>

የመጀመሪያው ዘመነ መሳፍንት 1769-1855 ወይም የፌዴራሊዝም ሙከራ (አበበ ሀረገወይን)

የመጀመሪያው ዘመነ መሳፍንት 1769-1855 ወይም የፌዴራሊዝም ሙከራ
አበበ ሀረገወይን

የመጀመሪያው ዘመነ መሳፍንት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ከ፲፰ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀምሮ እስከ ፲፱ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ድረስ የተከሰተ ዘመን ነበር፡፣
በወቅቱ የየአካባቢው መሳፍንት ኃይል የገነነበትና እርስ በርሳቸው የሚዋጉበት እንዲሁም ዋናው ንጉስ ተብዬው ሥልጣኑ ከመዳከሙ የተነሳ ከጎንደር ከተማ ውጭ እምብዛም ተሰሚነት ያልነበርበት ወቅት ነበር። በአንድ ወቅት እንግሊዛዊው ጄምስ ብሩስ ጎንደርን ጎብኝቶ እንደ ዘገበው ጎንደር ከተማው ራሱ ወምበዴ የበዛበትና በየመንገዱ ያልተነሳ ሬሳ የሚታይበት ቦታ ሆኖ ነበር።
ከነበረው አለመረጋጋት የተነሳ ከጎንደር ከተማ ተነስቶ ወርቃማው ዘመን ሊባል የሚገባው እየተስፋፋ የነበረው ስልጣኔ የኮሰመነበት፣ እንዲሁም ህብረተሰቡና ባህሉ ወደፊት አንድ እርምጃ መራመድ አቅቶት እየበሰበሰና እየወረደ የነበርበት ወቅት ነው። ከትውፊት አንጻር የዚህ ዘመን ጅማሬ የሚቆጠረው ራስ ሚካኤል ስሑል ዳግማዊ ዓፄ ኢዮአስን ሚያዝያ ፳፱ ቀን ፲፯፻፷፩ ዓ.ም. ሲያስገድለው ሲሆን በተቃራኒው የዘመኑ ፍጻሜ ዳግማዊ ዓፄ ቴዎድሮስ የካቲት ፬ ቀን ፲፰፻፵፯ ዓ.ም ንጉሠ ነገሥት ሆነው ስልጣን ላይ ሲወጡ ነው።
ከዊኪፒዲያ ተውሶ ያለበት
Filed in: Amharic