>

"..ለብሄር ፖለቲካ ተጨማሪ መርዝ የጎዳና ኢፍጠር...!!! (ስንታየሁ ቸኮል)

“..ለብሄር ፖለቲካ ተጨማሪ መርዝ የጎዳና ኢፍጠር…!!!

ስንታየሁ ቸኮል


*…. የጎዳና ‘ኢፍጠር’ የሚባል አዲስ ጅሀዳዊ  ፕሮጀክት በብሔር ግጭት አልፈርስ ላለች ኢትዮጵያ ጉሮሮዋን መቁረጫ የመጨረሻ ቢላዋ ነው…!!!

*…. አቡነ ዮሴፍ የመስቀል ዐደባባዩን ኢፍጥር ተቃወሙ

ሀገራችንን የብሄር ፖለቲካ የአልጋ ቁራኛ ላደረጋት በሽታዋ ተጨማሪ መርዝ አክራሪነትን ያባባሰ የጎዳና ኢፍጠር አዲሱ ፕሮጀክት ነው።  ባለፉት ሁለት አመታት የታየው የኦሮቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ለመስቀል ደመራና ሃይማኖታዊ ንግሥ በሚጠቀሙበት መስቀል አደበባይ ኢፍጠር እናደርጋለን በማለት፤ በጉልበት የማስፈጸም ተግባር  ዛሬ ያየነዉ በሰዉና በእምነት ቤቶች የደረሰ ጉዳት ማሳያ ሆኗል።

መንግስትም ለዚህ ተባባሪ በመሆን አንዱን ለማሰደሰት ሌላዉን መግፋት በተለይ ቀደመት ሀገር መስራች ቤተክርሰረቲያን ላይ በተናበበ አንድነት ድንጋይ ውርወራ ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና መዋቅራዊ ጭቆና እየደረሰባት ይገኛል።

ይህ ወደፊት መዘዙ አደገኛ ይመስለኛል። ሀገሪቷ በብሄር ችግር ከመለብለቧ በላይ የሃይማኖት ችግር ተፈጥሮባት ተያይዞ ማለቅ እንጅ መውጫ ያለን አይመስለኝም።

በኦህዴድ አገዛዝ ማሻሪያ የሌለው መርዝ እየተበጠበጠ ነው። የሚመለከታቸው የሃይማኖት አባቶች በአስቸኳይ ማስቆምና ማስተካከያ ሊያበጁለት እና ሊመክሩበት ይገባል።

አቡነ ዮሴፍ የመስቀል ዐደባባዩን አፍጥር ተቃወሙ

ቦታው ቤተ ክርስቲያን ያከበረችው የግል ይዞታዋ ስለኾነ መንግሥት የታሰበውን ያስቁምልን ሲሉ ከጠሚ ጀምሮ ለተለያዩ አካላት በጻፉት ደብዳቤ አስጠንቅቀዋል።

Filed in: Amharic