>

የክፍሉ ታደሰ ነገር [ክፍል ፩] (አቻምየለህ ታምሩ)

የክፍሉ ታደሰ ነገር [ክፍል ፩]

አቻምየለህ ታምሩ

የኢሕአፓው አምበል ክፍሉ ታደሰ ከሰሞኑ በባላገሩ ቴሌቭዥን ላይ ቀርቦ በሰጠው ባለ ሶስት ክፍል ቃለ ምልልስ ኢሕአፓ ኢትዮጵያዊ አላማ የነበረውና ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ትዘምን ዘንድ የታገለ ድርጅት መሆኑን ነግሮናል።
ክፍሉ ታደሰ ኢሕአፓ ኢትዮጵያዊ አላማ ይዞ ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ትዘምን ዘንድ የታገለ ድርጅት እንደሆነ ሊነግረን ቢቃጣውም ኢሕአፓ ግን ደርግ ነሐሴ 10 ቀን 1966 ዓ.ም. ላወጣውና “ኢትዮጵያ ትቅደም” የሚለው መፈክር መሪ ቃሉ መሆኑን ላብራራበት መግለጫው በልሳኑ በዲሞክራሲያ በሰጠው ምላሽ ኢትዮጵያ መቅደም ሳይሆን መውደም ነው ያለባት ብሎ መግለጫ አውጥቶ ነበር።
ኢሕአፓ በሐምሌ ወር 1966 ዓ.ም. በልሳኑ በዲሞክራሲያ ቅጽ 1 ቁ. 2 ገጽ 1 ላይ ባሳተመው ከታች በተያያዘው ድርጅታዊ አቋሙ የደርጎችን “ኢትዮጵያ ትቅደም” መሪ ቃል በመቃወም የለውጥ ተብዮው መሪ ቃል ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለው መሆን እንደለሌበት የሚከተለውን መግለጫ አውጥቷል፤
“ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለው[የደርግ] መሪ ቃል ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ መውደም እንዳለባት እስካላመለከተ ድረስ ለሚፈለገው አብዮታዊ ለውጥ ተገቢ መሪ ቃል ሊሆን አይችልም”
ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ በዚህ መልክ መውደም እንዳለባት በይፋ መግለጫ ያወጣው ድርጅት አምበል ነው እንግዲህ ኢሕአፓ ኢትዮጵያዊ አላማ የነበረውና ታሪካዊቷ ኢትዮጵያ ትዘምን ዘንድ እንደታገለ ሳያፍር ሊነግረን የሚቃጣው።
ለማንኛውም ከታች የታተመው ዶሴ ኢሕአፓ ኢትዮጵያ መቅደም ሳይሆን መውደም እንዳለባት በልሳኑ በዲሞክራሲያ ነሐሴ 18 ቀን 1966 ዓ.ም. ያወጣው መግለጫ ነው።
ይቀጥላል.
Filed in: Amharic