>

ጋዜጠኛውን መሰወር አቅልሎም ይሁን አሳንሶ ማየት እጅግ አደገኛ ነው....!!! (መስከረም አበራ)

ጋዜጠኛውን መሰወር አቅልሎም ይሁን አሳንሶ ማየት እጅግ አደገኛ ነው….!!!
መስከረም አበራ 

ከጎበዜ ሲሳይ መሰወር የታዘብኩት አንድ ወሳኝ ጉዳይ ለአማራ ህዝብ የሚሟገት ሰው ከመንገዱ ላለመደናቀፍ ሁለት ነገሮችን ብቻ ይዞ መጓዝ እንዳለበት ነው።
የመጀመሪያው  ለደሃው የአማራ ህዝብ ሲሟገት ለሚደርስበት ማንኛውም ነገር መድህን የሚሆነው የአማራ ልሂቅ እንደሌለ አስቦ፣ ለገባው እውነት ብቻውን ዋጋ ለመክፈል ቆርጦ መሆን እንዳለበት ነው።
ሁለተኛው ለአማራ ህዝብ መሟገት የሚያስከፍለው ዋጋ እጅግ አደገኛው፣ውድና ለብቻ መቆምን የሚጠይቅ  እንደሆነ መገንዘብ ናቸው።
 
 
አማራ ጋዜጠኞች የሉትም ወይ⁉
የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይን ጉዳይ የአማራ ጋዜጠኞች በማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻው ከፊት ሆነው ያስተባብራሉ፣ ይመሩታልም የሚል ግምት ነበረኝ። እውነታው ግን ያንን አያሳይም‼
በሌላ በኩል የብአዴን መደበኛና ኢ-መደበኛ “ጋዜጠኞች” የአሳዳሪ ጌቶቻቸውን ፍላጎት ለማሳካት ከመንደፋደፍ ውጪ በተከበረው ሙያ ላይ የሚገለሙቱና ተደራራቢ አጀንዳ በመፍጠር የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ጉዳይ ተሸፋፍኖ እንዲቀር የማድረግ የቀጥታና የተዘዋዋሪ ሚና እየተጫወቱ እንዳለ እያየን ነው። ይህ ተጠባቂ ነው‼
ነገር ግን ከዚህ ብአዴናዊ ስብስብ ውጪ የሚገኙ የአማራ ጋዜጠኞች፥ ይህንን ጉዳይ ከፊት ሆነው ሊመሩትና ሊያስተባብሩ ይገባል‼‼‼ ዛሬም አልረፈደምና‼‼‼
በዚህ አጋጣሚ መረሳት የሌለበት ጉዳይ ቢኖር፥ የአማራ ጋዜጠኞች፥ ከብአዴንና ግብረአበሮቹ ነፃ የሆነ “የአማራ ጋዜጠኞች ማህበር” ፈጥረው እስከዛሬ አለመንቀሳቀሳቸው እነሱም እንዳይጠናከሩና እንዳያድጉ፤ የአማራም ድምፅ ቅርፅ ይዞ እንዳይሰማ አድርጎታል ‼‼
የጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ታፍኖ መሰወር፥ የግለሰብ ጉዳይ አይደለም ብለን ደጋግመን እየተናገርን ነው‼‼‼ የታፈነው የአማራ ህዝብ ድምፅ ነው‼‼‼ የዚህ ወንጀል precedent ደግሞ በቀሪ የአማራ ህዝብ ድምፆች ላይ domino effect አለው‼‼‼
ይህንን አቅልሎም ይሁን አሳንሶ ማየት እጅግ አደገኛ ነው‼‼‼
ህዝባችንም ቢሆን በከሃዲ መደዴዎች እየተካደ ጠንካራ የሚዲያ ተቋም መገንባት ቢሳነው እንኳ፥ እውነተኛ ድምፅ እየሆኑት ያሉትን የአብራኩ ክፋይ ልጆቹን ከነጣቂና አፋኝ ፋሽስት እጅ መታደግ እንዴት ይሳነዋል⁉
የሙያ አጋር የአማራ ጋዜጠኞችስ የመሪነትና የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻው ላይ የቀዳሚነት ሚናውን መውሰድ እንደምን ተሳናቸው⁉ ዛሬ በጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ላይ የተፈፀመው ነውረኛ ፋሽስታዊ ወንጀል፥ ነገ በእነሱ ላይ ሊደገም ቀን እየጠበቀ ያለ ጉዳይ አይደለምን⁉
በግፍ ታፍኖ ስለተሰወረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ዝም አልልም ‼‼
Filed in: Amharic