>

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለአረንጓዴ ቢጫ ቀይዋ ባንዲራ እውቅና ሰጥቷል፤ መግለጫውንም በመግለጫ ሽሯል...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

የአዲስ አበባ ፖሊስ ለአረንጓዴ ቢጫ ቀይዋ ባንዲራ እውቅና ሰጥቷል፤ መግለጫውንም በመግለጫ ሽሯል…!!!
ዘመድኩን በቀለ

“…በትናንትናው ዕለት ከወያኔ ህወሓት ኢህአዴግ ባለ አምባሻው የዘንዶው ባንዲራ በቀር አንድም ሰው በአዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ይዞ፣ ለብሶ፣ አስሮ፣ አጊጦ አደባባይ መውጣት አይችልም። ክልክል ነው። ብሎ ዐዋጅ ዐውጆ የነበረው የአዲስ አበባው የአዳነች አቢቤ ፀረ ኢትዮጵያ የኦሮሙማው ፖሊስ ዛሬ የህዝቡን ንዴት፣ ወኔና ድፍረት አይቶ ሂሱን ውጦ ክልከላውን በይፋ አንስቶታል። የህዝብን ትእግስት ሁልጊዜ እንደፍርሃት ለሚቆጥሩ ጀማሪ አንባገነኖችም ትምህርት ነው። ይሄን የዘገቡ ሚዲያዎችም ኤዲት አድርገውታል።
•…የሴቶችን ቀሚስ ታስወልቅ እንደሁ እናያታለን የሚል መልእክት የደረሰው የኦሮምቲቲዋ አዳነች አቢቤ ፖሊስ፣ ሃገር ምድሩ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መሽቆጥቆጡን ሲመለከት አኣ በዚህ ሁኔታ ኢትዮጵያዊነትን ማሸነፍ አይቻልም በሚል ፖሊስ ድንፋታ ፉከራውን ስቧል። ዝምታን፣ ትእግስትን እንደፍርሃት የቆጠረው ፖሊስ ብዙም ሳይቆይ ተንፍሷል። ሱሪው ወልቆ መቀመጫው እየታየ የአሜሪካ ባንዲራ፣ የካናዳ ኮፍያ ከብሶ የማንም ጋጠወጥ በሚመላለስባት ኢትዮጵያ የገዛ ሃገርህን ሰንደቅ ዓላማ አታጌጥበትም ማለት የበዛ ጀዝባነት ነው። ፋሽስት ኢጣልያ እንኳ እንዲህ አልተበተም።
•…ለመናኝውም የፖሊስ ትዕቢቱ ለአሁኑ በርዶለታል። ኦርቶዶክሳውያንም በገዛ ሃገራቸው በእናት ሃገር ሰንደቅ ዓላማ ተንቆጥቁጠው፣ ደምቀው፣ ፏ ብለው ይውላሉ። እንዲህ መሆን ለጊዜው የማይቻለው፣ የኦሮሙማው ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን ቅኝ ግዛቱን ባሳረፈው በናዝሬትና በደብረ ዘይት፣ በአንዳንድ የወለጋ ግዛቶች ነው። በቡራዩ ከተማም የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መያዝ ብቻ ያሰቅላል። ያሳርዳል። እዚያም ቢሆን ኢትዮጵያዊነት ቆይቶ ያሸንፋል።
“… እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ  ‼
• ማርያምን ኢትዮጵያማ ታሸንፋለች።
Filed in: Amharic