>

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከ500 በላይ አማሮች  ታስረዋል....!!! (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ )

በአዲስ አበባ ዙሪያ ከ500 በላይ አማሮች ታስረዋል….!!!
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ 

ከስንታየሁ ለማ ጋር የፊርማ ንቅናቄውን ሲያስተባብር የነበረው የባልደራሱ ታደሰ ካስሮ አማዶ ታሰረ! 
 
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) ኢትዮጵያ አቀፍ ድርጅት ለመሆን የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ተከትሎ በደቡብ ኢትዮጵያ ከሕዝብ የድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ንቅናቄው ቀጥሏል።
ይህንን ንቅናቄ ሲያስተባብር የነበረው አቶ ስንታየሁ ለማ ከሕግ ውጭ በግፍ መታሰሩን ቀደም ብለን ዘግበናል።
ከስንታየሁ ጋር ሕዝቡን ሲያስፈርም እና ንቅናቄውን ሲያስተባብር የዋለው ሌላኛው የፓርቲው አባል ታደሰ ካስሮ አማዶ፣ በጋሞ ዞን፤ ምዕራብ አባያ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በግፍ ታስሯል።
 በአሁኑ ሰዓት ሁለቱም አባሎች በአንድ ክፍል ውስጥ ከሌሎች እስረኞች ጋር የሚገኙ ሲሆን፣ አንድ ሻለቃ በር ቆልፎባቸው ከሄደ በኋላ ያነጋገራቸው ፖሊስ የለም። ፖሊስ ጣቢያው ቃልም ሆነ አድራሻ አልተቀበላቸውም።
ከስንታየሁና ከታደሰ ጋር በድጋፍ ፊርማ የማሰባሰብ ንቅናቄው ውስጥ ሲሳተፉ የነበሩ ሌሎች ሰዎችን ፖሊስ እየፈለጋቸው ነው።
ሰሞኑን በተከፈተው የእስር ዘመቻ፣ ከባልደራስ አባላት በተጨማሪ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከ500 በላይ አማሮች ታስረዋል።
/
Filed in: Amharic