>
5:13 pm - Saturday April 19, 9102

አጨብጫቢው ዙምቢ ዳያስፖራ ዛሬ ለአቢይ ንግግር ያሰማው ጭብጨባ  (ወንድወስን ተክሉ....)

“አጨብጫቢ ትውልድ…!!!” 
 ሄኖክ አበበ

በዓሉ ግርማ በደርግ ግዜ በየስብሰባው በትንሽ በትልቁ ነገር የሚያጨበጭቡትን “አብዮታውያን” ተመልክቶ ‘ኦሮማይ’ ወይም ‘የቀይ ኮከብ ጥሪ’ መፅሃፉ ላይ  “አጨብጫቢ ትውልድ” ብሏቸው ነበር:: ትናንትና ቤተ-መንግስት ውስጥ በተደረገ የእራት ግብዣ ፕሮግራም ላይ አብይ አህመድ ገና ዓርፍተ-ነገሩን ሳይጨርስ ሲያጨበጭብ ያመሸውን ዳያስፖራ ቢመለከት ‘አጨብጫቢነት ዘመን ተሻጋሪ በሽታ ነው’ ብሎ በዓሉ ግርማ ይፅፍልን ነበር::
የጠቅላይ ሚንስቴሩ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻዎች አማካሪ ከሶስቱ ኤዲተሮች አንዱ በሆነበት Ethiopia in the Wake of Political Reforms በሚለው መፅሃፍ ላይ
የፖለቲካ ስልጣን በቅርቡ ያገኘ ማንኛውም ንቅናቄ ወይም ቡድን የመጀመሪያዎቹ ቀናቶቹን ከሚገባው በላይ ቃል መግባት:- ከዜጎቹ ቅቡልነት ለማግኘት መጣርና አብዛኛው ሰው ይቀበለዋል የሚባለውን ሃሳብ መደስኮርና መተግበር ላይ መጠመድ ያለ ሂደት ነው ይላል::
“It is only natural for any movement or group that newly acquires political power to use its early days in office to 𝚘𝚟𝚎𝚛𝚙𝚛𝚘𝚖𝚒𝚜𝚎 and attempt to buy legitimacy in the eyes of its citizens, 𝚝𝚊𝚕𝚔𝚒𝚗𝚐 𝚊𝚗𝚍 𝚊𝚌𝚝𝚒𝚗𝚐 𝚋𝚛𝚘𝚊𝚍𝚕𝚢 𝚒𝚗 𝚕𝚒𝚗𝚎 𝚠𝚒𝚝𝚑 𝚠𝚑𝚊𝚝 𝚝𝚑𝚎 𝚖𝚊𝚓𝚘𝚛𝚒𝚝𝚢 𝚊𝚛𝚎 𝚕𝚒𝚔𝚎𝚕𝚢 𝚝𝚘 𝚊𝚙𝚙𝚛𝚘𝚟𝚎 𝚘𝚏.”
ያው አብይ ሰዎችን የሚፈልጉትን ነገር እያሳየህ ወደጉድጏድ ወስደህ ጣላቸው ብሎ በመፅሃፉ የፃፈው ነፀብራቅ ማለት ነው:: በዚህ የብዙሃኑን ሃሳብ ና ቀልብ የመግዛት እሳቤ ነው አብይ አህመድ በየሄደበት ታዳሚው ምን እንደሚያስጨበጭበው በመረዳት እርስ በእርስ የሚቃረኑ ሃሳቦችን እንዲሁም ውሸቶችን እዚህም እዚያም እየደሰኮረ ሰውን ሁሉ አጨብጫቢና አሸብሻቢ አድርጎት የቀረ:: የሚገርመው ግን ይህ የመድረኩን ድባብ እያዩ መደስኮር ከመጀመሪያዎቹ የስልጣን ግዚያቶች አልፎ የአብይ መንግስት መገለጫ ይሆን ዘንድ ቀን ከቀን መደጋገሙ ነው::
በትንሽ በትልቁ:- በእውነቱ በውሸቱ:- ለሃቁ ለሴራው:- ለስድቡ ለምስጋናው ለገዥዎች የሚያጨበጭብና የሚያሸበሽብ ልሂቅ: ከተሜ: አርሶ አደር:- ቢሮክራት: ዳያስፖራ: ሚድያ ይዘን ህዝብን የሚንቅ ውሸታም መሪ እንጂ ሃገሪቱን በቅንነት እየመራ ወደ ዴሞክራሲ የሚያሻግር መንግስትና መሪ ልንፈጥር አንችልም:: የመንግስትን ስህተት ጀስቲፋይ ለማድረግ ደፋ ቀና ከማለት እንዲሁም ከአጨብጫቢነትና ከአሸብሻቢነት ተላቀው የመንግስት ሹመኞችን ስራና ውሳኔ መተቸት:- መንቀፍ:- መጠየቅ የሚችሉ ሚድያዎችና ልሂቃን:- ካድሬና ቢሮክራት ያስፈልጉናል::
አጨብጫቢው ዙምቢ ዳያስፖራ ዛሬ ለአቢይ ንግግር ያሰማው ጭብጨባ 
      ወንድወስን ተክሉ 
• «በእርግጠኝነት የምናገረው፣ ዘንድሮ ሀገሬን ብላችሁ ጥሪያችንን ተቀብላችሁ የመጣችሁ ሰዎች ባላጋንን 90% እጅግ በጣም ደስተኞች ናችሁ …….   . .,. 👏👏👏👏 የዳያስፖራው ጫጫታና ጭብጨባ እንደ ነሀሴ በረዶ ሲያስተጋባ  ተደመጠ ……
