>

እጅግ አሰቃቂው የመተሃራ ጭፍጨፋ ...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

እጅግ አሰቃቂው የመተሃራ ጭፍጨፋ …!!!

ዘመድኩን በቀለ

*… የኦሮሞ ነፃ አውጪዎቹ በጥይት እሩምታ ጭፍጨፋውን ከፈጸሙ በኋላ በመጡበት አኳኋን ዘና ብለው ህዝብ ወደማያውቀው መንግሥት ግን ወደሚያውቀው  ካምፓቸው በሰላም መመለሳቸው ነው የሚነገረው።
“…ትናንት መጋቢት 8/2014 ዓም ምሽት 3:00 ዓት ሲሆን በምሥራቅ ሸዋ ፈታሌ ወረዳ መተሃራ አልጌ በምትባል ቀበሌ የተፈጸመ አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ነው። አልጌ ማለት በመተሃራ ስኳር ፋብሪካ ውስጥ ሲያገለግሉ ኖረው በስተመጨረሻ ጡረታ ሲወጡ እዚያው የሚኖሩባት መንደር ናት። ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ሽንኩርት እያመረቱ ህይወታቸውን የሚገፉባት የጡረተኞች መንደር ናት።
“…ካለፉት ወራት ጀምሮ በየሳምንቱ በችርቻሮ ሰው ሲገድል የከረመው ኦነግ ሸኔ የሚባለው የኦህዴድ ፕላን ቢ ጨፍጫፊ ቡድን ትናንት ምሽት 3:00 ሰዓት ሲሆን ግን ወደ አልጌ መንደር በመምጣት በዚያ የሚኖሩ ወጣቶች ኳስ እያዩ፣ ፑል እየተጫወቱ እየተዝናኑ ወደሚያመሹበት እና ጊዜአቸውን ወደሚያሳልፉበት ቤት በመሄድ፣ በዚያም እንደደረሱ መሣሪያቸውን በመምዘዝ በመዝናኛዋ ውስጥ በነበሩት ወጣቶች ላይ የጥይት እሩምታ በማዝነብ ከደርዘን በላይ ሰላማዊ የጡረተኛ ልጆችን በመረሸን ለኦሮሞ ህዝብ ታላቅ ድል በማጎናጸፍ፣ የኦሮሞ መንግሥትና የኦሮሚያን ህዝብ በማስደሰት ግዳጃቸውን ፈጽመው በድል ተመልሰዋል።
“…የኦሮሞ ነፃ አውጪዎቹ በጥይት እሩምታው ጭፍጨፋውን ከፈጸሙ በኋላ በመጡበት አካኋን ረጋ ብለው ህዝብ ወደማየውቀው መንግሥት ግን ወደሚያውቀው ወደመጡበት ካምፓቸው በሰላም መመለሳቸው ነው የሚነገረው። የጥይት እሩምታ የሰማው ሀዝብ ተሰበሰ። የሞቱትንም ለመሞት እያጣጣሩ ያሉትንም አነሡ። አምቡላንስም መጣች። ቢያንስ ደማቸው የሚፈሰውን ለማሳካምም ጉዞ ተጀመረ። ድንገት ባለሥልጣናት ደወሉ። አምቡላንሱ ይመለስ አሉ። አምቡላንሱም ተመለሰ። የልጆቹም ደም ፈሶ አለቀ። ሞቱ።
