>
5:33 pm - Tuesday December 5, 1522

የባልደራስ ልኡካን ቡድን ትምህርት ቤታቸው፣ መኖሪያ ቤታቸውና ቤተ እምነታቸው የፈረሰባቸውን ወገኖች ጎበኘ....!!!! ባልደራስ

የባልደራስ ልኡካን ቡድን ትምህርት ቤታቸው፣ መኖሪያ ቤታቸውና ቤተ እምነታቸው የፈረሰባቸውን ወገኖች ጎበኘ….!!!!
ባልደራስ

 * በጦርነት የወደመውን ገረገራ ት/ቤት 
በአማራ የተለያዩ አካባቢዎች በጦርነት የተጎዱ ቦታዎችንና ጀግኞች ፋኖዎችን እየጎበኘ የሚገኘው ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ልዑክ በጦርነት የተጎዳውን ገረገራ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ዛሬ ቅዳሜ ጥር 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ጎብኝቷል። ከመማሪያና ማስተማሪያ ቁሳቁሶች ጀምሮ ንብረቶች በአመዛኙ ወድመዋል። በትግርኛ ቋንቋ የተፃፉ መፈክሮችም በየመማሪያ ክፍሎች ይገኛሉ።
የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ብርሐኑ ምህረቴ “የተማሪዎች የትምህርት  ሰነዶች ሙሉ በሙሉ ጠፍተዋል። የተማሪዎች እጅ ላይ በነበረ መረጃ ነው ትምህርቱን የቀጠልነው። የትምህርት ቤቱ ንብረት  ወድሟል። መፅሐፎችን አቃጥለዋቸዋል”ብለዋል።
መንግሥት ትምህርት ቤቱን መልሶ ለማቋቋም ቃል ከመግባት ውጭ እስከ አሁን የወሰደው ተግባራዊ እንቅስቃሴ አለመኖሩንም ርዕሰ መምህሩ ተናግረዋል። የመማር ማስተማር ሂደቱ ቢጀመርም የተማሪዎቹ ቁጥር መቀነሱንም አብራርተዋል። ለዚህም እንደምክንያት የተጠቀሰው አካባቢው በጦርነት በመውደሙ ማሕበረሰቡ ልጆቹን የማስተማር ምጣኔ ኃብታዊ አቅም በማጣቱ መሆኑን ርዕሰ መምህር ብርሐኑ ምህረቴ አስረድተዋል። ትምህርት ቤቱ በአሁኑ ጊዜ ከ1, 100 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።
ለመልሶ ማቋቋሚያ የትምህርት ቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ለምትፈለጉ፦
-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000224015465 ገረገራ አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት
ስልክ፦+2519 14 06 49 82 ብርሐኑ ምህረቴ፤ ርዕሰ መምህር
*****
 * በደብረ ዘቢጥ በጦርነቱ ቤታቸው የፈረሰባቸው
በአቶ እስክንድር ነጋ የሚመራው የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ልዑክ ቡድን ከፍተኛ ጦርነት በተደረገበት ደብረ ዘቢጥ ቤታቸው የፈረሰባቸውን መምህር ታምራት ማሞን ጠይቋል።
ወያኔዎች በከባድ መሳሪያ ከተማውን ሲደበድቡ ቤቱን በመድፍ ማውደማቸውንም መምህር ታምራት ገልፀዋል።
 “ሙሉ ዕቃው ወድሟል። አሁን ተከራይተን ነው የምንኖረው። በመንግሥት ሠራተኝነት አቅም 15  ዓመት ሙሉ ያፈራሁት ጥሪት ወድሞቦብኛል” ብለዋል መምህሩ።
መንግሥት መልሶ ለማቋቋም ተገቢውን ድጋፍ  ያላደረገላቸው መሆኑንም ገልፀዋል። “ሌላው ቀርቶ ኬንዳ (ተወጣሪ ላስቲክ ማለታቸው ነው) እንኳን አልሰጠንም”  ብለዋል።
አሁን ካለው የኑሮ ውድነት አንፃር በ15 ዓመት የገነቡትን እና የወደመውን ንብረታቸውን መልሶ ለማቋቋም እስከ 30 ዓመት ሊወስድባቸው እንደሚችልም መምህር ታምራት ተናግረዋል።
መምህር ታምራት ማሞን ማግኘት የምትፈልጉ፦
ስልክ ቁጥር፦ +2519 12 34 82 14
* በጦርነት የተጎዳውን ጨጨሆ መድሀኃኒዓለም …!!!!
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ልዑክ ቡድን የታሪካዊውን ጨጨሆ መድኅኒዓለም ደብር ዛሬ ቅዳሜ ጥር 14 ቀን 2014 ዓ.ም. ጎብኝቷል። ከ1, 200  ዓመት በላይ እንዳስቆጠረ የሚነገርለት ደብሩ በሮቹ በጥይት ተበሳስተዋል። የውስጥና የበረዳ ጣሪያው በከፊል ፈርሷል።
በአካባቢው አንዳች ወታደራዊ ጉዳይ የሌለበትን ቤተክስቲያንና ቅርስ በጥይት መደብደቡ የወያኔን አረመኔነትና ሀገር አፍራሽነት እንደሚያረጋግጥ የልዑክ ቡድኑ መሪ አቶ እስክንድር ነጋ ተናግረዋል።
ልዑኩ ደብሩ ውስጥ በደረሰበት ንጋት 12 ሰዓት ላይ አንዳች ምዕመንም ሆነ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓት አልነበረም። ደብሩ ወደ መደበኛ አገልግሎቱ አልተመለሰም።
 ከወራሪው የትግራይ ሃይል ጋር ከፍተኛ ፍልሚያ የተደረገበትን የሊማሊሞ፣ ዘሪማ፣ ጨው በር ግንባር
        ቡድኑን በክብር ተቀብለው ያስጎበኙት የፋኖ ብርጌድ መሪ በመሆን ጦርነቱን እየመሩ የሚገኙት ሻለቃ ሰፈር መለሰ ናቸው።
Filed in: Amharic