>

ለኢትዮጵያና ሰንደቅ አላማዋ በዐቢይ አሕመድ፣ በመለስ ዜናዊና በቤንቶ ሙሶሎኒ መካከል ልዩነት የለም...!!! (አቻምየለህ ታምሩ)

ለኢትዮጵያና ሰንደቅ አላማዋ በዐቢይ አሕመድ፣ በመለስ ዜናዊና በቤንቶ ሙሶሎኒ መካከል ልዩነት የለም…!!!
አቻምየለህ ታምሩ

የኦሮሙማው ዐቢይ አሕመድ፣ የፋሽስት ወያኔው መለስ ዜናዊና የጣሊያኑ ፋሽስት ቤንቶ ሙሶሎኒ አድዋ ላይ ከፍ ብሎ የተውለበለበሰው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዳይውለበለብ በሕግ ያገዱ፤ ሲያውለበለብ የተገኘን በእስርና በሞት የቀጡ የርዕዮተ አለም ወንድማማቾች ናቸው።
እነሆ ዛሬ የኦሮሙማው ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያን የሚፋሟት የፋሽስት ወያኔንና የናዚ ኦነግን አርማ ማውለብለብ ፈቅዶ መተማ፣ አድዋ፣ ማይጨው፣ ካራማራና ባድመ ላይ የተውለበለበውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ማውለብለው ግን ሕገ ወጥ መሆኑን በድጋሜ ማወጁን አስታውቋል።
ልብ በሉ! በዐቢይ አሕመዷ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያን የሚፋለሟት የናዚ ኦነግና የፋሽስት ወያኔን አርማ ማውለብለብ የተፈቀደ ነው፤ የተከለከለው የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ማውለብለብ ነው።
እንግዲህ ጥያቄው አድዋ ላይ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ጀግኖች የድል ሰንደቅ አዲስ አበባ ላይ እንዳይውለበለብ በከለከለው በዐቢይ አሕመድና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይውለበለብ ባገደው በመለስ ዜናዊ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው የሚለው ነው?
ለኛ ለኢትዮጵያውያን አድዋ ላይ ከፍ ብሎ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አዲስ አበባ ውስጥ እንዳይውለበለብ በከለከለው የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ እና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ እንዳይውለበለብ ባዘዘው በቅኝ ገዢው የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስቴር በፍራንቼስኮ ክሪስፒ መንግሥት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
አድዋ ላይ የተውለበለበውን የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ አዲስ አበባ ውስጥ እንዳይውለበለብ በከለከለው በዐቢይ አሕመድ እና አድዋ ላይ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ጀግኖች ሰንደቅ ዓላማ አዲስ አበባ ውስጥ እንዳይውለበለበ በከለከለው በፋሽስቱ መሪ በቤንቶ ሙሶሎኒ መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?
ፋሽስት ወያኔ በመንግሥትነት ተሰይሞ በነበረበት ወቅት ያላደረገው፤ የኦሮሙማው አገዛዝ ያደረገው ነገር ቢኖር የናዚ ኦነግን አርማ ማውለብለብን መፍቀዱ ነው። ባጭሩ በፋሽስት ወያኔዋ ኢትዮጵያ ተከለከለ፤ በዐቢይ አሕመዷ ኢትዮጵያ ግን የተፈቀደ አንድ ነገር ቢኖር የናዚ ኦነግን አርማ በአደባባይ ማውለብለብ መፈቀዱ ነው። ከዚህ ውጭ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን እንዳይውለበለብ በሕግ ማገድን ጨምሮ በጸረ ኢትዮጵያዊነት በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ የፋሽስት ወያኔ የጭካኔ አገዛዝ ወራሽና ታናሽ ወንድም ነው።
በፋሽስት ወያኔ ዘመን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዳይውለበለብ ሲከለከል የተቃወሙ ብዙ ሰዎች ነበሩ። በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ አፓርታይድ አገዛዝ የናዚ ኦነግና የፋሽስት ወያኔ አርማዎችን እንጂ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዳይውለበለብ ሲከለክል እነዚያ የተቃውሞ ድምጾች የሉም።
የናዚ ኦነግና የፋሽስት ወያኔ አርማዎች እንዲውለበለቡ ተፈቅዶ መተማ፣ አድዋ፣ ማይጨው፣ ካራማራና ባድመ ላይ የተውለበለበው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ እንዳይውለበለብ ሲከለከል ዝም ብለው የሚያዩ ሰዎች የግለሰብ ከዳሚዎችና ውታፍ ነቃዮች እንጂ የኢትዮጵያ ፍቅር ያላቸው አይደሉም።
Filed in: Amharic