“…ቀጥሎ መብራት፣ የስልክም የሞባይል፣ የኢንተርኔት አገልግሎትም በአካባቢው ብቻ ተለይቶ እንዲጠፋ ተደረገ። ትራንስፖርትም ተቋረጠ። ቀደም ሲል የተቋረጠው የባጃጅ አገልግሎትም በድጋሚ ተከለከለ። ተጎጂዎችን ለማነዳን ማንም እንዳይንቀሳቀስ ተደረገ። መከላከያም፣ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም፣ የከተማው ፖሊሶችም የት እንደገቡ ሳይታወቅ ሌሊቱ ነጋ። ጠዋት ኦሮሚኛ ተናጋሪው የመከላከያ ሠራዊት ጅንን እያለ መጣ። እሱን ተከትሎም የኦሮሚያ ልዩ ኃይልም ተብዬውም መጣ። ምንአልባትም ማታ ሸኔ የነበሩት ናቸው አሁን ፖሊስ ሆነው የመጡት ይላሉ ታዛቢዎች። ሹማምንቱም ኮራ እያሉ መጡ።
“…ነፍሳቸው ያልወጣች ተጎጂዎች ለህክምና ሲፈቀድላቸው ሟቾችን ግን ህዝቡ ከመቅበሩ በፊት በግዳጅ ወደ ስብሰባ እንዲመጣ ተጠራ። እኔም ስብሰባው መሃል እንድገኝ ሆነ። ሰብሳቢዎቹ የመንግሥት አካላት ችግሩ ዳግም እንዳይከሰት ምን እናድርግ? አትፍሩ፣ ሃሳብ ስጡ፣ ዝምካላችሁ ግን ችግሩ ይቀጥላል ወዘተ እያሉም ወተወቱ። አንደኛው ተሰብሳቢ በድፍረት ” ልጆቻችንን ብንቀብር አይሻልም? ሬሳ አስቀምጠን ስብሰባ ምን የሚሉት ነው? ልጆቹ እንዳይተርፉ እንኳ አምቡላንሱን ከመንገድ የመለስከው አንተ አይደለህ? አሁን ይሄን አልክ ብለህ ልታስረኝ ትችላለህ። ልሞትም ጭምር። እባካችሁ ተዉን። ልጆቻችንን እንቅበርበት አለ። ጭብጨባ። ሌላው ህዝብ ግን ዝም ጭጭ። ሰብሳቢውም ለእናንተ ብለን ነው እንጂ እኛ እኮ ቢዚ ነን። ሌላ ቦታ ስብሰባ ትተን ነው እዚህ የመጣነው ብሎም አረፈው።
“…አሁን መተሀራ አልጌ 13 ልጆቿን በአንድ ደቂቃ አጥታ የሀዘን ማቅ ለብሳለች። ለአባድር 4ኛ እና 3ኛ ካምፕ ኑዋሪዎች በሙሉ የሀዘን መብረቅ መታቸው። አስከሬኖቻቸውንም ተከፋፍለው ይዘው ሄደው ቀበሩ። ከሟቾቹም መካከል እስከአሁን በደረሰኝ የስም ዝርዝር ውስጥ ወጣት ተስፋጽዮን ዳንኤል በቅጽል ስሙ “ቡችች” ቢንያም ዓለሙ፣ ታደለ ኤልያስ፣ ዘርዬ ደምሴ፣ ሉልሰገድ መለሰ፣ ደባልቄ ገብሬ፣ እና ትርፌ ወንዲፍራው እንደሚባሉ የመረጃ ምንጬ ነግሮኛል። በሆስፒታል ከሚገኙት ውስጥም በሞትና በህይወት መካከል የሚገኙ እንዳሉም ተሰምቷል።
“…በቀጣይ መንግሥትና ሸኔ ልክ እንደ ወለጋውና እንደ ምዕራብ ሸዋው በመርቲ፣ በዶኒ፣ በቲቢላ፣ በመንበረ ህይወት፣ በአዲስ ህይወት፣ በአሩሲ ስሬ፣ በሁሩታ፣ በጮሌ፣ በጉና፤ በአቦምሳ በአጠቃላይ በአርሲ ዞን በችርቻሮ የነበረውን ግድያ ወደ ጅምላ ፍጅት ለማሸጋገር እንዴት እየተዘጋጁ እንዳሉ ነገ ጠዋት አጭር መረጃ አደርሳችኋለሁ። እስከዚያው እንደተለመደው እናንተ ነፍስ ይማር በሉ።
• ነፍስ ይማር።
Filed in: Amharic