>
5:21 pm - Tuesday July 20, 8230

የምኒልክ ብርጌድ ዋና አዛዥ ሻለቃ ፋኖ አንተነህ ድረስ  ታስሮ ውሏል! (ባልደራስ)

የምኒልክ ብርጌድ ዋና አዛዥ ሻለቃ ፋኖ አንተነህ ድረስ  ታስሮ ውሏል!

ባልደራስ


*… “ወንጀሉ ወልቃይት ለመሄድ ጉዞ ጀምሯል” የሚል ነው!

*…. የባህር ዳሩ ኘሮፌሰር የሺጌታ ገላው ታሰሩ!

*…. በቡሬ ከተማ የአማራ ህዝባዊ ኃይል(ፋኖ) ወታደራዊ አመራር ታዬ ብርሃኑ ቤት በጥይት ተደበደበ !

*… የፋኖ ጠበቃ አስረስ ማረ ቤት በሕገ ወጥ ሂደት ተበረበረ

*    *    *

የምኒልክ ብርጌድ ዋና አዛዥ የሆነው ሻለቃ ፋኖ አንተነህ ድረስ ታሰረ። ምክትል አዛዡን ጨምሮ የምኒልክ ብርጌድ ከፊል አባላትን በመያዝ ወደ ወልቃየት ጠገዴ ለመጓዝ ከጎንደር ዛሬ ማለዳ ተነስተው የነበረ ሲሆን፣ ይሁን እንጅ ምሴባምባ ፧ልዮ ስሙ ፈረስ መግሪያ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ ፣ “ወደ ወልቃይት መሄድ አትችሉም”በሚል ከባድ መሳሪያ በመጥመድ ጭምር አግተዋቸው ውለዋል።

የብርጌዱ ምክትል አዛዥ ፋኖ መብራቱ ስላለው ሁኔታ ሲናገር ” እኔ የተወለድኩት ወልቃይት ነው፤እውነተኛ ፋኖም ነኝ።ከመንግስት ተለጥፌ ጥቅማጥቅም የማሳድድም አይደለሁም።ብልፅግና ሁን! ዋሽ! ቅጠፍ! ይሉኝ ነበረ።እኔ ግን ለ7 ዓመት የታገልኩት ለአገሬ፣ለሀቅ እና ለሰንደቅ ዓላማየ ነው።መቼም እሞታለሁ እንጅ ለጥቅም ብየ ከውሸት ጋር አልቆምም “በማለት መልሸላቸዋለሁ ብሏል።

አያይዞም “ብልፅግናዎች ስብሰባ ሲጠሩ እኛን አይጠሩንም፤ ለዕውነት የቆምን መሆኑን ስለሚረዱ። ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ትጥቅ ለማስፈታት ሞክረው ነበረ።

Filed in: Amharic