በላይዋ ላይ ለረዥም ግዜ የቀጠለ ወታደራዊ፡ ፖለቲካዊ፡ ኢኮኖሚያዊና ዲፕሎማስያዊ ሴራዎች ሲፈጽሙ ቆይተዋል። ከ 1998 እስከ 2000 ዓ.ም. በወያኔ ውክልና ኣማካይነት በኤርትራ ግልጽ ወታደራዊ ወረራ እንዲካሄድ ኣበረታትተዋል፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ የድንበር ኮምሽን ውሳኔ እንዳይተገበር በእግት ይዘው፡ የሰላምም የጦርነትም ያልሆነ ውጥረት የሰፈነበት ኩነት ፈጠሩ። በ 2009/2011 ደግሞ ምንም ምክንያት ያልነበረው ኢ-ህጋዊና ኢ-ፍትሃዊ እገዳ ወሰኑ።
ከወታደራዊ፡ ፖለቲካዊና ዲፕሎማስያዊ ክብ ዙርያ በቀጣይ ከተካሄዱት ጠብ-ኣጫሪነቶች ጎን ለጎን፡ የኤርትራን የኢኮኖሚ እድገት በማነቅ፡ የማህበረ-ኢኮኖሚ ችግርና ሰብኣዊ ቀውሶችን በመፍጠር፡ የቆየ ‘ስርዓት የመለወጥ’ ኣጀንዳቸውን ለመተግበር የሚያስችል ህዝባዊ ዓመጽ ለማነሳሳት፡ የኣሜሪካ ኣስተዳደር፡ በታህሳስ ወር 2003 ዓ.ም. ኤርትራን ኣፍሪካ-ኣሜሪካ የኢኮኖሚ ትብብር (ኣጎዋ) የሰረዛት ሲሆን፡ በሰኔ ወር 2009 ዓ.ም. በኢ-ህጋዊ የሰዎች ዝውውር (human trafficking) ከሚሳተፉ ኣገሮች ተርታ በመፈረጅ፡ በላይዋ ላይ ጠንካራ የፋይናንስ ማዕቀብ እንዲደረግ ወሰነ። ከዚህም በተጨማሪ ኣሜሪካና ሸሪኮቿ፡ ኤርትራ በሷ ከሚዘወሩት ዓለም-ኣቀፍ ድርጅቶች፡ የፋይናንስ ብድር እንዳታገኝና የምዕራብ ኩባንያዎች በኤርትራ ወዋእለ-ንዋያቸውን እንዳያፈሱ (ኢንቨስት) እንዳያደርጉ ኣገደቻቸው።
“ የስደተኞችና የተመላሽች ጉዳይ ኣስተዳደር” ማለት (Administration for refugee & Returnee Affairs) በምህጻረ-ቃል ARRA ‘ኣራ’ በሚል ስያሜ የሚጠራው በወያኔ ካድሬዎችና በትግራይ ክልል ደህንነት ኣባላት የሚተዳደር ተቋም፡ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽን ሰራተኞች ጋር በመተባበር፡ በኤርትራውያን ስደተኞች ስም ሲያካሂደው የቆየው የጥቅም ጨዋታ ለኣብነት፡ እነዚያን ሰብኣዊ ኣሳቢነት ከሚመስሉ የ UNHCR እንቅስቃሴ በስተ-ጀርባ ያሉትን ግዙፍ ጥቅሞች የሚያጋልጥ ነው።
“ የስደተኞችና የተመላሾች ጉዳይ ኣስተዳደር” ማለት ‘ኣራ’ ከትግራይ ክልል መስተዳድር መሬት በመከራየት ሽመልባ፡ ሕንጻጽ፡ ማይ-ዓይኒና ዓዲ-ሓርሽ የተባሉ ኣራት የስደተኞች መጠለያ ካምፖችን በማቋቋም፡ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽን ጋር በመተባበር፡ ኤርትራውያንን ሲቀበል የነበረ ተቋም ነው። የነዚህ መጠለያ ካምፖች ኪራይ ፡ UNHCR የሚከፍለው ሲሆን፡ ለኣንድ የስደተኞች ካምፕ በዓመት 2.4 ሚልዮን የኣሜሪካ ዶላር ይከፍልበት ነበር። በዚህ ስሌት ደግሞ የኣራቱም የስደተኛ መጠለያ ካምፖች በኣንድ ዓመት 9.6 ሚልዮን ዶላር፡ UNHCR በማእከላዊ የኢትዮጵያ መንግስት ኣማካይነት ወደ ‘ኣራ’ ገቢ ያደርገዋል። ‘ኣራ’ ደግሞ ለያንዳንዱ ስደተኛ በየወሩ 150 ዶላር የኪስ ገንዘብ ከ UNHCR ይቀበል ነበር። ለስደተኞቹ የሚሰጠው ግን በወር 80 ብር ብቻ ነበር። የቀረው ደግሞ ወደ ትግራይ ክልል ካዝና ገቢ ይሆን ነበር። ከዚህ ክፍያ የትግራይ ክልል መስተዳድር በየወሩ ከ 4.5 እስከ 6 ሚልዮን ዶላር ገቢ ነበረው። ከዚህም ሌላ፡ በኤርትራውያን ስደተኞች ስም ከተለያዩ ለጋሽ ማህበራት የሚመጣውን ስፍር-ቁጥር የሌለው ዓይነታዊ (ቁሳዊ) ድጋፍ የ’ኣራ’ ሃላፊዎች ከ UNHCR ተወካዮችና የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ጋር እየተመሳጠሩ እንደፈለጉ ያደርጉታል። ከዚህም በተጨማሪ ለህጻናትና ለታዳጊዎች እየተባለ በ UNICEF ይሰጥ የነበረው እርዳታም፡ በሙሉ ወደሚመለከታቸው ሳይደርስ፡ የትግራይ ክልል ሃፊዎች፡ የ’ኣራ’ ና የUNHCR ሰራተኞችን ኪስ ሲያሳብጡበት ቆይተዋል።
የ’ኣራ’ ባለስልጣናት፡ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽን ሃላፊዎች ጋር በመመሳጠር ሲፈጽሙት የቆዩ ሌላ ኣስደማሚ ሴራ ደግሞ ፡ ወደ ሶስተኛ ኣገር የማሸጋገር ዕድሎችን ፡ በኤርትራውያን ስም ገንዘብ እያስከፈሉ ኮሮጇቸውን ያሳብጡበት ኣልያም በእከከኝ ልከክህ ዕድሉን ለሌሎች የትግራይ ተወላጆች ይሰጡት የነበረ መሆኑ ነው። በዚህም ፋይላቸው በወደ ኣውሮፓ፡ ኣውስትራልያ፡ ካናዳና በኣሜሪካ የተላከ፡ ኑሯቸው ግን በስደተኛ መጠለያ ካምፖች ተገድቦ የቀረ ኤርትራውያን ቁጥር ጥቂት ኣይደለም።
Filed in: Amharic