>

ኢትዮጵያ እናታችን አባይ ደማችን...!!! (ወንዴ መሸሻ)

ኢትዮጵያ እናታችን አባይ ደማችን…!!!

ወንዴ መሸሻ

 

ኢትዮጵያን የሚወድ በዚህ ምስል ደስ_ይበለው!!
አንዳንድ ኦርቶዶክሳዊ አረብኛ ጽሑፍ ሲያይ የእስልምና ብቻ ይመስለዋል፤ ሌላው ደግሞ የእስክንድርያ ወይም የሶርያ ኦርቶዶክስ ይሆን ብሎ ለማጣራት ይፈጋል። ምክንያቱም በክብረ ነገሥት የሚመሩት ቤተክህነታውያን ያስተማሩን በእስልምና እና ሙስሊም ማንነት ላይ ተጠራጣሪነትን ነውና።
ለሰብአዊ አጀንዳ ወይም ሀገራዊ ኃላፊነት ሙስሊም ወንድምህን ከተጠራጠርክ የተማርከውን ትምህርት ራሱን ተጠራጠረው። ስድብ እና ጥላቻን የሚነግሩህንማ አንተ ራስህ በአክብሮት ንቀፋቸው። የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ወዳጅ መስለው እና ሽፋን አድርገው፣ በአረብ ሀገራት የጥንት ወዳጆቻችን ጥላቻና በሙስሊሙ ግፍ ደልበው ሀገርህን ኢትዮጵያን  ከገደል አፋፍ ያስቀመጧት ሰለሞናውያን መሆናቸውን ካልተረዳህ ክርስትናን አልተረዳኸውም እልሃለሁ።
#ዐጼ_ገብረመስቀልን ከቅዱስ ያሬድ እና አቡነ አረጋዊ ጋር ብቻ አያይዘው ነው የተነገሩህ። እሳቸው ግን ሶርያ ላይ መቅደስ ለመገንባት አናጺ እና የግንባታ ቁሳቁስ በመርከብ ጭነው የላኩ፣ የካዕባን መቅደስ የገነቡ፣ አክሱም ላይ ከተደበቀው የሮም እጆች ጋር ሲዋጉ የተሰዉ፣ አሟሟታቸውን ደብቀው ያስቀሩት ደግሞ የቤተክህነቱ ፍቅረኞች የኋለኞቹ ሰለሞናውያን እንደሆኑ መጻፍትን መርምር። ነብዩ መሐመድ ዝም ብለው ለስደት ጊዜ ብቻ ኢትዮጵያን አልወደዷትም፤ ቀድመው የወደዷት የለመዷት ያመኗት የተማመኑባት የወዳጃቸው ምድር ነች።
የኢትዮጵያን ወዳጅ እንደ ጠላት ፣ አሳዳጆቿን እንደ ወዳጅ አድርጎ የሳሉልህን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሰነዶች ዳግም ካልመረመርክ ኢትዮጵያችን ሰላም አታገኝም። ቤተክርስቲያንህ ላይ #እንደ_አለቃ እና #መዥገር የተጣበቁባት መዋቅር ነው ቤተክህነት ፤ ሌላ ማሽሞንሞኛ አትፈልግለት። ቤተክርስቲያን ክብሯ እና ብርታቷ ገዳማቷ እና የቆሎ ትምህርት ቤቶቿ እንጂ ብዥታዎች ውስጥ ከትቶን ሀገርን እያፈረሰ ያለው የሰለሞናውያኑ መለካዊ ተላላኪ ቤተክህነት አይደለም። #ቤተክህነታዊነት የኢትዮጵያ ሰላም እና አንድነት እንቅፋት ነው።
በየዓመቱ መጋቢት ፲፮ የምዘክረው የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን ተአምር እንዳለ እና የጎንደር ወዳጆቼን ለማመስገን እንደማልረሳ አስታውሱልኝ፤ ለዚህ ዓመት ይህ ጽሑፍ ዝክር ይሁንልኝ። በሕይወት ተርፌ የኢትዮጵያን ጥንታዊና ሰፊ አንድነት ለወገኖቼ በመጽሐፍ የማጋራበት ዕድሜ የተጨመረልኝ ቀን ነውና።
ሆሳዕና_፳፻፲፬ እየደረሰ ነው።
Filed in: Amharic