>

እነ እስክንድር ነጋ የዳባት ተራሮችን አቆራርጠው  ጫካ ድረስ በመሄድ ከእነ መሳፍንት ተስፉ ጋር ተወያዩ...!!!! መረጃ ቲቪ

እነ እስክንድር ነጋ የዳባት ተራሮችን አቆራርጠው  ጫካ ድረስ በመሄድ ከእነ መሳፍንት ተስፉ ጋር ተወያዩ…!!!!
መረጃ ቲቪ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ልዑክ ቡድን ጎንደር፤ አጅሬ ጃኖራ ገብቷል። ልዑክ ቡድኑ የጎንደር አምባዎችን፣ የዳባት ተራሮችን አቆራርጦ አዲ ቀርኒ ቀበሌ፤ ጫካ በመድረስ ከጀግናው አርበኛ መሳፍንት ተስፉና ወታደሮቻቸው ጋር ተገናኝቷል።
የባልደራስ ልዑክ ቡድን በፓርቲው ፕሬዚደንት አቶ እስክንድር ነጋ የተመራ ሲሆን የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም (ቀለብ)፣ አስካለ ደምሌ፣ ዘቢባ ኢብራሒም እና ሶስና ፈቃዱም ተገኝተዋል።
ቡድኑ የአማራ ፋኖ እየከፈለው ላለው መስዋዕትነት ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል። አርበኛ መሳፍንት ተስፉም “እስከ ዛሬ ብቻችንን ታግለን ውጤት አስመዝግበናል። ከአሁን በኋላ የእናንተን እገዛ ካገኘን ይበልጥ ስኬታማ እንሆናለን” ብለዋል። ልዑክ ቡድኑንም አመስግነዋል።
አቶ እስክንድር ነጋ በበኩላቸው “አሁን የፖለቲካ አጀንዳ አይደለም የያዝነው፤ ኢትዮጵያን የማስቀጠል ጉዳይ ነው። በታሪክም ኢትዮጵያ ችግር ውስጥ በገባች ጊዜ ሁሉ በጀግንነታቸውን ሀገር የሚታደጉት ፋኖዎች ናቸው” ብለዋል።
ፋኖ አንድም ሀገር ብሔራዊ ችግር ሲገጥማት፤ ሌላም እንደ ህወሓት አይነት አጥፊ መንግሥታት ሲፈጠሩ የሚፈጠር መሆኑን የገለፁት አቶ እስክንድር የእነ መሳፍንት ነፍጥ ማንሳትም ከወያኔ መብቀል ጋር የተያያዘ መሆኑን አብራርተዋል።
Filed in: Amharic