ዋ! ወይብላ ማርያም !!!
መስፍን ማሞ ተሰማ
ለኢትዮጵያ ሉዓላዊነት እያውለበለብናት ከጠላት ወራሪ ጋር ስንዋደቅ መንግሥት የማያግዳት፣ በነፃነት በአደባባዮች ስናውለበልባት ደግሞ በመንግሥት በታዘዙ የፀጥታ አካላት በጥይት የምንቆላባት በቆመጥ የምንቀጠቀጥባት ንፁሗ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሠንደቅ ዓላማችን !!! በወይብላ ማርያም የጥምቀት በዓል ላይ በተውለበለበችው የኢትዮጵያችን ሠንደቅ ዓላማ ምክንያት እንደ ሞሶሎኒ ጥቁር ሸሚዝ ለባሽ ፋሽስት ወታደሮች በሀገር በቀል ፀረ ኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ የመንግሥት የፀጥታ ኃይላት በጥይት ተደብድበው ህይወታቸው ያለፈ ሠማዕታትን ፈጣሪ አምላክ ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን! ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድና ለኢትዮጵያውያን መፅናናትንና ፅናትን ይስጥልን!! በግፈኛ ፀረ ሠንደቅ ዓላማ የመንግሥት ኃይላት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸውም አምላክ በምህረት ይዳብስልን!! በተደጋጋሚ ፍትህን ከመንግሥት ተነፍገናልና – ፍትህን ለማግኘት ስለ ፍትህና ስለ ሠንደቅ ዓላማችን ነፃ መውጣት አምርረን እንታገላለን !! ገዳዮች ከዘርና ከአድልዖ በፀዳ ፍትህ እስኪዳኙ ከቶም አናርፍም፣ ነገም ስዚህችው የነፃነት ሠንደቅ ዓላማችን ይገድሉናልና !!! የብልፅግና መንግሥት መቆሚያ ላጣው ተደጋጋሚ የሠንደቅ ዓላማችን ጥቃት ቀጥተኛ ተጠያቂ ነው – እስከ ዛሬ የወያኔን እግድ ተግባራዊ እያደረገ ነውና !!!!