>

በባህርዳር ከተማ በንፁሀን ዜጎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ያደረሱ በህግ ፊት ይቅረቡ! [አንድነት - መግለጫ]

Bahir Darአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በትናንትናው ዕለት ታህሳስ 10/ 2007 ዓም በባህርዳር ከተማ መንግስት ኃይሎች የጥምቀት ክብረ በዓል ታቦት የሚያርፍበትን ቦታ ሊፈርስ ነው በመባሉ ምክንያት ስሞታ ለማሰማት ወደ አስተዳደሩ ጽ/ቤት ያመሩ ንፁሃን ዜጎች ላይ የመንግስት ኃይሎች የወሰዱትን የግዲያና የድብደባ ህገወጥ ተግባር ያወግዛል።

ኢህአዴግ ቤተ እምነቶችን በየምክንያቱ መዳፈር የጀመረው ዛሬ አይደለም፤ መንግስተ በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ አይገባም የሚለውና የሀይማኖት ነፃነት ማክበር ሲገባው፤ ስለኃይኖታቸው ጥያቄ የሚያነሱትን ዜጎች መግደል፣ ማሰርና ማሳድድ ተያይዞታል። ከአሁን በፊት በሞስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የፈፀመውን ግፍና የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ አሁን ደግሞ በባህር ዳር ከተማ የኦርተዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች ላይ የወሰደው የኃይል እርምጃ ለሰው ህይወት መጥፋትና ለአካል መጉደል ምክንያት ሆናል፤ አንድነት በዚህ ጭፍጨፋ ህይቀታቸውን ያጡ ዜጎች ቤተሰቦች መፅናናትን እየተመኘ፤ እነዚህ ወንጀሉን የፈፀሙ፣ ያዘዙና ያስፈፀሙ አካላት በየደረጃው በህግ ፊት ቀርበው እንዲጠየቁ ለማድረግ አስፈላጊውን ትግል የምናደርግ መሆናችን ለማሳወቅ እንፈልጋለን።

ድል የህዝብ ነው!
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ታህሣሥ 11 ቀን 2ዐዐ7 ዓም
አዲስ አበባ

Filed in: Amharic