>

ብልጽግና ያካሄዳቸው "የህዝብ" ውይይቶች     እንደከሸፉበት የውስጥ አዋቂዎች ገለፁ! (ባልደራስ)

ብልጽግና ያካሄዳቸው “የህዝብ” ውይይቶች
    እንደከሸፉበት የውስጥ አዋቂዎች ገለፁ!
ባልደራስ

 

 የመንግሥት ሰራተኞች ደመወዝ እንዲጨመር
    ተጠይቋል!
ገዥው ፓርቲ ብልጽግና ሰሞኑን ካደረገው ጉባኤ በኋላ በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች ያደረጋቸው ውይይቶች እንዳልተሳኩለት የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለፁ፡፡ ፓርቲው ከጉባኤው በኋላ ከሕዝብ ጋር ውይይት አደረኩ ቢልም፣ለይስሙላ ከተሳተፉት አንዳንድ ሰዎች ባሻገር የፓርቲው ደጋፊዎች ናቸው የተባሉ ተመርጠው የተሳተፉበት መድረክ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም መልክ ቢሆን፣ ፓርቲው ከህዝብ የተነጠለ መሆኑን ከደጋፊዎቹ ጭምር የተደመጠበት አጋጣሚ ነበር፡፡
ከተደመጡት አስተያየቶች መካከል፣ የሰላም እጦት፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስና፣ ተረኝነት፣ ዘረኝነት በዋናነት የተነሱት ነጥቦች ሲሆኑ፣ በብልጽግና አመራር በኩል አገሪቷ ከፈተና ወደ ልዕልና እየጓዘች  ነው በሚል መንፈስ ስብሰባዎችን ለመቃኘት የተደረገው ሙከራ አልተሳካም ተብሏል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ ተስፋ ሳይሆን ስጋት እንዳላቸው ማጉላታቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በውይይቶቹ  ከተንፀባረቁት አስተያየቶች መካከል፡-
 
1.ሕዝቡ እህል አጥቶ የሚርበውን ያህል፣ ሠላም እርቦታል፣ መንግሥት በማንነት ላይ  የሚደረጉ ግድያዎችን ማስቆም አለበት፣ መንግሥት ውስጡን ማጥራት አለበት፣
 
2.የቤት ኪራይ ከህዝቡ አቅም በላይ እየሆነ ነው፣ 
 
3.የመንግሥት ሰራተኛ ደመወዝ መጨመር አለበት፣
 
4.በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ዘረኝነት፣ ተረኝነትና ሙስና አስቸግሯል፣
 
5. ህዝብን መናቅ፣ ጥቅምን መፈለግ በከተማዋ ባለሥልጣናት ዘንድ የሚስተዋል ችግር ነው፡፡
በገዥው ፓርቲ ውስጥ አሁን ተስፋ መቁረጥ ፣ ባለችው አጋጣሚ ተጠቅሞ መሹለክ፣ ሀሜት፣ ጥላቻና አለመተማመን ሰፍኖ አንደሚገኝ የውስጥ አዋቂ ምንጮቹ ገልፀዋል፡፡ ፓርቲውንም ከድርጅት  ይልቅ ስብስብ ነው ቢባል የተሻለ መገለጫው ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
Filed in: Amharic