ባልደራስ
*… የጥቃቱ ዒላማዎች በብዛት ሙስሊሞች ናችው!
/
በኦሮሚያ መስተዳድር ሆሮጉድሩ ወለጋ፤ ጃርደጋ ጃርቴ ወረዳ፤ ደርጌ ኮትቻ ቀበሌ ውስጥ በሚኖሩ አማሮች ላይ ኦነግ-ሸኔ ባለፈው ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ማለዳ 2 ሰዓት ጀምሮ ተኩስ ከፍቷል።
የአማራ ተወላጅ የአካባቢው የሚሊሻ አባላት ወጣቱን በማስተባበር ራሳቸውን እየተከላከሉ ይገኛሉ። በውጊያዎቹ ከሞቱት መካከል ፊት ለፊት እየተፋለሙ የተሰው የ75 ዓመት አዛውንት ይገኙበታል።
የኦነግ/ሽኔ ተዋጊዎች ከትናንት በስቲያ ከነበሩበት በማፈግፈግ አቅጣጫቸውን ቀይቀው አጎራባች በሆነው አሞሮ ወረዳ፤ ስዴን በርከን ቀበሌ ውስጥ አዲስ ተኩስ ከፍተዋል።
አሸባሪው ቡድን በአንዳንድ የኦሮሚያ መስተዳድር ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት እየታገዘ መሆኑንም የዓይን እማኞች ገልፀዋል። የጥቃቱ ኢላማ ከተደረጉት አማሮች መካከል አብዛኞቹ የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው።
በአካባቢው ኗሪ ዘንድ በስፋት የሚታወቁ አንድ ኡስታዝ ከሁለት ሳምንት በፊት ታግተው ቆይተው መለቀቃቸውንም ተናግረዋል።