>

የኢትዮጵያ አምላክ ሆይ!?

የኢትዮጵያ አምላክ ሆይ!?




የኢትዮጵያ አምላኮ ሆይ
በሰማይ የምትኖር
ስምህ በሰጠኸን መሬት
ይመስገን
የሚረዳን ሩህሩህ መንግስት ስጠን
ሞታችንና ስቃያችን በዝቷልና
በደላችንን ተመልከት እንደገና
ለሚገድሉን ልቦናቸው ይመለስ ዘንድ ፈቃድህ
ይሁን
እጇቿን ትዘረጋለች ባልከው መሬት ጭካኔ
አበዛን
የዘረኝነት አስተዳደር አጥፋልን
እኛም ለአፍሪካውያን ነፃነት ምሳሌ ነበርንና
ያጣነውን ነፃነታችን  መልሰው እንደገና
ከጥጋብ ብዛት እርስበርስ እየተጫረስን ሰለሆነ
እድሜ ዘመናችን እንዳይሆንብን ቀርቶ የባከነ
ሀጢያታችን ለቀጣይ ትውልድ እንዳያልፍ
ፈቃድህ ይሁን
ከሰጠኸን መሬት ኣጥፋልን መርገማችን
ዘላለማዊው የማይፈርስ መንግስት ያንተነውና
ለዘላለሙ አሜን!!!

ዘምሳሌ
Email: zemesale@gmail.com

Filed in: Amharic