>

በመዐዛ ላይ ማስረጃ ተገኝቷል...!!!  (አስረስ ማረ ዳምጤ)


በመዐዛ ላይ ማስረጃ ተገኝቷል…!!! 

አስረስ ማረ ዳምጤ

የህወሓትን ተልዕኮ ተቀብላለች ተብላ ከ16 ቀናት በፊት ጀምሮ 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስራ ያለችው Meaza Mohammed “ለህወሃት የተላላከችባቸው” ጉዳዮች ከብዙ በጥቂቱ¡:-
፩/ ከወለጋ የተፈናቀሉትን  አማራወች ገንዘብ ለምና ቤት ተከራይታ አስቀምጣለች፣
፪/ የመተከል አማራወችን ሰቆቃ አለም እንዲያውቀው አድርጋለች፣ የተፈናቃዮችን ህይወት ለማቆየት በብዙ ጥራለች፣
፫/ በደቡብ ወሎ ግምባር ተሰለፎ ለነበረው የነምሬ ወዳጆ ፋኖ 200 ካርቶን ተምር አስረክባለች፤ የወሎ ፋኖወች በገንዘብ እንዲረዱ ባደረገችው ጥረት መጠኑን ከዚህ መግለፅ የማልፈልገው ላቅ ያለ ድጋፍ እንዲያገኙ አድርጋለች፣
፬/ ቆስለው በየህክምና ጣቢያዎች የነበሩ የወሎ ፋኖወችን እየዞረች አሳክማለች ጠይቃለች፣
፭/ ህወሃት በራያ፣ በወልድያ፣ በጋይንት፣ በጨጨሆ እና ሌሎችም ቦታወች የፈፀመውን ግድያ እና ዘረፋ በቪዲዮ ማስረጃ አቅርባለች፣
፮/ የአማራ ኢመርጀንሲ ፈንድ በሚባለው ተቋም ውስጥ በነበራት ኃላፊነት በሚሊየን ለሚቆጠሩ ተጎጅወች እና ተፈናቃዮች ድጋፍ አድርጋለች፣
፯/ የትግራይ ወራሪ ጦር በጋይንት እና በደባርቅ መስመር በቆየበት ግዜ ከ100 በላይ በሆኑ እናቶች እና እህቶች ላይ የፈፀመዉን አሰቃቂ ወንጀል በቪዲዮ ማስረጃ አቅርባለች፣ ተጎጅወችንም በማሳከም ላይ ነበረች፣
፰/ በወልቃይት ሰቲት ሁመራ አስተዳደር በተደረገላት ግብዣ መሰረት የማይካድራ እና አካባቢውን ጭፍጨፋ ለህዝብ አሳውቃለች፣
፱/ በሰሜን ሸዋ አጣዬ እና ማጀቴ የደረሰውን ውድመት ለህዝብ ይፋ አድርጋለች፣ ተጎጀወችን ለማቋቋምም ብዙ ደክማለች፣
፲/ የህክምና ቁሳቁስ እጥረት የነበረባቸውን በአፋር እና አማራ ክልል የሚገኙ 6 ሆስፒታሎችን የህክምና መሳሪያ እንዲሟላላቸው አድርጋለች፣
፲፩/ በሻሸመኔ፣ ዶዶላ፣ አጋርፋ እና ሌሎችም ቦታወች በአማራ ላይ የተፈፀመውን ሰቆቃ በአካል በመገኘት ዘግባለች።
ለአማራ ህዝብ የሚያስብ ሁሉ ከመዓዚ ጎን መቆም አለበት (Naive ካልሆነ በስተቀር)።
Filed in: Amharic