• ከዚያም ቀጠለ   « ምክንያቱም በልባችሁ ይዛችሁ የመጣችሁት እዚያ እያላችሁ ሙዲያዎች የሰጣችሁን የፈራረሰች ኢትዮጲያ ሆኖ እዚህ ስትደርሱ ግን ጽዳት ውበት ይህንን የመሰለ አዳዲስ የመዋያ ስፍራዎችን ስታዩ ማንኛውምን ኢትዮጲያዊ የሚያስደስት መሆኑን  ጥርጥር ስለሌለኝ ነው….,» አሁንም እልም ያለ ጫጫታ ፉጨትና ጭብጨባ ቀለጠ 👏👏👏👏
• ቀደዳውን እሱም ለጠቀበት « የ No More Movement ከዛሬ ጀምሮ አያስፈልግም …. እናንተ ባላችሁበት ሀገር አሜሪካ ካናዳ ሆናችሁ  አማራ ነኝ ኦሮሞ ነኝ ትግሬነት አያስፈልጋችሁም…..»  ጩህትና ጭበጨባ 👏👏👏👏👏
• «አሜሪካ ላይ እንደጎርጎራ የሚያምር ሪዞርት የለም……» ጭብጨባና ሁካታ
በ 1 ሚሊዮን ዶላር – እያንዳንዱ ዳያስፖራ አንድ ሚሊዮን ዶላር ካለው ባለቤትና ባለመሬት ነገውኑ እናደርጋለን ጩህትና ጭብጨባ👏👏👏👏👏
• « ሰሞኑን ትንሽ ውዥንብር ስላለ ኢትዮጲያ ውስጥ ዲያስፖራውም በትንሹ ስላዘነ ጥቂት ሀሳቦች ….   ….ዳያስፖራው አቌርጦት ጩህቱንና ጭብጨባውን አቀለጠ 👏👏👏👏 …. ጥቂት ሀሳቦች እሰነዝራለሁ ………
እናንተን በጥቂቱ ያሳዘኑ ውሳኔዎቻችን በሙሉ የተወሰኑት ውሳኔዎች በሶሥስት መሰረታዊ መስፈርትነት በመጠቀም ነው….. . .
በማለት ወንጀለኞቹን እስረኞች የፈታበትን እና No More movement የሰረዘበት
•ሉዓላዊነት
• ብሄራዊ ጥቅም
•ሀገራዊ ክብር
ምክንያት ነው እልም ያለ ጩህትና ጭብጨባ 👏👏👏👏👏👏
• ኢትዮጲያ ጠላት የምትለው እና በጠላትነት የምትፈርጀው አንድም ጠላት የሆነ ሀገር የለም…………ጩህትና ጭብጨባ 👋👋👋👋
• አሜሪካ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ከጀርመንና ከጃፓ ጋር በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተዋግታ ግን በማርሻል ፕላን አልምታለችና እኛም ስንፈታ በዚህ እሳቤ ነው ጩህትና ጭብጭባ  👏👏👏👏👏
• የአምስት አመት ኮንትራት የሰጣችሁን ሀገር ለማፍረስ አይደለም  ….  … ጩህትና ጫጫታ
👏👏👏👏👏
•እና ይገርማችኋል እኛም ደንግጠን ነበር…..እስረኞች ሲፈቱ ደንግጠናል …..ጩህትና ጭብጨባ
👏👏👏👏👏
• ከእስር ቤት የተፈቱት ሰዎች ከእኔ በላይ የሰደቡት ከእኔ በላይ ያዋረዱት ሰው የለም…..
ጩህትና ጭብጨባ👏👏👏👏
• ብልጽግና ውስጥ ከወራት በፊት እስረኞቹን እንፍታ ብለን ተወያይተንበታል…..
ጩህትና ጭብጨባ 👏👏👏👏
• ወታደሩ በጋሸና ግንባር ሽንት እየጠጣ ነው የተጋዘው ጩህትና ጭብጨባ 👏👏👏
• በእኛ ውሳኔ ሂደቱን ለእኛ ተውት ውጤቱን ጠብቁ ያማረ ይሆናል …..ጩህትና ጭብጨባ👏👏👏👏
• የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በአዲስ አበባ እንዲካሄድ በማድረግ ደረጃ የእስረኞች መፈታትና የእናንተ ዳያስፖራ እግረ እርጥቦች ያመጣው ውጤት ነው …….ቅልጥ ያለ ጩህት ጭብጨባ ….👏👏👏👏
• ሰሞኑን ለመከላከያ አመራሮች የሰጠነው ማእረግና ሽልማት ከእስረኞቹ መፈታት በላይ በጣም ነው የረበሸኝ ያሳዘነኝ….  ጩህትና ጭብጨባ👏👏👏👏
፠ ዳያስፖራው ልክ እንደ ደርግ ዘመኑ በየደቂቃው የሚያጨብጭብ ሆኖ ታይታል። ሲወረፍም ያጨበጭባል። ሲነቀፍም ያጨበጭባል ።
እንዲህ አይነት አጨብጫቢ ዳያስፖራ ከዚህ በፊት እንዳልኩት በጃንክ ምግብ አእምሮው የዛገ ዙምቢ Zombies ናቸው።
Filed in: Amharic