>
5:31 pm - Monday November 12, 9629

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ  ተነስቷል፤ ዛሬስ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራን አሳሪው ፈችው ማን ነው?! (መረጃ ቲቪ)

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ  ተነስቷል፤ ዛሬስ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራን አሳሪው ፈችው ማን ነው?!
መረጃ ቲቪ

ለጥያቄ ትፈለጋለህ ተብሎ ከመኖሪያ ቤቱ ከተወሰደ እና ያለፍትህ እስር ቤት እየማቀቀ ከሆነ 49 ቀናትን ያስቆጠረው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ጉዳዩን የሚከታተልለት ማነው?!
የገላን ከተማ ፍርድቤት በነፃ ያሰናበተው ሲሆን በእለቱ ጉዳዩን የያዘው ፍርድቤት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታይ መወሰኑ የሚታወስ ነው። ሆኖም አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በትናንትናው እለት ተነስቷል ስለዚህ የወንድማችን #የታምራት ነገራን ጉዳይ የሚከታተለው ማነው?!
ክቡር የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር #Daniel_Bekele #ዳንኤል በቀለ መልሱን በአስቸኳይ እንጠብቃለን!
Filed in: Amharic