>

ዘመነ ካሴ ላይ የማደኛ ማዘዣ አውጥተዋል! (ሰለሞን አላምኔ)

ዘመነ ካሴ ላይ የማደኛ ማዘዣ አውጥተዋል!
“ሊበላህ የመጣውን ጅብ በልተኸው ተቀደስ……!!!”
ሰለሞን አላምኔ

 

*…. ዘመነ ካሴ ይህንን ብሏል
 
ለሚመለከተው ሁሉ …!
ቆሜ እየሄድሁ የኔን እጅ ይዞ ማሰር አይቻልም።ባራት አያት ሽንፈትን አላውቅም።… ከሞትሁ በኋላ ሬሳዬን ስትፈልጉ ለውሻ ስጡት።…
በቁሜ ግን ማንም ደንቆሮ እጄን ይዞ አያስረኝም።…..በሚወዱኝና በምሳሳላቸው ታናሾቼ እንደምጠበቅም እወቁ።… ከድንግል ልጅ በታች  
ጀግኖች ናቸው የሚጠብቁኝ።
ድል ለአማራ ህዝብ!
/አዲስ ትውልድ፥አዲስ አስተሳሰብ፥አዲስ ተስፋ!/
ህዝብ መሪውን ይፈጥራል። በተለይም እንደ አማራ በዚህ ጭንቅ ሰዓት አደራጅቶ ከፊት ተስልፎልህ አብረን ለህዝብ እና ለሀገር እንዋደቅ የሚልህን መሪ ደጋግመህ ልትፈጠር እና የፈጠርከውን መሪ ደግሞ እንደ አይን ብሌንህ በቀንም በማታም ለትጠበቅው የግድ ግድ ግዴታ አማራጭህ ነው።
#መራዊ ላይ ወጣ ገባ በዛ ያለህን የአማራ ህዝባዊ ሃይል ዋና ሰው Tilahun Abeje ሰምተህ ያሳየኸው ንቅናቄ ይበል ደግ የሚያሰኝ ነው። አባይን ተሻግሮ  የሚመጣውንም ሆነ ከዛው ከቅየህ ታዝዞ ለሚመጣ ማነኛውም ሃይል ፋኖን ሊያግዝ ሊረዳ እና ሊያመስግን እንጅ ሊበላ ከሆነ የመጣው “ሊበላህ የመጣውን ጅብ በልተኸው ተቀደስ” ነው መልሴ።
በዚህች 4ወር ውስጥ ብቻ ዘመነን ለመብላት ከ3 ጊዜ በላይ ሙከራ ተደርጓል። ልብ በል የእስካሁኑ ሁሉ ሙከራ ነው።
#እኔምዘመነካሴነኝ ‼ይህን ከተግባባን ላለፉት 27 ዓመት በርካታ መሪዎችን አስበልተን፧ ነብዩን ጀኔራል አሳምነው ፅጌን በተረኞቹ ያን ጀግና ያን ነብይ ያን ልባም ያን ግራማሞገሳም እንደዋዛ አስበልተን ለማያባራ እልቂና መከራ አይናችን እያየ እንደተዳረግነው ሁሉ ከሞት ከስደት ከውርደት እና ከእልቂት ተደራጅተን ታጥቀን በአንድ ቆመን ነፈሰ በላውን ስርዓት እናስወግድ ያለውን የአማራ ህዝባዊ ኃይል ሰብሳቢ ዘመነ ካሴን ዳግም ካስበላን ራስን እንደ ፊዩዝ መቁጠር ነው‼
ስለሆነም መላው አማራ መሪህን በቀን በሌት ልክ እንደኔ ጠብቅ። በጎጥ ስር ተደብቆ ጆከር ካርታ እያወጣ ሊያዘናጋህ የሚሻውን ጎጠኛ ዞር በል በለውና መሪህን ጠብቅ። እንደ ድሮው ህውሃትን የታገለ ሁሉ ጀግና መስሎህ ዛሬ መሪህን ሊያስበላ የሚቅበዘበዘውን ጎጠኛ እነቂ ነኝ ባይ ባናትህ ቁም በለውና መሪህን ጠብቅ። ከዛ ውጭ ለሚሆነው ለማለት…
መውጫ :-  በዘመነ ካሴ ላይ ለሚፈጠር ማነኛውም ነገር ተጠያቂው በኔ እይታ……
…..የብዓዴን ስራ አስፈፃሚ እና የክልሉ ፕሬዘዳንት
…..ያልጠራ ግን የሚጠራ በአብን ካባ ስር የተጠለለ ጎጠኛ (ለአማራ ህዝብ እና ለዘመነ ካሴ የቆመ በሽዎች የሚቆጠር አብናውያን እንዳሉ ልብ ይሏል!) ፣
…..ከብልፅግና ጋር አንሶላ የተጋፈፉ የአብን አመራሮች
…..በኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ስር የተደበቁ፣ የነ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፣ አንዳርጋቸው ፅጌ፣ ነዓመን ዘለቀ፣ የብልፅግናን ወንጌል የተቀበለ አማራ ጠል ስብስብ
…..ነገሩን ልብ ያላለው እና ከስህተቱ የማይማር ራሱን አማራ ነኝ ብሎ የሚቆጥሩ በዋናነት በዘመነ ካሴ እና በአማራ ህዝብ ላይ ለሚደርሱ  ነገሮች የመጀመሪያ ተጠያቂዎች ናቸው።
Filed in: Amharic