ስንታየሁ ቸኮል
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የሰራተኞች አቤቱታ ጨምሯል።
ወለጋ ብትወለድ አሩሲ ብታድግ ብሔርህ አማራ እስከሆነ ድረስ ለኦህዴድ ብልፅግና አደጋ ነህ ስለዚህ ከስራ ትባረራለህ የለዉጡ ትሩፋት ይኸው ነው።
በዚህ መሠረት በአራዳ ክ/ከተማ ሰሞኑን እየተሰራ ባለው ምደባ በርካታ ሰራተኞች ቅሬታ አቅርበዋል። ለምደባ የመረጡት ምርጫ ሳይጠበቅና የስራ ልምድ ሳይታይ ያለፍላጎታቸው ብሔራቸዉ ተመዝኖ ተንሳፈው ይገኛል። ሰራተኞቹ እንደሚሉት ዋነኛ መመዘኛዉ ተረኝነት እንደ መስፈርት ያደረገ ከምደባ መመሪያ ውጪ ሕገወጥ ተግባር ተፈፅሟል በማለት ይገልፃሉ።
—–
ዛሬ የሚያልቀው ማሳሰቢያ!
የመንግስት ሰራተኞች መረጃ ቅፅ
የአዲስ አበባ ከተማ መንግስት ሰራተኞች በተረኞች አድራጊ ፈጣሪ በከፍተኛ ምሬት ውስጥ ናቸው። ከንቲባ አዳነች አበቤ በሚመሩት ከተማ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ መስሪያ ቤቶች በኦሮሙማ መነፅር ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ በማለት የተረኝነት ሽግሽግ በደብዳቤ መጥቷል።
ይህ መረጃ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ እስከ መጋቢት 19/07/2014 ዓም ብሔራችሁን ለይታችሁ ንገሩን የተባለበት በአባሪ የተላከ ቅፅ ነው ማንን ለማባረር እንደሆነ ግልፅ ነው።