>

የአንዳንድ ፖለቲከኞች እና የ 'አባቶች ' ነገር  (አንዱአለም ቦኪቶ ገዳ)

የአንዳንድ ፖለቲከኞች እና የ ‘አባቶች ‘ ነገር 

አንዱአለም ቦኪቶ ገዳ

እንደው ፖለቲከኞቹስ የፈለገ ይሁኑ እንዴት የሃይማኖት አባቶች በዚህ ደረጃ ስሜታዊ ይሆናሉ!?
ትላንት የትግራይ አባቶች ከማእከላዊው ቅዱስ ሲኖዶስ የተነጠለ የትግራይ ጠቅላይ ቤተክህነት እናቋቁማለን ብለዋል!
ምን ጉድ ነው ይሄ!?
እንዴትስ ሃይ ባይ ጠፋ!?
የሺ አመታት ታሪክ ያላት ቤ/ክርስትያን እንዲህ ስትከፋፈል ጉዳዩስ እንዴት የጥቂት አመታት ታሪክ ካለው የመስቀል አደባባይ ንትርክ ያነሰ አጀንዳ ይሆናል!?
በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ  አባቶች ሽምግልና ልከው ተው አይሏቸውም ወይ!?
ምናልባት ትግራይ ትገነጠልና እራሷን የቻለች ሃገር ትሆን ይሆናል!
 እንዴት ግን ክፍፍሉ ከቤተክርስትያን ይጀመራል!?
በቃ የማንም ጠባብ ብሄርተኛ ሁላ ሃገር ለማፍረስ ሲያስብ የሰፈር እና የጎሳ  ቤተክህነት ለማቋቋም የሚርመጠመጥባት ሃገር ይዘን ቀረን ማለት ነው!?
ሃገሬ ወዴት እየሄድሽ ነው!?
ይሄ ነገርስ የመጨረሻው መጀመሪያ ይሆን?!
ያሳፍራል!
አባቶች ይህን የነቀዘ ፖለቲካችን የፈጠረውን የቤተ ክርስትያን ክፍፍል አስወግደው የቤተክርስትያኗ ህብረት የሀገር አንድነት መሰረት እንዲሆን አንድ ነገር ያደርጋሉ ብዬ አስባለሁ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን አስባት!
Filed in: Amharic